Askwala More

Feb 06, 2020 at 09:59 AM

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በፍጥነት እየተዛመተ ነው ተባለ

Informer: Askwala

የኮሮና ቫይረስ ከተገመተዉ በላይ በፍጥነት እየተዛመተ መሆኑን የጤና ባለሙያዎችና የሐገራት ባለስልጣናት አስታወቁ።የጤና ባለሙያዎች እንደሚሉት የተለያዩ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸዉን ሳያዉቁ ከሌሎች ሰዎች ጋር በመገናኘታቸዉ በገዳዩ ቫይረስ የተለከፈዉ ሰዉ ቁጥር እየናረ ነዉ።ይሁንና በቫይረሱ እስካሁን ሰዎች የገደለዉ ዋናዋ ቻይና፣ የቻይና ልዩ ግዛት በሆነችዉ ሆንግ ኮንግ እና ፊሊፒንስ ዉስጥ ነዉ።እስከ ዛሬ ድረስ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 492 ደርሷል። በቫይረሱ የተለከፈዉ ሰዉ ቁጥር ደግሞ 24,500 ነዉ።አብዛኛዉ ሰዉ የቻይና ዜጋ ወይም ቻይና ዉስጥ የሚኖር ሲሆን ጃፓን ዉስጥ 35፣ ሲንጋፑር 28 እና ታይላድ ዉስጥ 25 ሰዉ በቫይረሱ በመለከፍ ከቻይና ቀጥሎ ከአንድ እስከ ሶስት ያለዉን ስፍራ ይይዛሉ።ባጠቃላይ በ26 ሐገራት በተሕዋሲዉ የተጠቁ ሰዎች መኖራቸዉ ተረጋግጧል።

Info source: ዶይቼ ቬለ


ONLINE E-BOOKS

Online E-books, Textbooks and related materials.