Askwala Home
Upcoming day, World Day of Social Justice, 20 February. 2020 Theme: "Closing the Inequalities Gap to Achieve Social Justice!"

                                      

Inform       Today is Tuesday, February 18, 2020 and day 049 of the year.

Feb 11, 2020 at 06:56 AM

Corona virus update

Informer : Askwala

ቻይና ዉስጥ ከ 900 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ተነገረ። በአንድ ቀን ብቻ 97 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸውን ፔኪንግ የሚገኘዉ የቻይና መንግሥት አስታዉቋል። በሀገሪቱ ከ 40 ሺህ በላይ ቻይናውያን በኮሮና ተኅዋሲ መያዛቸውን መንግሥት አስታውቋል። በቻይና የተዛመተውን የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የቻይና ማዕከላዊ ባንክ ወደ 40 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ሰጥቷል። ቫይረሱን ከሀገሪቱ ለማጥፋት እና መድኃኒት ለማግኘት የተለያዩ የቻይና ኩባንያዎች ለሚያደርጉት ርብርብ ከማዕከላዊ ባንክ የገንዘብ ብድር ማግኘታቸውም ተያይዞ ተዘግቧል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 10, 2020 at 11:22 AM

Corona viruses (made in china) update

Informer : Askwala

ቻይና ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 811 ከፍ ማለቱን ባለስልጣናት ገለፁ ፡፡ ይህም እስካሁን ከነበሩ ተመሳሳይ ወረርሽኞች ብዙ ሰዎች የሞቱበት ወረርሽኝ ያደርገዋል ተብሏል። ከዚህ በፊት እ.ኤ.አ. በ 2002 እና በ 2003 ሳርስ የተባለው ወረርሽኝ የተከሰተ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 774 ነበር። ቻይና ውስጥ በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ቁጥር አሁን ከ 37,200 በላይ የደረሰ ሲሆን የበሽታው ማዕከል የተባለችው የቻይና አውራጃ ሁባይ ናት። በሽታው አምጪ ቫይረስ ከውሃን ከተማ ወደ እዚችው አውራጃ መዛባቱም ተገልጿል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 10, 2020 at 11:18 AM

33ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ

Informer : Askwala

የአፍሪቃ መሪዎች ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም መፍትሔ ነው ያሉትን ሀሳብ አወገዙ። ለሁለት ቀናት በሚቆየው እና ዛሬ በጀመረው 33ኛ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ንግግር ያሰሙት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ መሃመት ባለፈው ወር የቀረበው የሰላም ሀሳብ ዓለም አቀፋን ማህበረሰብ ያላሳተፈ እና የፍልስጤማውያንን መብት የማያከብር ነው ብለዋል። የጉባኤው ታዳሚያንም በጭብጨባ አጋርነታቸውን ገልፀዋል። የህብረቱ የ 2020 ሊቀ መንበር ሆነው የተመረጡት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ደግሞ « አፍሪቃን እንገንባ ጠመንጃዎቹን ዝም እናሰኛቸው» ሲሉ ጥሪያቸውን አሰምተዋል። ሀሙስ ዕለት ከጀርመን መራሂተ መንግስት ጋር የተገናኙት ራማፎሳ ሊቢያ እና ደቡብ ሱዳን ውስጥ ያሉትን ግጭቶች መቋጨት ቅድሚያ የሚሰጡት አላማቸው እንደሚሆን ገልፀው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ በሴቶች መብት ላይ መስራት እንደሚሹ ራማፎሳ ተናግረዋል። ራማፎሳ የአንድ ዓመት የሊቀመንበርነት ስልጣናቸውን የተቀበሉት ከግብፁ መሪ ፕሬዚዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ነው። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 09, 2020 at 12:44 PM

Scholarship opportunity at Royal Holloway, University of London, for Ethiopians

Informer : Askwala

pursue knowledge 

Info source: Royal Holloway University


Feb 09, 2020 at 11:33 AM

2020 ACADEMY AWARD NOMINEES

Informer : Hermella

THE 92ND ACADEMY AWARDS | 2020
Dolby Theatre at the Hollywood & Highland Center
Sunday, February 9, 2020 NOMINEES 

Info source: Oscar


Feb 07, 2020 at 09:04 AM

የሕዋ ተመራማሪዋ ክብረ ወሰን በማሻሻል ወደ ምድር ተመለሰች

Informer : Askwala

የሕዋ ተመራማሪዋ ወደ ምድር ተመለሰች በሕዋ ላይ በመቆየት አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ያስመዘገበችው የናሳ የጠፈር ተመራማሪዋ ክርስቲና ኮች በሰላም ወደ ምድር ተመለሰች። ክርስቲና በዓለም አቀፉ የሕዋ የምርምር ጣቢያ ለ328 ቀናት ከሌሎች ሁለት ባልደረቦቿ ጋር በመሆን ሲያደርጉ የነበረውን የምርምር ስራ አጠናቀው ካዛኪስታን ውስጥ በሚገኝ አንድ ስፍራ ማረፋቸው ታውቋል። የ41 ዓመቷ ክርስቲና በዚህ የሕዋ ላይ ቆይታዋ በሌላኛዋ አሜሪካዊት የናሳ የህዋ ተመራማሪ ቬትራን ፔጊ ዊትሰን ተይዞ የነበረውን የ289 ቀናት ሕዋ ላይ የመቆየት ክብረ ወሰን በማሻሻል ታሪክ ሰርታለች። በህዋ ላይ የመሬት ስበት አልባ ቆይታዋ እንደሚናፍቃት የተናገረችው ኮች በፈለኩት ጊዜ መጣሪያ እና በወለል መሃል ተንሳፎ መቆየት ለእርሷ አዝናኝ እንደነበር ገልጻለች። ከእርሷ ቀድማ ወደ ጠፈር ሶስት ጊዜ የተመላለሰችውን የ59 አመቷን ቬትራን ዊትሰንን ለእኔ ጀግናዬ ናት ስትልም አሞካሽታታለች ።አሜሪካ በህዋ ሳይንስ የምርምር ሥራዎች ሴቶችን ለማትጋት ለሚሰሩ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ሰዓት ኬች ወደ ምድር መመለሷ ሴቶችን በብዛት ወደ መስኩ ለመሳብ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም ተገልጿል። ኮች ከሩሲያው የጠፈር ኤጄንሲ ባልደረባ ዲሚትሪ ሮጎዚን እና ከአውሮጳ የጠፈር ኤጄንሲ ባልደረባ ሉካ ፓርሚታኖ ጋር በመሆን ነው 328 ቀናቱን በህዋ ላይ ያሳለፈችው። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 06, 2020 at 10:51 AM

