AskwalaToday is Jummah. Happy Jummah, Happy friday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!


                                     

Welcome to askwala!


Inform          Today is Friday, October 02, 2020

የ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ እጣ ወጣ

Informed 7 hours ago

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ ሎተሪ እጣ ዛሬ በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ይፋ ሆነ። የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ8100 A አጭር የጽሁፍ መልእክት 2ኛ ዙር የሎተሪ እጣ አወጣጥ ሥነ-ስርዓት በብሄራዊ ሎተሪ አዳራሽ ተካሂዷል።
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ህብረተሰቡ ግድቡን እንዲደግፍ በ8100 A አጭር የጽሁፍ መልዕክት ማዘጋጀቱ ይታወቃል።
የግድቡን የመጀመሪያ የውሃ ሙሌት አስመልክቶ በ8100 A ለተሳታፊዎች የተዘጋጀው የሎተሪ እጣ አሸናፊም ዛሬ ተለይቷል።
በዚህም መሰረት የአሸናፊው እጣ ቁጥር 14 89 08 078 ሆኖ ወጥቷል፤ የእድለኛው የሞባይል ቁጥር ደግሞ 0930****71 ሆኗል።
የአስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤቱ አባል ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን ሁሴን እንዳሉት፤ ባለፉት ስድስት ወራት ብቻ በ8100 A የገቢ ማሰባሰቢያ ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል።
ባለፉት ስድስት ወራት በ8100 A የገቢ ማሰባቢያ 20 ሚሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም ከ52 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተገልጿል።
ህብረተሰቡ ወደፊትም በ8100 A አጭር የጽሁፍ መልእክት በመላክ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስበዋል።  


Grab 10% off and travel with ease

Informed 11 hours ago

Informer:  Ethiopian Airlines
Grab your 10% and Upgrade your travel experience using the Ethiopian Mobile App.

Our App offers seamless booking in multiple languages, passport and credit card scanner, mobile boarding pass on Google Wallet and Apple's Pass Book as well as 44 payment options including international and local cards, wallets, mobile money, bank transfer and much more.

Enjoy seamless and convenient airport experience using your mobile boarding pass which also saves you time by avoiding queues.

Once again, thank you for choosing Ethiopian.
Have a pleasant journey!  


Informed 13 hours ago

የማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄ እና ምርመራ ዘመቻ፣ ባሳለፍነው ነሀሴ ወር 2012 ዓ.ም መካሄዱ ይታወቃል፡፡ የዚሁ ዘመቻ አካል በሆነው ”ማስከ ኢትዮጵያ” ንቅናቄ የጤና ሚኒስቴር ባዘጋጀው፣ የማህበረሰቡን የማስክ አጠቃቀም ግንዛቤ የሚያሳድጉ የቪዲዮ፣ የፎቶግራፍ እና የሬዲዮ ማስታወቂያ ውድድር ላይ ከ 170 በላይ ተወዳዳሪዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡ ከየምድቡ ያለፉት ተወዳዳሪዎች ተለይተው የታወቁ ሲሆን እነዚህን ተወዳዳሪዎች ለሁለተኛ ዙር በማወዳደር እውቅና ይሰጣል፡፡ የእውቅና መስጫ ቀን በቅርብ የምናሳውቅ ሲሆን በውድድሩም ሆነ በዳኝነቱ የተሳተፋችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን፡፡  


የመግቢያ ፈተና ጊዜ ማስታወቂያ (በድጋሚ የወጣ)

Informed yesterday at 05:50 PM

ለድህረ ምረቃ አዲስ አመልካቾች በሙሉ
የአርባ
ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ለ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን እየመዘገባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ትናንት በወጣው የፈተና ጊዜ ማስታወቂያ በ25/01/13 ዓ/ም ሊሰጥ የነበረው የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና በአመልካቾች ጥያቄ መሠረት ለ30/01/13 ዓ/ም የተዛወረ መሆኑን እየገለፅን ተፈታኞች በተጠቀሰው ቀን ከጥዋቱ 02፡30 ጀምሮ በየተመደባችሁበት የመፈተኛ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት  


የፈተና ጥሪ

Informed 2 days ago

To: Technical Assistant I position applicants at Washera Geo-space and Radar Science Research Lab.
Your written examination is scheduled on October 5, 2020 (Meskerem 25/2013E.C).  


