Askwala More

Jan 26, 2020 at 01:09 PM

ፕሬዝዳንት ዢ ጂንጂንግ ቻይና በአዲሱ ቫይረስ አደጋ ውስጥ ገብታለች ሲሉ አስጠነቀቁ

Informer: Askwala

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ በሚገኘው እና 1,300 ሰዎችን በያዘው አዲስ ቫይረስ ሳቢያ አገራቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ አስጠነቀቁ። ከዚህ ቀደም በዚያው በቻይና ተከስቶ ከነበረው የሳርስ ቫይረስ ይመሳሰላል የተባለው አዲስ የቫይረስ ወረርሽኝ በ30 ግዛቶች ተስፋፍቷል። ከቻይና ውጪ በጃፓን፣ በደቡብ ኮሪያ እና በአሜሪካም ይኸው ቫይረስ በሰዎች ላይ ተገኝቷል። ፈረንሳይ በቫይረሱ የተያዘ ሰው በግዛቷ በማግኘት የመጀመሪያዋ የአውሮፓ አገር ሆናለች። ፈረንሳይ የቫይረሱ ሥርጭት ከበረታባት የውኻን ከተማ ዜጎቿን ለማውጣት ተዘጋጅታለች። ቫይረሱ እጅግ አደገኛ በሆነ ፍጥነት እየተስፋፋ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ቻይናን የሚመራው ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በጠንካራ አመራር መፍትሔ መሻት እንዳለበት አሳስበዋል።ውኻን የተባለችው የአስራ አንድ ሚሊዮን ሰዎች መኖሪያ ከተማን ጨምሮ ሌሎች 18 የቻይና ከተሞች የሕዝብ መጓጓዣዎችን ሙሉ በሙሉ አግደዋል። በውኻን አጠገብ ቻይና በቫይረስ የተያዙ ሕሙማንን ለማከም 10,000 አልጋዎች የሚኖሩት ሆስፒታል በ270,000 ስኩዌር ጫማ መሬት ላይ በ6 ቀናት ለመገንባት ሥራ ጀምራለች።እስካሁን 41 ሰዎችን የገደለው ቫይረስ ሥርጭትን ለመቆጣጠር ሖንግ ኮንግ በከተማዋ በርካታ ተሽከርካሪዎችን ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከልክላለች። ለሁለት ሳምንታት ትምህርት ቤቶች እንደሚዘጉም የሖንግ ኮንግ መሪ ላሪ ላም አስታውቀዋል። ሳይንቲስቶች ስለ ቫይረሱ ዛሬም በቂ መረጃ ባይኖራቸውም ከእንስሳት ወደ ሰው ሳይሸጋገር እንዳልቀረ ይነገራል። EB-LA

Info source: ዶይቼ ቬለ


ONLINE E-BOOKS

Online E-books, Textbooks and related materials.