AskwalaToday is Jummah. Happy Jummah, Happy friday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!


                                     

Welcome to askwala!


Inform          Today is Friday, October 02, 2020

አሜሪካ በምርጫ ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል ጠንከር ያለ ህግ አወጣች

Informed yesterday at 12:51 PM

በአሜሪካ በድምጽ አሰጣጥ ስርዓት ላይ የሚፈጸምን የመረጃ ጠለፋ ለመከላከል በወንጀሉ ተሰማርተዉ የተገኙ አካላትን በፌዴራል ወንጀል ደረጃ ለመዳኘት የሚያስችል የህግ ማእቀፍ ጸድቋል፡፡
ባለፉት ጥቂት አመታት በአዳጊ ሆነ ጠንካራ የዴሞክራሲ ስርዓት ባላቸዉ ሃገራት ውስጥ በምርጫ ስርዓት እና በዴሞክራሲ መገንቢያ ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መጥተዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ኢስቶኒያ፣ ጆርጂያ እና ዩክሬን በመሳሰሉ ሃገራት ባለፉት 10 እና ከዚያ በላይ ዓመታት በምርጫ ስርዓታቸዉ ላይ የሳይበር ደህንነት አደጋዎች እንዳጋጠማቸዉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዴሞክራሲና ምርጫ ጉዳዮች ላይ ድጋፍ የሚያደርገዉ አይዲያ #IDEA በ2019 ሪፖርቱ ጠቁሟል፡፡
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2016 በተካሄደዉ የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በከፍተኛ ደረጃ የመከራከሪያ እርስ የነበረዉ በምርጫዉ ላይ ተከስቷል የተባለዉ የሳይበር ጥቃት ነበር፡፡
ይህን ተከትሎም የአሜሪካ መንግስት በምርጫ ስርዓቶች ላይ የሚፈጸሙ የመረጃ ጥቃቶችን ለመከላከል "የተቀናጀ ምርጫ ሥርዓት ደህንነት ህግ" ባለፈው ዓመት በአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ይሁንታን ካገኘ በኋላ ባሳለፍነው ሳምንት በሴኔቱ በሙሉ ድምፅ መጽደቁ የኢንፎሴክ ማጋዚን መረጃ ያመለክታል፡፡  


የዓለም ጤና ድርጅት ተፈጸመ የተባለውን ወሲባዊ ጥቃት እመረምራለሁ አለ

Informed yesterday at 12:40 PM

Informer:  BBC News Amharic
የዓለም ጤና ድርጅት በዲሞክራቲክ ሪፓብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝነን ለመቆጣጠር የተሰማሩ የእርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ሴቶች ላይ ወሲባዊ ጥቃት አድርሰዋል መባሉን እንደሚያጣራ አስታወቀ።  


የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ1954 ቱን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ-ስርዓት እንዲተካ የተዘጋጀውን የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት እና የማስረጃ ህግ ረቂቅ አዋጅ እንዲሁም የግልግል ዳኝነትን እና የእርቅ አሰራር ስነ-ስርዓት ረቂቅ አዋጅን አጸደቀ፡፡

Informed 5 days ago

ከ59 ዓመታት በፊት ወጥቶ አሁንም ድረስ በስራ ላይ ያለውን የወንጀለኛ መቅጫ ህግ ስነ-ስርዓት በሌላ ህግ ለመተካት ለረጅም ጊዜያት ጥረት ሲደረግ የቆየ ሲሆን በረቂቅ ህጉ ላይ አያሌ ምክክሮች ሲደረጉ ቆይቶ መስከረም 16 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀርቦ ሊጸድቅ ችሏል፡፡
በምክር ቤቱ የጸደቀውን ረቂቅ ስነ-ስርዓት ህግ አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሃን ማብራርያ የሰጡት በኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የህግ ጥናት፣ ማርቀቅ እና ማጠቃለል ዳይሬክተር ጄኔራል የሆኑት አቶ በላይሁን ይርጋ ረቂቅ ህጉ 10 ክፍሎች እና 444 አንቀጾች ያሉት መሆኑን ገልጸው በ1954ቱ ስነ-ስርዓት ህግ ውስጥ ያልነበሩ አዳዲስ ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በተለይም ሀገሪቱ ከዚህ ቀደም እራሱን የቻለ ወጥ የማስረጃ ህግ ያልነበራት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የወንጀል ማስረጃን በተመለከተ የተሟላ የህግ ማዕቀፍ እንዲቀረጽ የተደረገ መሆኑን ሲያስረዱ የዚህ ህግ ጸድቆ ወደ ተግባር መግባት የማስረጃ አይነቶችን፣ የአሰባሰብ ስርዓታቸውን እና በፍርድ ቤት ስለሚቀርቡበት ሁኔታ ዝርዝር ድንጋጌ መያዙ የወንጀል ፍትህ ስርዓቱን ቀልጣፋ እና ውጤታማ ለማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡  


የአማራ ክልል መንግሥት ለ815 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ

Informed 5 days ago

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ በክልሉ ይቅርታ አሰጣጥ መሠረት በክልሉ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ 815 የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ ማድረጉን አስታውቋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለምሸት ምሕረቴ እንደገለፁት የክልሉ የይቅርታ ቦርድ የይቅርታ መስፈርቱን ያሟሉ ታራሚዎች ወደ ኅብረተሰቡ ተቀላቅለው የበደሉትን ሕዝብ በልማትና በአገር ግንባታ ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት እንዲክሱ በይቅርታ እንዲፈቱ ወስኗል።
በክልሉ ማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ይቅርታ የሚያሰጡ የእስራት መስፈርቶችን ያሟሉ በአጠቃላይ 801 ወንድ እና 14 ሴት በድምሩ 815 ታራሚዎች ናቸው የይቅርታው ተጠቃሚ እንዲሆኑ መወሰኑን አብመድ ዘግቧል።  


የገንዘብ ይመለስልኝ ክርክር

Informed 3 weeks ago

አመልካች፡- ሴፍሜት አግሪ ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር

አቶ
ወንድምአንተነህ መሸሻ ጠበቃ ውቤ አለነ ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ብረቱ ሱኬሱ ጠበቃ ወንድአወክ አየለ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል፡፡

ጉዳዩ የገንዘብ ይመለስልኝ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የጀመረው የአሁኗ ተጠሪ የአሁኑ አመልካቾችን እንደቅደምተከተላቸው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች፣ ወ/ሮ ትግስት ድረስ የተባሉትን ግለሰብ ደግሞ 3ኛ ተከሳሽ በማድረግ መጋቢት 27 ቀን 2003 ዓ/ም በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው፡፡  


ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.