አዲስ ማስታወቂያ ለነባር ሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች በሙሉ !

Informed 2 days ago

Informer:  Wachemo University
አዲስ ማስታወቂያ ለነባር ሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች በሙሉ !
Wachemo
University  


የመግቢያ ፈተና ጊዜ ማስታወቂያ

Informed 2 days ago

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት ለ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን እየመዘገባ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ የምዝገባ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ባሳወቅነው ማስታወቂያ የመግቢያ ፈተና ጊዜ ወደ ፊት እንደሚገለፅ የተነገረ ሲሆን በዚሁ መሠረት ለሁሉም አመልካቾች የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው በድህረ ምረቃ
ት/ቤት ሕንፃ መስከረም 25/2013 ዓ/ም ከሰዓት ከ08፡00 ጀምሮ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ድህረ ምረቃ ት/ቤት
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት  


የተሻሻለ ማስታወቂያ

Informed 2 days ago

Informer:  Mettu University
መቱ ዩኒቨርስቲ ከዚህ በፊት አዲስ ለድህረ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከመስከረም 4-18 አውጥቶ የነበረውን በተመዝጋቢዎች ተደጋጋሚ ጥያቄ መሠረት ምዝገባውን እስከ መስከረም 22/2013 ዓ.ም ያራዘመው መሆኑን ይገልፃል።
መቱ ዩኒቨርስቲ  


ሀገር አቀፍ የሐኪሞች ስፔሻሊቲ ስልጠና ማስታወቂያ

Informed 3 days ago

በህክምና የዶክትሬት ዲግሪ ላላችሁና የስፔሻሊቲ ስልጠና መውሰድ ለምትፈልጉ በሙሉ፡-
የጤና
ሚኒስቴር ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን፤ በ22 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች አመልካቾችን በብሄራዊ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቋል፡፡
በመሆኑም ፍላጎት ባላችሁ እስከ ሶስት የስፔሻሊቲ ትምህርት ዘርፎች ላይ በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ ላይ (www.moh.gov.et) መመዝገብና መወዳደር እንደምትችሉ አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን የምዝገባ ጊዜውም ከመስከረም 21 እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑን እያሳወቅን የፈተና ጊዜና ቦታ እንዲሁም ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በተመለከተ ከላይ በተጠቀሰው ድረ-ገፅ ላይ ወደፊት የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ከባለፉት ዓመታት በተለየ በዚህ ዓመት የስፖንሰርሽፕና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ አዳዲስ ለውጦችና መስፈርቶች ስለተካተቱ ምዝገባውን ከመጀራችሁ በፊት ዝርዝር መረጃዎችን ከERMP መመሪያ እና Instruction For Registration ላይ እንድትመለከቱ እናሳስባለን፡፡
የጤና ሚኒስቴር እና የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር !!!  


Informed 3 days ago

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቦርድ አመራር አባል የሆኑት ዶክተር ጌታሁን ካሳ በዛሬው እለት በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ለኢፌዲሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስገባታቸውን እናሳውቃለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  


የመስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ ዘመን ጋዜጣ በፒዲኤፍ

Informed 3 days ago

እንደምን አደሩ!
አዲስ
ዘመን ዛሬ!
የመስከረም
19 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይዘቶችን በሙሉ በፒዲኤፍ እነሆ!
መልካም ቀን!  


ነገ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ በአንዳንድ አካባቢዎች ኃይል ይቋረጣል

Informed 3 days ago

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ፡-
በመሳለምያ፣ በእሳት አደጋ፣ በሳንባ ነቀርሳ፣ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ በታይዋን፣ በሆላንድ ኤምባሲ እና አካባቢዎቻቸው፤
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በሃና ማርያም፣ በሃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንዶሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በሳሪስ አቦ ቤተ-ክርስትያን፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ በክሬሸር እና አካባቢዎቻቸው፤
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡  


ማስታወቂያ, ለድህረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Informed 3 days ago