የንግድ ስራ ፈጠራ ውድድር ማስታወቂያ ለስራ ፈጣሪዎች በሙሉ

Informer : Dire Dawa University

ድሬዳዋ ቴክኖሊጂ ኢንስትቲዩ ከዳሸን ባንክ አዋጭ የሆኑ የንግድ ሃሳቦችን በማወዳደር አሸናፊዎችን ጠቀም ያለ ገንዘብ ለመሸለም በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች ምዝገባ መጀመሩ ይታወሳል! ውድድሩ በመላው ሃገሪቱ ያሉ አዳዲስ የንግድ ሃሳብ ያላቸው ተወዳዳሪዎች የሚያሳትፍ ነው!
ተወዳዳሪዎች የንግድ ሃሳባቸው ችግር ፈቺ ሆኖ ሊተገበር የሚችልና የሃገሪቱን የቴክኖሎጂ አጠቃቀም አንድ ደረጃ የሚያሳደግ መሆን ይኖርበታል፡፡!
የውድድሩ ሂደት የተወዳዳሪዎችን ማንነት የሚገልፅ መረጃን ፣ በአንድ ገፅ ማካተት አለበት፡፡ (ስም ከነአባት፣ ፆታ ፣ እድሜ ፣ የትምህርት ደረጃ ፣ ክልል ፣ ዞን) ፕሮጀክቱን ለመተግበር የተወዳዳሪውን አስተዋፅኦ (በተለይ በበጀት) ያካተተ መሆን አለበት
ውድድሩን በሙያው የጠለቀ እውቀት ያላቸው ዳኞች የሚዳኙት ይሆናል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ ፡- በዋናው በር ላይ እየተመዘገበ ይገኛል በመላው ሀገሪቱ ባሉ የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች
ተወዳዳሪዎች የውድድር ሃሳባቸውን በሁሉም የዳሸን ባንክ ቅርንጫፎች ማስረከብና መመዝገብ ይችላሉ፡፡
ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት የመወዳዳሪያ ሃሳብ ምንነትና አዋጭነት ከሶስት ገፅ መብለጥ የለበትም፡፡ 

Info source: Dire Dawa university


Feb 06, 2020 at 10:24 AM

ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ: ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት ጥራት አስተባባሪ

Informer : Bahir Dar University

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ‘’በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራሮችና አስተዳዳሪዎችን ምርጫ፣ሹመት/ምደባ ለመደንገግ ባወጣው መመሪያ 002/2009 መሰረት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ‘’የመካከለኛ አመራር ምርጫ፣ሹመት/ምደባ መመሪያ ቁጥር 002/2010’’ በዩኒቨርሰቲው ሴኔት አጸድቆ ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡ በዚህም መሰረት በማህበራዊ ሳይንስ ፋኩሊቲ የጠቅላላ የትምህርት ጥራት አስተባባሪ የነበሩት በሌላ ኃላፊነት ምክንያት በመልቀቃቸው ምክንያት በምትካቸው በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መስፈርት፡...... 

Info source: Bahir Dar University


Feb 06, 2020 at 09:59 AM

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በፍጥነት እየተዛመተ ነው ተባለ

Informer : Askwala

የኮሮና ቫይረስ ከተገመተዉ በላይ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የጤና ባለሙያዎችና የሐገራት ባለስልጣናት አስታወቁ።የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት የተለያዩ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸዉን ሳያዉቁ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመገናኘታቸዉ በገዳዩ ቫይረስ የተለከፈዉ ሰዉ ቁጥር እየናረ ነዉ።ይሁንና በቫይረሱ እስካሁን ሰዎች የገደለዉ ዋናዋ ቻይና፣ የቻይና ልዩ ግዛት በሆነችዉ ሆንግ ኮንግ እና ፊሊፒንስ ዉስጥ ነዉ።እስከ ዛሬ ድረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 492 ደርሷል። በቫይረሱ የተለከፈዉ ሰዉ ቁጥር ደግሞ 24,500 ነዉ።አብዛኛዉ ሰዉ የቻይና ዜጋ ወይም ቻይና ዉስጥ የሚኖር ሲሆን ጃፓን ዉስጥ 35፣ ሲንጋፑር 28 እና ታይላድ ዉስጥ 25 ሰዉ በቫይረሱ በመለከፍ ከቻይና ቀጥሎ ከአንድ እስከ ሶስት ያለዉን ስፍራ ይይዛሉ።ባጠቃላይ በ26 ሐገራት በተሕዋሲዉ የተጠቁ ሰዎች መኖራቸዉ ተረጋግጧል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 06, 2020 at 09:53 AM

በአዲስ አበባ በኦርቶዶክስ አማኞችና በፀጥታ ኃይሎች ግጭት ሁለት ሰዉ ተገደለ

Informer : Askwala

በአዲስ አበባ ዉስጥ ቦሌ ክፍለ-ከተማ በልማዱ 22 ተብሎ በሚጠራዉ አካባቢ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችና በፀጥታ አስከባሪዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ሁለት ሰዎች መሞታቸዉና እና 17 መቁሰላቸዉን የዓይን ምስክሮች አስታወቁ።ግጭቱ የተነሳዉ አንዲት ቤተ-ክርስቲያንን «ሕገ-ወጥ» በማለት ከሌሌቱ 7 ሰዓት ግድም ለማፍረስ ወደ አካባቢዉ በተጓዘ የፀጥታ አስከባሪ ጓድና በአካባቢዉ በነበሩ ወጣቶች መካከል በተፈጠረ አተካራ ነዉ። በአካባቢው የነበረ አንድ የዐይን እማኝ እንደተናገረው «ፀጥታ አስከባሪዎቹ ቤተ-ክርስቲያኑን ለማፍረስ እንደመጡ ሲናገሩ፣ ወጣቶቹ እራሳቸዉን መቆጣጠር ተሳናቸዉ፤ ፀጥታ አስከባሪዎቹ አስለቃሽ ጢስ ተኮሱ።ወጣቶቹ ድንጋይ መወርወር ጀመሩ።ፀጥታ አስከባሪዎቹ ሽጉጥ ተኮሱ» እያለ ይተርካል። የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ፣ ለግድያዉ ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን ለፍርድ ለማቅረብ ቃል ገብተዋል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 05, 2020 at 11:02 AM

Ending Female Genital Mutilation by 2030

Informer : Askwala

Female genital mutilation (FGM) comprises all procedures that involve altering or injuring the female genitalia for non-medical reasons and is recognized internationally as a violation of the human rights, the health and the integrity of girls and women.

