Askwala More

Feb 04, 2020 at 10:04 AM

ጄኔቫ የዓለም ጤና ድርጅት ጥሪ

Informer: Askwala

የኮሮና ተህዋሲ ሥርጭትን ለመከላከል በዓለም አቀፍ ጉዞ እና ንግድ ውስጥ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት የሚያደርጉ እርምጃዎችን መውሰድ እንደማያስፈልግ የዓለም ጤና ድርጅት ሃላፊ አሳሰቡ።ሃላፊው ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሃገራት ከኮሮና ተህዋሲ ጋር በተያያዘ የሚወስዷቸው እርምጃዎች በመረጃ ላይ የተመሰረተ እና የማይዋዥቅ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።የዓለም የጤና ድርጅት ኮሮናን ዓለም አቀፍ የጤና ስጋት ሲል ባለፈው ሐሙስ ነበር ያወጀው። በኮሮና ተህዋሲ ሰበብ የተደረጉ የበረራ ገደቦች እና ከቻይና በሚመጡ መንገደኞች ላይ የተጣለው እገዳ በቻይና ላይ ዓለም አቀፍ መገለል አስከትሏል።ቻይና ውስጥ በተህዋሲው የሞቱት ሰዎች ቁጥር 361 ደርሷል።በተህዋሲው መያዛቸው የተረጋገጠው ደግሞ 17238 ናቸው።በ23 ሃገራት ደግሞ 151 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተነግሯል። በተህዋሲው የተያዘች አንዲት ሴት ፊሊፒንስ ውስጥ ሞታለች።

Info source: ዶይቼ ቬለ


ONLINE E-BOOKS

Online E-books, Textbooks and related materials.