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በ2013 የትምህርት ዘመን በድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች በመደበኛ (Regular) መርሃ ግብር በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም በመደበኛ (Regular) መርሃ ግብር በሦስተኛ ዲግሪ አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተከታታይ ትምህርት ተsም ለ2013 ዓ.ም በሁለተኛ ዲግሪ በቅዳሜና እሁድ (Weekend) መርሀ ግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡  


ነገ መስከረም 19 ቀን 2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች

Informed 3 days ago

ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ፡-
በመሳለምያ፣ በእሳት አደጋ፣ በሳንባ ነቀርሳ፣ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ በታይዋን፣ በሆላንድ ኤምባሲ እና አካባቢዎቻቸው፤
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ፡-
• በሃና ማርያም፣ በሃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንዶሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በሳሪስ አቦ ቤተ-ክርስትያን፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንዶሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ፣ በክሬሸር እና አካባቢዎቻቸው
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ደንበኞች ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ ሲል ድርጅቱ አሳስቧል፡፡  


በድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ ለ2013 ዓ.ም የድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች የምዝገባ ጊዜ መራዘሙን ስለማሳወቅ

Informed 4 days ago

ለድህረ-ምረቃ ተማሪዎች የመጨረሻ የማማልከቻ ቀን መስከረም 17, 2013 ዓ.ም መሆኑን ያሳወቅን ቢሆንም ኢንተርኔት ማግኘት ላልቻሉ ተማሪዎች ሲባል የማመልከቻ ጊዜ እስከ መስከረም 24, 2013 ዓ.ም ድረስ የተራዘመ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ አመልካቾች ከዚህ በፊት በገለፅነው መሰረት ትምህርት ፈላጊዎች በዩኒቨርስቲው ድህረ-ገጽ http://portal.uog.edu.et/graduateApplication ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ለመመዝገብ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፤ የምዝገባ ሂደት መግለጫ እና የትምህርት አይነቶች ከላይ በተጠቀሰው መግቢያ (link) በመግባት መመልከት ይቻላል፡፡
የመመዝገቢያ ቀን፡ እስከ መስከረም 24, 2013 ዓ.ም
የማመልከቻ ክፍያ ባንክ አካውንት ቁጥር(CBE): 1000018782492
ማሳሰቢያ፡- በኢንተርኔት እጦት ምክንያት ለመመዝገብ እገዛ ለሚፈልጉ አመልካቾች በየኮሌጁ ያሉ የኮሚውተር ላቦራተሪዎች ክፍት ሆነው እገዛ እንዲያገኙ ተመቻችቷል፡፡  


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ አስር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መመደቡ ተገለጸ

Informed 4 days ago

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ አስር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መመደቡን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገለጹ፡፡ በህትመት ስኬታማነት በአፍሪካ ካሉ ሶስት ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ መሆኑም ተጠቆመ፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባደረጋቸው ችግር ፈቺ የምርምር ተግባራት በዓለም አቀፍ የዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ መዳቢ አካላት በአፍሪካ ከሚገኙ ምርጥ አስር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ መመደቡን ገልጸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለዚህ የበቃው በምርምር ውጤቶችና በዩኒቨርሲቲው የሚታተሙ ህትመቶች ለሌሎች ተመራማሪዎች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ባላቸው የችግር ፈቺነት አቅም መሆኑን አመልክተዋል።  


Announcement about Graduate Admission Test (GAT)

Informed 4 days ago

The Graduate Admission Test (GAT) is composed of three sections: Verbal Reasoning, (60
questions), Quantitative Reasoning (40 questions) and Analytical Reasoning (25 questions).
Each of these tests lasts for one hour and you will need to stay working on the actual exams
for three hours. Students with Visual impairment will work only the Verbal Reasoning Section. Before starting your actual exam you are required to fill out a brief survey questionnaire. The system will not let you take the exam unless you complete the survey.  