Girls who undergo female genital mutilation face short-term complications such as severe pain, shock, excessive bleeding, infections, and difficulty in passing urine, as well as long-term consequences for their sexual and reproductive health and mental health.

Female circumcision involves removing part or all of a woman’s labia and clitoris and is usually performed on girls entering adolescence. This practice is painful, and often harmful, to the women of societies that perform it, but many of those societies claim that the practice is important and deeply rooted in their culture.

To promote the elimination of female genital mutilation, coordinated and systematic efforts are needed, and they must engage whole communities and focus on human rights, gender equality, sexual education and attention to the needs of women and girls who suffer from its consequences. 

Info source: United nations and Microsoft Encarta


Feb 05, 2020 at 10:40 AM

የኮሮና ተሐዋሲ በፍጥነት እየተዛመተ ነው

Informer : Askwala

ቻይና በኮሮና ተሐዋሲ የተነሳ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 425 መድረሱን ዐስታወቀች። ከቻይና ውጪ ደግሞ ሆንግ ኮንግ እና ፊሊፒንስ ውስጥ ኹለት ሰዎች ሞተዋል። የኮሮና ተሐዋሲ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከሃያ ሺህ በልጧል። የቻይና ብሔራዊ ጤና ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቻ 20,438 ሰዎች የኮሮና ተሐዋሲ አለባቸው። ከቻይና ውጪ ቢያንስ 180 ሰዎች በተለያዩ ሃገራት ውስጥ የኮሮና ተሐዋሲ እንዳለባቸው ተዘግቧል፤ 12ቱ ጀርመን ውስጥ ይገኛሉ። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 05, 2020 at 10:08 AM

የገናሌ ዳዋ ቁጥር 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ተመረቀ

Informer : Askwala

ደቡብ ምሥራቅ ኢትዮጵያ በዳዋ ወንዝ ተፋሰስ ላይ የተገነባው የገናሌ ዳዋ ቁጥር 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ትናንት መመረቁ ተዘገበ። 9 ዓመታት ለዘለቀው የኃይል ማመንጫ ግንባታ 451 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደፈሰሰበትም ታውቋል። የገናሌ ዳዋ ቁጥር 3 የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግንባታ የተጀመረው በ2003 ዓ.ም ነበር። ፕሮጀክቱ የተመራው በቻይናው ጌዙባ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ (CGGC)መኾኑም ተጠቅሷል። የኃይል ማመንጫው ሦስት ጀኔነሬተሮች እንዳለው እና እያንዳንዳቸውም 84.7 ሜጋ ዋት በድምሩ 254 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳላቸው ተዘግቧል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 04, 2020 at 01:26 PM

CALL FOR ABSTRACT, Rift Valley University

Informer : Rift Valley University

The Research and Community Outreach Office of the Campus is highly pleased to announce its Second In-House Research Seminar to be held on 28th of February 2020. Therefore, this is to kindly invite potential academics, researchers and practitioners submit a Research Abstract on one of the following thematic areas: – 

Info source: Rift Valley University


Feb 04, 2020 at 01:23 PM

Call for Papers, Rift Valley University

Informer : Rift Valley University

Rift Valley University is going to organize its 12th Annual Research Conference on the theme “Commitments of Ethiopian Higher Education Institutions in Promoting Peace Building Activities through Collaborative Work” 

Info source: Rift Valley University


Feb 04, 2020 at 12:55 PM

Call for paper from ITYOPIS Journal

Informer : Mekelle University

We are happy to inform you that ITYOPIS Northeast African Journal of Social Sciences and Humanities (NEAJ) is now accepting manuscripts for publication on any of the following themes... 

Info source: Mekelle University


Feb 04, 2020 at 11:17 AM

Vacancy, Academic Dean, School of Earth Sciences

Informer : Bahir Dar University

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ‘’በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራሮችና አስተዳዳሪዎችን ምርጫ፣ ሹመት/ምደባ ለመደንገግ ባወጣው መመሪያ 002/2009 መሰረት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ‘’የመካከለኛ አመራር ምርጫ፣ ሹመት/ምደባ መመሪያ ቁጥር 002/2010’’ በዩኒቨርሰቲው ሴኔት አጸድቆ ተግባራዊ እያደረገ ነው፡፡
በዚህም መሰረት ለ School of Earth Sciences አካዳሚክ ዲን በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡

ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ አካዳሚክ ዲን - School of Earth Sciences

የማወዳደሪያ መስፈርት፡-

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

አመልካቾች፡-

ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው ድህረ-ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ጥር 21/05/2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሰቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የዩኒቨርሰቲው ግንኙነት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች 0923 297333 ወይም 0918353494 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡
ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 

Info source: Bahir Dar University


Feb 04, 2020 at 10:52 AM

Scholarship call for the Postdoctoral programme

Informer : Bahir Dar University

2020 Call for applications of the CUI-TWAS Fellowships
The CUI-TWAS Fellowships call for applications is now open for PhD and
postdoctoral programmes.
These are offered in the natural and related applied sciences to
students and researchers from developing countries to gain postgraduate
education and research experience at the COMSATS University Islamabad
(CUI), Pakistan.

Deadline to apply: 16 March 2020.

Applications from women scientists and nationals from S&T-Lagging
countries (STLC) are highly encouraged.
Applications from non-STLC developing countries are also accepted. 

