Askwala More

Jan 31, 2020 at 10:13 AM

4ቱ ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ነጻ መሆናቸው ተረጋገጠ

Informer: Askwala

በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሊሆን ይችላል በሚል ጥርጣሬ በተገለል የሕክምና ማዕከል የቆዩ አራት ኢትዮጵያውያን ከህመሙ ነፃ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ምኒስትር ድዔታ ዶ/ር ሊያ ከበደ አስታወቁ። ምኒስትሯ ደቡብ አፍሪካ በተደረገ ምርመራ አራቱ ተማሪዎች ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል ብለዋል።በቫይረሱ ተይዘዋል ተብለው ከተጠረጠሩት አራቱ ተማሪዎች ሦስቱ ቫይረሱ ከተከሰተበት ኹዋን ከተባለዉ የቻይና ግዛት የመጡ ነበሩ።የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው እንደሌለ አስታውቋል።በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግሥት ቻይና የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር የተያያዘ የጤና ችግር አልደረሰባቸውም ሲል አስታወቀ።በቻይና ቻንቺግ ግዛት በሚገኘው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ተጠባባቂ ቆንስል ጀነራል አቶ አንተነህ ታሪኩ ተማሪዎቹ በሙሉ በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።አቶ አንተነህ እንዳሉት አስፈላጊ ከሆነ መንግሥት ዜጎችን ለማውጣት ዝግጁ ነው።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ወደ ቻይና የሚያደርገውን መደበኛ በረራ ሙሉ በሙሉ አቋርጧል።ሮይተር ዜና አገልግሎት የአየር መንገዱን የመንገደኞች የስልክ ጥሪ ማዕከልን ጠቅሶ እንደዘገበው ወደ ቻይና የሚደረጉ በረራዎች በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ ተቋርጠዋል የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ግን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

Info source: ዶይቼ ቬለ


ONLINE E-BOOKS

Online E-books, Textbooks and related materials.