የፓስፖርት እድሳት በኦንላይን አገልግሎት መስጠት ሊጀመር መሆኑ ተገለፀ፡፡

Informed 5 days ago

Informer:  Ministry of Peace
የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል ከሸገር ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት ሰዎች ለረጅም ጊዜ ቅሬታ ያቀርቡበት የነበረውን የፓስፖርት እድሳት ጉዳይ አስመልክቶ መፍትሄ መበጀቱን ገልፀዋል፡፡
ይህም የአገልግሎቱን ተደራሽነት የሚያሰፋ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን ሰዎች ባሉበት ሆነው ዶክመንታቸውን በኢንተርኔት የሚልኩበትና ክፍያውን በባንክ ከፈፀመ በኋላ በአቅራቢያው ባለው ፖስታ አገለግሎት ፓስፖርቱ እንዲደርሳቸው የሚያደርግ አሰራር እያዘጋጀን ሲሆን ይህም ሲስተም 90 በመቶ ዝግጅቱ ተጠናቋል ብለዋል፡፡
በተለይም በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የፓስፖርት እድሳትና የትውልድ መታወቂያ ካርድ አሰጣጥ ፈጣንና የዘመነ እንዲሆን መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡ ይህም ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ተገልጋዮች በግንባር ሳይመጡ ፤ሶስት ወርም ሳይጠብቁ በ12 ቀናት ብቻ ፓስፖርታቸውን መሳደስ የሚችሉበት ሲስተም መዘርጋቱንና አሁንም ይህ አገልግሎት በአሜሪካ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መሰጠት ከጀመረ ሶስት ሳምንት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡  


ለ2013 ዓ.ም አዲስ ገቢ የማስተርስ መደበኛ ተማሪዎች

Informed 5 days ago

በፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዪት የ2ኛ ዲግሪ መደበኛ መርሐ-ግብር ለመማር ከክልሎችና ከከተማ መስተዳድሮች ተመልምላችሁ የመግቢያ ፈተና ለምትጠባበቁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የ2013 የትምህርት ዘመን የመግቢያ ፈተና የሚሠጠው መስከረም 25/2013 ከቀኑ 8:00 በመሆኑ በተጠቀሰው ቀንና ሠአት እንድትገኙ እያሳሰብን ፈተናው የሚሰጠው አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው ጊቢ መሆኑን እናሳስባለን።
ለበለጠ መረጃ፦ በ0937 118124 ይደውሉ
አድራሻ: አዲስ አበባ ከላምበረት መነሐሪያ ወደወሠን በሚወስደው መንገድ 200ሜትር አለፍ ብሎ
ፈደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት  


የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥረት ኤጀንሲ በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ በበይነ መረብ መስመር ትምህርት የዕውቅና ፈቃድ አሰጣጥ መገምገሚያ ቅጽ

Informed 5 days ago

የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥረት ኤጀንሲ በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ በበይነ መረብ መስመር ትምህርት የዕውቅና ፈቃድ አሰጣጥ መገምገሚያ ቅጽ (Undergraduate Online Learning Accreditation checklist-2020( HERQA, Ethiopia)  


ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ለ7ኛ ግዜ 1732 ተማሪዎችን ኣስመርቃል!

Informed 5 days ago

Informer:  Adigrat University
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ 75 የሕክምና ዶክተሮች ጨምሮ 1732 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት ኣስመርቃል:: የምርቃት ስነስርዓቱ በትግራይ ቴለቭዥን በቀጥታ ስርጭታ የተላለፈ ሲሆን ዶ/ር ሓጎስ ጎዲፋይ, የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሓላፊ በክብር እንግድነት ተገኝተዋል::
ዩኒቨርስቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው ተማሪዎች የሕክምና ተማሪዎች ጨምሮ በማታ በክርመትና በድህረ መረቃ ኣስመርቃል::
ውድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን እንካን ደስ ኣላችሁ!  


የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች የቅድመ-ማጣርያ በማለፍ በአፍሪካ የምስለ-ችሎት ውድድር እየተሳተፉ ነው