Info source: Bahir Dar University


Feb 04, 2020 at 10:48 AM

Scholarship call for the Postgraduate programme

Informer : Bahir Dar University

2020 Call for applications of the CUI-TWAS Fellowships
The CUI-TWAS Fellowships call for applications is now open for Postgraduate programmes.
These are offered in the natural and related applied sciences to
students and researchers from developing countries to gain postgraduate
education and research experience at the COMSATS University Islamabad
(CUI), Pakistan.

Deadline to apply: 16 March 2020.

Applications from women scientists and nationals from S&T-Lagging
countries (STLC) are highly encouraged.
Applications from non-STLC developing countries are also accepted. 

Info source: Bahir Dar University


Feb 04, 2020 at 10:22 AM

የአሜሪካ የጉዞ እገዳ

Informer : Askwala

የደኅንነት ደረጃዎችን አያሟሉም ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በፈረጇቸው ስድስት ተጨማሪ ሃገሮች ላይ የትረምፕ አስተዳደር በሕጋዊው ኢሚግሬሽን ላይ ገደብ እንደሚጥል አስታውቋል።
ከኪርጊዝስታን፣ ከማያንማር፣ ከኤርትራ፣ ከናይጀሪያ፣ ከሱዳንና ከታንዛንያ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ በሚፈልጉ ሰዎች ወይም ኢሚግራንቶች ላይ አንዳንድ የመግቢያ ፍቃዶች ወይም ቪዛዎች ላይ አዳዲስ እገዳዎችን እንደሚያደርጉ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

አዋጁ ላይ ፕሬዚዳንቱ የፊታችን ዐርብ ከፈረሙ በኋላ ከየካቲት 12/2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታውቋል። 

Info source: VOA


Feb 04, 2020 at 10:04 AM

ጄኔቫ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ

Informer : Askwala

የኮሮና ተህዋሲ ሥርጭትን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ጉዞ እና ንግድ ውስጥ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት የሚያደርጉ እርምጃዎችን መውሰድ እንደማያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አሳሰቡ።ሃላፊው ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሃገራት ከኮሮና ተህዋሲ ጋር በተያያዘ የሚወስዷቸው እርምጃዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ እና የማይዋዥቅ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮናን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ሲል ባለፈው ሐሙስ ነበር ያወጀው። በኮሮና ተህዋሲ ሰበብ የተደረጉ የበረራ ገደቦች እና ከቻይና በሚመጡ መንገደኞች ላይ የተጣለው እገዳ በቻይና ላይ ዓለም አቀፍ መገለል አስከትሏል።ቻይና ውስጥ በተህዋሲው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 361 ደርሷል።በተህዋሲው መያዛቸው የተረጋገጠው ደግሞ 17238 ናቸው።በ23 ሃገራት ደግሞ 151 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተነግሯል። በተህዋሲው የተያዘች አንዲት ሴት ፊሊፒንስ ውስጥ ሞታለች። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 04, 2020 at 09:49 AM

አዲስ አበባ ጠ/ሚ ዓቢይ በተወካዮች ም/ቤት የሰጡት ማብራሪያ

Informer : Askwala

የታገቱ የዶምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ጉዳይ ውስብስብ እና መንግሥትም እደፈለገው መናገር ያልቻለበት መሆኑን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ አስታወቁ።ዶክተር ዓቢይ ትናንት በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከምክር ቤቱ አባላት የዶምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ ጨምሮ በሌሎች የሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች በሰጡት መልስ እስካሁን እገታውን ፈጽሜያለሁ ብሎ ራሱን ይፋ ያደረገ የተደራጀ ኃይል እንደሌለ ተናግረዋል።የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው ባደረገው አሰሳም የተጎዳም ይሁን የሞተ አለማግኘቱን ገልጸዋል። የሰዎቹ ሕይወት ለአደጋ እንዳይጋለጥ መንግሥት ጉዳዩን በጥንቃቄ መያዙን ያስረዱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን ለማጣራት የተቋቋመው ኮሚቴ ስራውን ሲያጠናቅቅ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።የምዕራብ ወለጋ የፀጥታ ችግር በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት መልስ የመንግሥት ፍላጎት ችግሩን በድርድርና በንግግር በሰላማዊ መንገድ መፍታት መሆኑን አስታውቀዋል።ያም ሆኖ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ መውሰዱ የግድ እንደሚሆን ነገር ግን ችግሩን በሰላም እንዲፈታ የሚፈልግ ኃይል ካለ እንደሚቀበል ገልጸዋል።ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በትናንት የምክር ቤት ገለጻቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ወደ ግል ስለማዛወር ፣ስለ ኢትዮ ቴሌኮም እና ስለ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች ጉዳዮች ማብራሪያ ሰጥተዋል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Feb 03, 2020 at 12:02 PM

Call For Papers, The 7th annual international research symposium

Informer : Debre Berhan University

The 7th annual international research symposium of Debre Berhan university will be held on may 8 and 9, 2020 in Debre Berhan University, Ethiopia. Hence, all interested researchers, experts\' practitioners and scholars are invited to submit completed research papers....  

Info source: Debre Berhan university


Feb 03, 2020 at 11:03 AM

የኅዳሴ ጉዳይ የጋራ መግለጫ

Informer : Askwala

በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ላለፉት ሦስት ቀናት የመከሩት ኢትዮጵያ፣ ግብፅና ሱዳን እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስና የዓለም ባንክ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር የሕዝብ ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ባሠራጨው መግለጫ የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችና ልዑኮቻቸው በታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ አሞላልና ሥራ ላይ ከጥር 19/2012 ዓ.ም. እስከ ዛሬ ጥር 22/2012 ዓ.ም. ዋሺንግተን ዲ.ሲ. ውስጥ ባደረጉት ድርድር ላይ በታዛቢነት እየተሣተፉ ካሉት የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስትር እና የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር መገናኘታቸውን አስታውቋል።

በስብሰባዎቻቸው ማብቂያ ሚኒስትሮቹ በአጠቃላይ ስምምነቱ መፈረም ባለባቸው ሦስት ነጥቦች ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አመልክቷል።

