Askwala More

Jan 29, 2020 at 09:53 AM

አዲስ አበባ በኮሮና ቫይረስ የተጠረሩ 4 ኢትዮጵያዉያን አሉ ተባለ

Informer: Askwala

በኮሮና ተሐዋሲ ሳይያዙ አልቀረም በሚል የተጠረጠሩ 4 ሰዎች አዲስ አበባ ውስጥ ከኅብረተሰብ በማይቀላቀሉበት ገለልተኛ ቦታ የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸዉ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዛሬ ዐስታወቀ። በተሐዋሲው የተጠረጠሩት አራቱም ኢትዮጵያዊያን ናቸዉ ተብሏ። ሦስቱ ኢትዮጵያዉያን ቫይረሱ በተከሰተበት ኹዋን ከተባለዉ የቻይና ግዛት የመጡ መኾናቸውም ተገልጧል። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ በኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር የሚኒስትር ጽ/ ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ሙኒር ካሳ እንደተናገሩት ኮሮና ተሐዋሲ ተስፋፍቶበታል ተብሎ ከተነገረባቸው ከተሞች ብሎም በአጠቃላይ ከቻይና የሚመጡ ተጓዦች ላይ ቦሌ ዓለም አቀፍ አዉሮፕላን ጣብያ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል። «ከመጡት መካከል ትኩሳት ያለባቸውን ከኅብረተሰቡ ጋር እንዳይቀላቀሉ አድርገን [ለብቻቸው እናቆያቸዋለን] በአኹኑ ሰአት አራት አብዛኛው ኢትዮጵያያውያን የኾኑ ተማሪዎች ከዚህ ሀገር ስለመጡ፤ ከመጡት መካከል ደግሞ ኹለቱ እንደ ጉንፋን ነገር ስላላቸው ከኅብረተሰቡ እንዳይቀላቀሉ ለይተን አስቀምጠናቸዋል። በአኹኑ ሰአት ኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ ቫይረስ ተገኘ ተብሎ የተባለው ውሸት ሙሉ ለሙሉ ውሸት ነው። የሰጠነው መግለጫም የሚያሳየው ይኼንን እንጠረጥራለን፤ ማንኛውም ትኩሳት ያለው እና ከነዚህ አካባቢ የሚመጣን ሰው ስክሪን እያደረግን ወደሀገር ውስጥ እንዳይገባ እየተከላከልን ነው።»ቀደም ሲል የአፍሪቃ ኅብረት የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል በሰጠዉ መግለጫ የኮሮና ተሐዋሲን ለመከላከል ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እየተሠራ ነዉ ብሏል።

Info source: ዶይቼ ቬለ


ONLINE E-BOOKS

Online E-books, Textbooks and related materials.