Informed 5 days ago

Informer:  Aksum University
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ክፍል ቡድን የአፍሪካ ሰብአዊ መብቶች በሚያዘጋጀው የምስለ ችሎት ውድድር ለመጀመርያ ጊዜ እየተሳተፉ ይገኛል።
ኢትዮጵያን ወክሎ እየተወዳደረ የሚገኘው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤትን ጨምሮ 29 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች የቅድመ-ማጣርያውን አልፈው ቀጣዩ ዙር የኦንላይን የችሎት ውድድር ጀምረዋል።
የአራተኛ አመት ተማሪዎች ዲያና ፅጋቡ፣ ማህደር አሰፋና አማካሪያቸው መምህር ደረጀ ነጋሽን ያካተተው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ቡድን በመጀመርያው የኦንላይን የችሎት ውድድር የከሳሽ ሚና በመወከል መስከረም 21 2020 ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ (UNISA) ቡድን ጋር ተወዳድረዋል።
ሁለተኛው ዙር የኦንላይን የችሎት ውድድር የዩኒቨርሲቲው ቡድን ተከሳሽን በመወከል መስከረም 23 2020 ከኡጋንዳው ማከረሬ ዩኒቨርሲቲ ጋር ተፋልመዋል።
በውድድሩ እየተሳተፈች ያለችው ተማሪ ማህደር አሰፋ “የምስለ-ችሎት ውድድሩ አለማቀፍ ተሞክሮዎችን በማግኘት የተሻለ አቅም እንድገነባ ረድቶናል” ብላለች።
ተማሪ ዲያና ፅጋቡ በበኩልዋ “በውድድሩ ከበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተፎካክረን የቅድመ ማጣሪያዎችን አልፈን አሁን እያካሄድን ላለነው ዙር መድረሳችን የትምህርት ሂደቱ በጥሩ ደረጃ ላይ እንዳለ ማሳያ ነው” ስትል ገልፃለች።
ተማሪዎቹ በቀጣይም በተሻለ መልኩ በተግባር የታገዘ ትምህርት ለማግኘት ከትምህርት ክፍል ጀምሮ እስከ አገራዊ የህግ ትምህርት ቤቶች የምስለ-ችሎት ውድድሮች በስፋት ሊኖር ይገባል ብለዋል።
መምህር ደረጀ ነጋሽ በበኩላቸው ውድድሩ በህግ ትምህርት አለማቀፍ ልምድ ያገኙበት መሆኑን ገልፀው በተግባር ትምህርት ላይ ማትኮር እንደሚያስፈልግም አስምረውበታል።
የዚህ ለ29ነኛ ጊዜ የሚደረገው የአፍሪካ ሰብአዊ መብቶች የምስለ-ችሎት ውድድር የመጨረሻ ዙር ከ16 እስከ 19 ታሕሳስ በዩኒቨርሲተ ቨርቹዋለ ደ ሴኔጋል (UVS) እና ዩኒቨርሲተ ቼክ አንታ ደዮፕ (Cheikh Anta Diop de Dakar (UCAD) አዘጋጅነት በሴኔጋል መዲና ዳካር ይካሄዳል፡፡
የአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ቡድንም አሁን የተወዳደረበት ዙር ካለፈ ሴኔጋል በሚካሄደው ስድስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሳተፉት የመጨረሻው ውድድር ይሳተፋል።
ይህ ውድድር በአንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛና ፖርቱጌስ ቋንቋዎች በየአመቱ የሚዘጋጅ የምስለ-ችሎት ውድድር ነው፡፡  


Space Apps 2020

Informed 5 days ago

We are pleased to invite you to the 3rd NASA Space Apps Challenge Addis Ababa, scheduled for October 2 - 4, 2020 with R-Ladies Addis Ababa and Space Generation Advisory Council (SGAC).
Form your team and register for the online Hackathon, at https://2020.spaceappschallenge.org/locations/addis-ababa. For Further inquiries, spaceappschallenge.addis@gmail.com  


Youth Space Ambassador Application

Informed 2 weeks ago

ESSS Youth Ambassador Registration deadline is extended till September 25

Ethiopian
Space Science Society (ESSS) has various public engagement programs. Included in that is the youth space ambassador program, which recognizes youth involvement in space science development in the community such as school and media. The program is run every year since 2018 and it was responsible for selecting, assessing, and awarding 5 active ESSS youth members.  