ነጥቦቹም አንደኛ፣ የታላቁ ኅዳሴ ግድብ ደረጃ በደረጃ አሞላል የጊዜ ሰሌዳ፤ ሁለተኛ፣ በድርቅና በተራዘመ ድርቅ ጊዜና በተራዘሙ ደረቅ ዓመታት ወቅት የግድቡ አሞላል ቅነሳ ሥርዓት፤ እንዲሁም ሦስተኛ፣ በድርቅና በተራዘመ ድርቅ ጊዜና በተራዘሙ ደረቅ ዓመታት ግድቡን የማንቀሳቀስ ዓመታዊና የተራዘመ ጊዜ ቅነሳ ሥርዓት መሆናቸውን የጋራ መግለጫው አመልክቷል።

በተጨማሪም ሚኒስትሮቹና ልዑኮቻቸው በመደበኛው የእርጥበትና የውኃ ግኝት ሁኔታዎች ውስጥ በግድቡ ዓመታዊና የተራዘመ ጊዜ የማንቀሳቀስ ሥርዓት ዝግጅት ማጠናቀቅ ላይ እንዲሁም በቅንጅት ሥርዓት፣ በውዝግብ አፈታት ደንቦችና በመረጃ ልውውጥ ላይ መወያየታቸውንና መስማማታቸውንም መግለጫው ጠቁሟል።

በተጨማሪም ለግድቡ ደኅንነትና ለተንጠለጠሉ የተፈጥሮ አካባቢና የማኅበራዊ ጫና ጥናቶችም መፍትኄ ለመስጠት መስማማታቸውም በጋራ መግለጫው ተጠቁሟል።

ከላይ የተጠቀሱትን ስምምነቶች ያካተተ የመጨረሻ የሥምምነት ሰነድ ለፌብርዋሪ 2020 ዓ.ም. መጨረሻ (የካቲት 2012 ዓ.ም. የመጨረሻ ሣምንት) እንዲያዘጋጁ ሚኒስትሮቹ ለቴክኒክና ለህግ ቡድኖቻቸው ትዕዛዝ መስጠታቸውንም መግለጫው አስታውቋል።

ወሰን ተሻጋሪ ትብብርን፣ አካባቢያዊ ልማትና ምጣኔ ኃብታዊ መቀናጀትን ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ ከስምምነቱ የሚመነጩ ጉልህ አካባቢያዊ ጥቅሞችን ሚኒስትሮቹ እንደሚገነዘቡ ወይም ዕውቅና እንደሚሰጧቸው አመልክቷል የአምስቱ ወገኖች የጋራ መግለጫ።

ጥቁር አባይን በማልማት የኢትዮጵያን፣ የግብፅንና የሱዳንን ሕዝቦች ሕይወቶች ለማሻሻል የወሰን ተሻጋሪ ትብብርን አስፈላጊነት ሚኒስትሮቹ በድጋሚ ማረጋገጣቸውን የጋራ መግለጫው አመልክቷል። 

Info source: VOA


Feb 03, 2020 at 10:52 AM

ፍልስጤማውያን በሊባኖስ ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ

Informer : Askwala

የእስራኤል እና ፍልስጤማውያንን ግጭት በዘላቂነት ይፈታል በማለት ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረበችውን የሰላም ሃሳብ በመቃወም በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን እና ሊባኖሳውያን ሊባኖስ በሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሟቸውን አሰሙ። ሰልፈኞቹ የፍልስጤምን ሰንደቅ አላማ በመያዝ «ሞት ለአሜሪካ ፣ሞት ለእስራኤል! በሞታችን የፍልስጤም ትንሳዔ እናረጋግጣለን የሚሉ መፈክሮችን ሲያሰሙ መዋላቸውን AFP ዘግቧል። በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የረቀቀው ይኸው የሰላም ሃሳብ የእየሩሳሌም ከተማን ጨምሮ ሌሎች በእስራኤል ተይዘው ያሉትን አካባቢዎች ለእስራኤል ይሰጣል። ሰልፈኞቹ በቤይሩት በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አጥር ድረስ በመጠጋታቸው ፖሊስ አስለቃሽ ጋስ በመጠቀም በትኗቸዋል። በትንሹ ሶስት ሰዎችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተነግሯል። በሊባኖስ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ስደተኞች የሚገኙ ሲሆን በ12 የስደተኞች ጣቢያዎች የሰላም ሃሳቡ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ። የፍልስጤሙ ፕሬዚዳንት መሀሙድ አባስ ቅዳሜ ጥር 23 ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ በግብጽ ተሰባስበው የነበሩት የአረብ ሊግ አባል ሃገራት የሰላም ሃሳቡን ውድቅ አድርገውታል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Jan 31, 2020 at 11:07 AM

Call for Papers – Advancement of Science and Technology for Sustainable Development

Informer : Debre Markos University

Debre Markos Institute of Technology will hold its 2nd National Conference under a main theme “Advancement of Science and Technology for Sustainable Development” on May 2 & 3, 2020 at Debre Markos, Ethiopia. 

Info source: Debre Markos University


Jan 31, 2020 at 10:13 AM

4ቱ ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው ተረጋገጠ

Informer : Askwala

በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሊሆን ይችላል በሚል ጥርጣሬ በተገለል የሕክምና ማዕከል የቆዩ አራት ኢትዮጵያውያን ከህመሙ ነፃ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ምኒስትር ድዔታ ዶ/ር ሊያ ከበደ አስታወቁ። ምኒስትሯ ደቡብ አፍሪካ በተደረገ ምርመራ አራቱ ተማሪዎች ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል።በቫይረሱ ተይዘዋል ተብለው ከተጠረጠሩት አራቱ ተማሪዎች ሦስቱ ቫይረሱ ከተከሰተበት ኹዋን ከተባለዉ የቻይና ግዛት የመጡ ነበሩ።የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው እንደሌለ አስታውቋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዘ የጤና ችግር አልደረሰባቸውም ሲል አስታወቀ።በቻይና ቻንቺግ ግዛት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተጠባባቂ ቆንስል ጀነራል አቶ አንተነህ ታሪኩ ተማሪዎቹ በሙሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።አቶ አንተነህ እንዳሉት አስፈላጊ ከሆነ መንግሥት ዜጎችን ለማውጣት ዝግጁ ነው።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ወደ ቻይና የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ሙሉ በሙሉ አቋርጧል።ሮይተር ዜና አገልግሎት የአየር መንገዱን የመንገደኞች የስልክ ጥሪ ማዕከልን ጠቅሶ እንደዘገበው ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጠዋል የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Jan 30, 2020 at 04:26 PM

Art gallery at Addis Fine Art

Informer : Addis Fine Art

No Country for Young Men, Tesfaye Urgessa
Jan 30 - Feb 15, 2020

Tesfaye Urgessa’s first solo show with Addis Fine Art, No Country for Young Men, runs until the 15th of February 2020. The exhibition explores subject matters such as social criticism, race, and the politics of identity, influenced by his own experiences as an immigrant living in Germany and witnessing first hand the 2015 migrant crisis. 

Info source: Addis Fine Art


Jan 29, 2020 at 10:11 AM

ባህርዳር ተቃውሞ ሰልፎች በተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች

Informer : Askwala

ከደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች የታገቱት በአብዛኛው ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲለቀቁ መንግሥትን የሚጠይቁ ሰልፎች በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ዛሬ ተከናወኑ። ወደ አደባባዮች የተመሙት ሰልፈኞች «ተማሪዎቹ የት ናቸዉ? እህቶቻችንን መልሱ፤ ስለታገቱት ተማሪዎች ዝም አልንልም፤ ፍትኅ ለታገቱ እህት ወንድሞቻችን፤ የሕግ የበላይነት ይከበር፤ መንግሥት የት አለ? እህቶቻችን ይፈቱ» የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል። በባሕር ዳር ከተማ ቁጥሩ ከፍተኛ የኾነ ነዋሪ ለሰፍል አደባባይ የወጣ ሲኾን፤ የፌደራሉንና የአማራ ክልል መንግስትን የሚወቅሱ መፈክሮች መሰማታቸው ታውቋል። አንዳንድ የሰልፉ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት መንግስት ከሚገባው በላይ ቸልተኝነቱን አሳይቷልም ብለዋል። ማንነታቸው ባልታወቀ ሰዎች የታገቱት በአብዛኛው ሴት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከታገቱ ከ50 ቀናት በላይ የኾናቸው ሲኾን፤ መንግስት 17ቱ ተለቀዋል ብሏል። ኾኖም እሰካሁን አንዳቸውም ከቤተሰቦቻቸው አልተገኛኙም። በዋሽንግተን ዲሲም ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተገኝተው ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Jan 29, 2020 at 09:53 AM

አዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተጠረሩ 4 ኢትዮጵያዉያን አሉ ተባለ

Informer : Askwala

በኮሮና ተሐዋሲ ሳይያዙ አልቀረም በሚል የተጠረጠሩ 4 ሰዎች አዲስ አበባ ውስጥ ከኅብረተሰብ በማይቀላቀሉበት ገለልተኛ ቦታ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸዉ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ዐስታወቀ። በተሐዋሲው የተጠረጠሩት አራቱም ኢትዮጵያዊያን ናቸዉ ተብሏ። ሦስቱ ኢትዮጵያዉያን ቫይረሱ በተከሰተበት ኹዋን ከተባለዉ የቻይና ግዛት የመጡ መኾናቸውም ተገልጧል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ሙኒር ካሳ እንደተናገሩት ኮሮና ተሐዋሲ ተስፋፍቶበታል ተብሎ ከተነገረባቸው ከተሞች ብሎም በአጠቃላይ ከቻይና የሚመጡ ተጓዦች ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣብያ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል። «ከመጡት መካከል ትኩሳት ያለባቸውን ከኅብረተሰቡ ጋር እንዳይቀላቀሉ አድርገን [ለብቻቸው እናቆያቸዋለን] በአኹኑ ሰአት አራት አብዛኛው ኢትዮጵያያውያን የኾኑ ተማሪዎች ከዚህ ሀገር ስለመጡ፤ ከመጡት መካከል ደግሞ ኹለቱ እንደ ጉንፋን ነገር ስላላቸው ከኅብረተሰቡ እንዳይቀላቀሉ ለይተን አስቀምጠናቸዋል። በአኹኑ ሰአት ኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ ቫይረስ ተገኘ ተብሎ የተባለው ውሸት ሙሉ ለሙሉ ውሸት ነው። የሰጠነው መግለጫም የሚያሳየው ይኼንን እንጠረጥራለን፤ ማንኛውም ትኩሳት ያለው እና ከነዚህ አካባቢ የሚመጣን ሰው ስክሪን እያደረግን ወደሀገር ውስጥ እንዳይገባ እየተከላከልን ነው።»ቀደም ሲል የአፍሪቃ ኅብረት የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል በሰጠዉ መግለጫ የኮሮና ተሐዋሲን ለመከላከል ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እየተሠራ ነዉ ብሏል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Jan 27, 2020 at 04:39 PM

እነሆ ሌላ አዲስ ዜና (askwala loan calculator)

Informer : Space

አስኳላ ሎን ካልኩሌተር (askwala loan calculator ) የተሰኘ አዲስ ካልኩሌተር ተለቋል
እርስዎ የሆነ ያህል ብር ከባንክ ሲበደሩ በስተመጨረሻ ከነወለዱ ምን ያህል ብር እንደሚከፍሉ እና በየወሩም ምን ያህል ብር ለባንክ እንደሚገብሩ ይወቁ
ካልኩሌተሩን ለማግኘት ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ. 

Info source: space


Jan 27, 2020 at 09:51 AM

Road to Arteficial Intelligence (AI)

Informer : Space

Ethiopia has set a plan to establish an artificial intelligence (AI) research and development center. Council of Ministers has announced that it is a time towards Artificial intelligence.  