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለ የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ለማዘመን ያለመ የክዋኔ መርሃግብር ይፋ ተደረገ፡፡

Informed 2 weeks ago

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን የመረጃ አያያዝ ስርዓት ለማዘመን ያለመ እና ከመስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ የክዋኔ መርሃግብር ከ500 በላይ የዩኒቨርስቲዎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቨርቹዋል በተሳተፉበት ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡
በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ ዶ/ር ሙሉ ነጋ እና ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
መረጃ ህይወት ነው፡፡ ትክክለኛ መረጃ የብዙዎችን ሕይወት የመቀየር አቅም አለው፡፡ የእያንዳንዱ ኩነት መረጃዎች በአግባቡ ተሰንዶ ሲያዝ ስለኩነቱ መረጃ ለመስጠትም ሆነ ከዚያ ኩነት ለመማር የራሳቸው አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡  


ለአዲስ የ2ኛ ዲግሪ የተከታታይ (Extension Program) ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፣

Informed 3 weeks ago

ለአዲስ የ2ኛ ዲግሪ የተከታታይ (Extension Program) ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ፣

የደብረ
ማርቆስ ዩኒቨርስቲ በ2013 ዓ/ም 1ኛው ሴሚሰተር በተከታታይ (Extension Program) አዲስ የግል አመልካቾችን ተቀብሎ በሁለተኛ ዲግሪ ማስተማር ይፈልጋል፡፡  


ማስታወቂያ: ለመላው የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ማህበረሰብ

Informed 3 weeks ago

በኮቪድ 19 ወረርሸኝ ምክንያት የገጽ ለገጽ ትምህርት መቋረጡና ለበለጠ ጥንቃቄ ሲባል ተማሪዎች በልዩ ዝግጅት ወደቤተሰቦቻቸው መሸኛታቸው ይታወሳል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተቋረጠውን ትምህርት ለማስቀጠል የሚያስችሉ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ መሆኑን ቀደም ብለን መግለጻችንም ይታወቃል።
ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርስቲዎች የሚከፈቱበት ቀን እንደተቆረጠ ሆኖ በተለያዩ አካላት የሚወጣው መረጃ የተሳሳተ እንደሆነና የተቋረጠው ትምህርት ሊቀጥል የሚችለው ከሚመለከተው የመንግስት አካል ትምህርት ማስቀጠል የሚያስችል መረጃ ሲገኝ ብቻ እንደሆነ እና መረጃውም የሚሰጠው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በኩል ብቻ መሆኑን እያሳወቅን እስከዛው ድረስ የቫይረሱን ስርጭት ለመከለካል የሚያስችል አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ እያደረጋችሁ ከክፍያ ነጻ በሆነው የዲጂታል ላይበራሪያችን በመግባት አጋዥ መጻህፍትን እያነበባችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።  


New Online Submission of Your Final Theses and Dissertation for Defence

Informed 3 weeks ago

To: All Masters’ and PhD Candidates Who Are Ready to Submit Your Research Work

From: Postgraduate Programs Directorate, Haramaya University

Subject: New Online Submission of Your Final Theses and Dissertation for Defence

This is to inform you that New Online Submission of your Finalized Theses and Dissertations for the Next Session Defence will start on August 31 and will end on September 14, 2020.  


DISTANCE EDUCATION OPPORTUNITIES

Informed 3 weeks ago

Informer:  Jimma University
Jimma University, Continuing and Distance Education Directorate Office is pleased to announce commencement of registering new applicants for the upcoming academic year of 2020/21 (2013 E.C) with its well established and accredited DISTANCE EDUCATION PROGRAMS:

1. B.A Degree in Accounting and Finance
2. B.Sc. Degree in Economics
3. B.A Degree in Management
4. B.A Degree in Sociology
5. B.A Degree in Social Work
6. B.A Degree in Governance and Development Studies, and
7. B.Sc. Degree in Agricultural Economics

Registration Time: September 12/2020 to October 25/2020
Registration Place: Center coordinating offices at Jimma, Nekemte, Metu, Wolkite, Mizan and Addis Ababa
Admission Criteria: Higher Learning admission criteria set by Ministry of Education
For more information: Please call on 0471116654, 0471112181  


COVID-19 Computer-Readable Observational Data Installed at AAU

Informed 3 weeks ago

Addis Ababa University college of Health Science /School of Public Health/CBM project install COVID-19 Computer-Readable FAIR Data point on Tuesday, 18th August 2020 https://fdp.aau.edu.et/. The installation was carried out by the Virus Outbreak Data Network (VODAN-Africa) Ethiopian team member, School of Public Health and ICT Directorate of Addis Ababa University.  


ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.