Info source: askwala


Jan 26, 2020 at 01:26 PM

የ ዊንዶ 7 የሳይበር ደህንነት ድጋፍ መቋረጥ

Informer : Askwala

የማይክሮ ሶፍት ኩባንያ ምርት የሆነዉ «ዊንዶ 7» የተባለዉ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ከኩባንያዉ ይደረግለት የነበረዉ የሳይበር ደህንነት ድጋፍ ከጎርጎሮሳዉያኑ ጥር 15ቀን 2020 ጀምሮ ተቋርጧል። በመሆኑም ከዚህ በኋላ «ዊንዶ 7»ን መጠቀም የተጠቃሚዎችን መረጃ ለጥቃት ያጋልጣል ሲል ኩባንያዉ አስጠንቅቋል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Jan 26, 2020 at 01:09 PM

ፕሬዝዳንት ዢ ጂንጂንግ ቻይና በአዲሱ ቫይረስ አደጋ ውስጥ ገብታለች ሲሉ አስጠነቀቁ

Informer : Askwala

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ በሚገኘው እና 1,300 ሰዎችን በያዘው አዲስ ቫይረስ ሳቢያ አገራቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አስጠነቀቁ። ከዚህ ቀደም በዚያው በቻይና ተከስቶ ከነበረው የሳርስ ቫይረስ ይመሳሰላል የተባለው አዲስ የቫይረስ ወረርሽኝ በ30 ግዛቶች ተስፋፍቷል። ከቻይና ውጪ በጃፓን፣ በደቡብ ኮሪያ እና በአሜሪካም ይኸው ቫይረስ በሰዎች ላይ ተገኝቷል። ፈረንሳይ በቫይረሱ የተያዘ ሰው በግዛቷ በማግኘት የመጀመሪያዋ የአውሮፓ አገር ሆናለች። ፈረንሳይ የቫይረሱ ሥርጭት ከበረታባት የውኻን ከተማ ዜጎቿን ለማውጣት ተዘጋጅታለች። ቫይረሱ እጅግ አደገኛ በሆነ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ቻይናን የሚመራው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በጠንካራ አመራር መፍትሔ መሻት እንዳለበት አሳስበዋል።ውኻን የተባለችው የአስራ አንድ ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ ከተማን ጨምሮ ሌሎች 18 የቻይና ከተሞች የሕዝብ መጓጓዣዎችን ሙሉ በሙሉ አግደዋል። በውኻን አጠገብ ቻይና በቫይረስ የተያዙ ሕሙማንን ለማከም 10,000 አልጋዎች የሚኖሩት ሆስፒታል በ270,000 ስኩዌር ጫማ መሬት ላይ በ6 ቀናት ለመገንባት ሥራ ጀምራለች።እስካሁን 41 ሰዎችን የገደለው ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር ሖንግ ኮንግ በከተማዋ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከልክላለች። ለሁለት ሳምንታት ትምህርት ቤቶች እንደሚዘጉም የሖንግ ኮንግ መሪ ላሪ ላም አስታውቀዋል። ሳይንቲስቶች ስለ ቫይረሱ ዛሬም በቂ መረጃ ባይኖራቸውም ከእንስሳት ወደ ሰው ሳይሸጋገር እንዳልቀረ ይነገራል። EB-LA 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Jan 26, 2020 at 01:04 PM

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአማራ ክልል መንግሥትን ሊከስ ነው

Informer : Askwala

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሞጣ ከተማ በመስጂዶች እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ንብረት ላይ ለተፈጸመው ጥቃት «አጥጋቢ እርምጃ» አልወሰደም ያለውን የአማራ ክልል ሊከስ መዘጋጀቱን አስታወቀ። በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ በሞጣ እና ሌሎች የአማራ ክልል ከተሞች «ለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች፤ ለደረሰ የገንዘብ፣ የንብረት እና የሥነ-ልቦና ቀውስ በሕግ ለመጠየቅ » ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የሕግ ክፍል ትዕዛዝ መስጠቱን አስታውቋል። ምክር ቤቱ በመግለጫው የሞጣውን ድርጊት «የሽብር ጥቃት» ሲል ገልጾታል። በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ባለፈው ታኅሳስ መስጊዶች ከተቃጠሉ በኋላ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተቃውሞ ሰልፎች ሲካሔዱ ነበር። ድርጊቱ "ስርዓት አልበኛ የሆኑ ቡድኖች" እንደፈጸሙት ያስታወቀው የክልሉ መንግስት ተጠጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል። አምስት ጥያቄዎች ለክልሉ መንግሥት ያቀረበው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እስካሁን ይፋ መልስ አለማግኘቱን አስታውቋል። ምክር ቤቱ «በሞጣ ለደረሰው የሽብር ጥቃት የከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም የክልሉ መንግሥት ገለልተኛ የአጣሪ ኮሚቴ ያላዋቀረ ሲሆን እየተወሰደ ያለው የህግ እርምጃም አጥጋቢ አይደለም» ሲል ነቅፏል። "የፌደራል መንግሥት ገለልተኛ የምርመራ ቡድን በመላክ የደረሰውን የሽብር ጥቃት እንዲያጣራ እንዲሁም በወንጀለኞች ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስድ» ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። በሀረር፣ ድሬዳዋ እና ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ላይ እየደረሰ ነው ያለው «ትንኮሳ» እንዲቆም ጠይቋል። 

Info source: ዶይቼ ቬለ


Jan 24, 2020 at 01:04 PM

Corona viruses

Informer : Rediet

All you need to know about Corona viruses and take care  

Info source: Agence France Presse


Jan 24, 2020 at 01:03 PM

Corona viruses

Informer : Rediet

All you need to know about Corona viruses and take care  

Info source: Agence France Presse


Jan 24, 2020 at 01:00 PM

Corona viruses

Informer : Rediet

All you need to know about Corona viruses and take care  

Info source: Agence France Presse


Jan 24, 2020 at 12:57 PM

Corona viruses

Informer : Rediet

All you need to know about Corona viruses and take care  

Info source: Agence France Presse


Jan 24, 2020 at 12:56 PM

Corona viruses

Informer : Rediet

All you need to know about Corona viruses and take care  

Info source: Agence France Presse


Jan 23, 2020 at 10:06 AM

World’s Most Admired Companies

Informer : Askwala

world\'s most admired companies according to Fortune, Apple claims the top spot for 13 straight years in fortune\'s annual ranking of world\'s most admired companies. To view the lists click the below link... 

Info source: Fortune


Jan 22, 2020 at 04:45 PM

CALL FOR ABSTRACTS

Informer : Debre Markos University

The First Annual National Research Conference (May 2-3,2020)

Institution of Educational and Behavioral Science Will host its first National Research Conference under the grand theme “Quality Education for Character and Personality Development” from May 2-3,2020. 

Info source: Debre Markos University


Jan 22, 2020 at 03:29 PM

Vacancy Announcement Child Health and Mortality Surveillance (CHAMPS) Ethiopia Assistant IT Systems and Datacentre Specialist

Informer : Haramaya University

JOB PURPOSE:

This is an entry level position for this opening. The holder will be responsible for software development of Software applications in the environment that meets HHR objectives in accordance to set standards.

JOB DESCRIPTION

Post: Assistant IT System and Datacentre specialist

Location Haramaya University, Oromia, Ethiopia

Responsible to: Chief Technology Officer

Full Time/Part Time/Casual: Full time

No. of posts 1

Duration of contract 1 year with likely extension

Salary: 10,000 Birr per month

Place of application:

1. Haramaya University Cluster Human Resource Management Office, College of Business and Economics Building.
2. Haramaya University College of Health and Medical Sciences, Human Resource Management and Development Associate Director Office, No.7 at Harar.
3. Haramaya University Liaison Office at Addis Ababa, Arat Kilo. Former Germany Cultural Institute Building Office No.15
Application Deadline: 8 (Eight) working days after the day of advertisement

SKILLS AND COMPETENCE:

1. Degree level in Engineering or Computer Science or BSc IT and experience of least 1 years in IT.
2. Excellent customer support and communication skills
3. Experience of installing and supporting Windows 20xx, 7, 8.x
4. Knowledge of Active Directory support and management
5. Knowledge of installing and configuration of a Microsoft Exchange Server 201x, Microsoft Lync, DHCP, DNS, radius and GPO support and management
6. Good understanding of: Enterprise systems, firewall concepts, network-based storage solutions, and server hardware
7. Ability to develop architectural diagrams to illustrate infrastructure layout

Desirable:

1. Experience of supporting a 20+ mixed Operation System server environment
2. MCSE Server Infrastructure (Must give evidence of the exam certificate done by an authorised testing body, i.e. Pearson VUE, Prometric, etc.)
3. Knowledge of configuring Microsoft Hyper-V
4. Experience of working in a research establishment
5. Supporting a multi-subneted, VLAN network environment
6. Microsoft SQL server support
7. MySQL database support
8. IT Security certification
9. Knowledge in unified communication technologies 

Info source: Haramaya University


Jan 22, 2020 at 03:17 PM

Communication Officer

Informer : Haramaya University

Job Profile:

1. Place of work: Haramaya University, main campus
2. Type of employment: Contractual
3. Duration: Two years with possible extension up to five years
4. Reports to: ACE Center Leader

Job Description:

The communication officer will be responsible for publicizing, networking, and conveying activities of the ACE project.

Required Qualifications and Work Experience:

A minimum of Master’s degree in communication, agricultural information and communication management, Journalism, or other relevant disciplines with at least two-year experience in written, oral, and online communications

Preferred Specific Experiences:

1. Demonstrated ability to plan, organize and facilitate conferences, workshops, meetings, seminars, etc.
2. Experience in proper handling of university property and communication with national and international students and staff
3. A thorough knowledge of the working environment in Ethiopian universities is a plus
4. Qualified women are particularly encouraged to apply


Required Skills:

1. Extensive knowledge and conceptual understanding of the job of a communications officer, to take care of specialized technical as well as administrative functions of the job, e.g. knowledge of relevant policies and procedures to be able to determine an appropriate course of action based on these guidelines with ability to analyse, interpret and modify complicated information.
2. High level of computer skills such as website management, web publication, communication, document formatting, etc.
3. Excellent written and verbal communication skills in English.
4. Ability to work with a diverse population of faculty, staff, partners and stakeholders
Qualified women are particularly encouraged to apply.

Salary and Benefits:

USD 12000 per annumsubject to income tax deduction. Payment will be made in Ethiopian Birr based on the exchange rate at the time of transfer of the money from the donor.

Place of application:

1. Haramaya University Cluster Human Resource Management Office, College of Business and Economics Building.
2. Haramaya University College of Health and Medical Sciences, Human Resource Management and Development Associate Director Office, No.7 at Harar.
3. Haramaya University Liaison Office at Addis Ababa, Arat Kilo. Former Germany Cultural Institute Building Office No.15
Application Deadline: 8 (Eight) working days after the day of advertisement 

Info source: Haramaya University


Jan 22, 2020 at 10:21 AM

የዕለቱ የገንዘብ ምንዛሬ ተመን ጥር 13

Informer : Askwala

የዕለቱ የገንዘብ ምንዛሬ ተመን ጥር 13 / January 22, 2020 

Info source: commercial bank of Ethiopia


Jan 19, 2020 at 10:57 AM

Call for Abstracts

Informer : Jimma University

The Institute of Oromo Studies (IOS), Jimma University is organizing the Fifth International Oromo Studies Conference to be held from 26th–27th May, 2020 at Jimma University, Oromia, Ethiopia. The conference welcomes abstracts with full length paper from scholars and students around the world. 

Info source: Jimma University


Jan 19, 2020 at 09:43 AM

VACANCY ANNOUNCEMENT

Informer : Bahir Dar University

Bahir Dar University Co llege of Medicine and Health Science wants to fill the following Vacant academic Positions for 2nd Semester 2012 E.c ,Hence it invites interested and eligible applicants to apply for the academic posts announced. 

Info source: Bahir Dar University


Jan 16, 2020 at 04:58 PM

Call For Papers

Informer : Bahir Dar University

Faculty of Humanities, BDU is pleased to announce the call for papers for its Seventh Annual International Conference on Language, Culture and Communication to be held 11-12 March, 2020 (Megabit 2-3, 2012 E.C). 

Info source: Bahir Dar University


Jan 16, 2020 at 04:15 PM

Call for Abstracts

Informer : Bahir Dar University

Call for Abstracts
National Annual Conference on March 6-7, 2020
College of Agriculture and Environmental Sciences
Bahir Dar University  

Info source: Bahir Dar University


Jan 16, 2020 at 04:11 PM

Call for Abstracts

Informer : Bahir Dar University

Faculty of Social Sciences at Bahir Dar University calls for all interested intellectuals to send abstracts for the 7th National Social Science Conference to be held from 9-10 April, 2020 on the topic: Political Transition, Peace and Democracy in Contemporary Ethiopia. 

Info source: Bahir Dar University


ONLINE E-BOOKS

Online E-books, Textbooks and related materials.