AskwalaToday is Jummah. Happy Jummah, Happy friday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!


                                     

Welcome to askwala!


Inform          Today is Friday, October 02, 2020

ትራምፕ በክርክር መሃል ጣልቃ እንዳይገቡ ማይክራፎን ሊዘጋባቸው ይሆን?

Informed 7 hours ago

Informer:  BBC News Amharic
ትራምፕ ባይደንን የክፍልህ ሰነፉ ተማሪ ነበርክ፣ አሳፋሪ ነህ ሲሉ፤ ባይደን በበኩላቸው አሜሪካ እንዳንተ የከንቱ ከንቱ መሪ አይታ አታውቅም ሲሉ መልሰዋል።
ባይደን ትራምፕን ‹ቀጣፊ› ብለዋቸዋል። ወደ ካሜራው በቀጥታ በመዞርም ‹ይህ ሰውዬ የሚላችሁን ታምኑታላችሁን?› ሲሉ የአሜሪካን ሕዝብ ጠይቀዋል።
በዚህ ክርክራቸው ትራምፕ ባይደንን 73 ጊዜ አቋርጠዋቸዋል። ትራምፕ ለ38 ደቂቃ የተናገሩ ሲሆን ባይደን ደግሞ 43 ደቂቃ ተጠቅመዋል። ከዚህ ውስጥ 20 ደቂቃ ወስደው የተነጋገሩት በኮቪድ-19 ጉዳይ ነው።
የመጀመሪያው ፕሬዚደንታዊ ክርክርም በአሜሪካም ሆነ በመላው ዓለም ትችት ዘንቦበታል።  


ፖሊስ እራሱን ለህዝብና ለሀገር አሳልፎ እየሰጠ ያለ ኃይል ነው-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

Informed 2 days ago

Informer:  Ministry of Peace
ፖሊስ ሁልጊዜም ቢሆን እራሱን ለህዝብና ለሀገር አሳልፎ የሰጠ ለባንዲራውና ለሀገሩ ክብር ከፍተኛ መስዋዕትነት አየከፈለ ያለ ኃይል መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
የፌደራል ፖሊስ "ከራስ በላይ ለህዝብና ሀገር" ክብር በዓል ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ፖሊስ ለኢትዮጵያ ሰላምና ለህዝቦቿ ኩራት መሆኑን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡
ፖሊስ ሁልጊዜም ቢሆን ራሱን ለህዝብና ለሀገር የሰጠ ለሰንደቅ አለማውና ለሀገሩ ክብር ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ያለ ኃይል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
የፖሊስ ሰራዊት ዝናብ፣ ፀሃይም ሆነ ሀዘን ሳይበግረው የተሰጠውን ግዳጅ አንደሚወጣ የዛሬው ትርዒት ማሳያ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል፡፡
ወደፊትም የሚያኮራ ሰራዊት እንዲሆን የተጀመረውን የለውጥ ስራ አጠናክሮ መቀጠል ይገባልም ነው ያሉት፡፡  


በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ ሊያጋጥም የሚችል ማንኛውንም ጥቃት የማስቀረት አቅሙ አለን – የኢትዮጵያ አየር ሃይል

Informed 2 days ago

በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ሊያጋጥም የሚችል የትኛውም የጠላት እንቅስቃሴ ማስቀረት የሚያስችል የተሟላ ዝግጁነት እንዳለው የኢትዮጵያ አየር ሃይል አስታወቀ።  


Trust, linkage, and cooperation can resolve the Ethiopia-Egypt-Sudan GERD dispute – Ethiopia Insight

Informed 2 days ago

A circumscribed arbitration process might be able to break the dispute-resolution deadlock. Source: Trust, linkage, and cooperation can resolve the Ethiopia-Egypt-Sudan GERD dispute - Ethiopia Insight While world news has been centered on COVID-19, an international dispute has been raging in northeast Africa. The spat could have a lasting impact on the African riparian nations […]  


በመጀመሪያው ምዕራፍ ሀብት ምዝገባ ስድስት ተቋማት በሚፈለገው መልኩ ምዝገባውን አለማካሄዳቸው ተገለጸ

Informed 4 days ago

ዘንድሮ በተጀመረው የሀብት ምዝገባ ሥርዓት በመጀመሪያው ምዕራፍ እንዲያስመዘግቡ ከተመረጡ 16 ተቋማት ውስጥ ስድስቱ በሚፈለገው መልኩ ምዝገባውን ተግባራዊ አለማድረጋቸውን የፌዴራል ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
በኮሚሽኑ የሥነ ምግባር መከታተያና የሙስና መከላከል ዳይሬክተር አቶ አክሊሉ ሙሉጌታ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንዳስታወቁት ፤ ኮሚሽኑ በ2013 ዓ.ም በአገር አቀፍ ደረጃ በተቋማት የመጀመሪያው ምዕራፍ ምዝገባ ከተመረጡት 16 ተቋማት ውስጥ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን፣ ንግድ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምዝገባውን በሚፈለገው መልኩ አላከናወኑም።
ተቋማቱ ምዝገባውን በሚፈለገው መልኩ ላለማከናወናቸው የሥነምግባር ክፍል በቅርቡ ማደራጀታቸው፣ ምዝገባውን ዘግይተው መጀመራቸው፣ የቀድሞው አሰራራቸውን ለመለወጥ በሂደት የሚገኙ መሆናቸውን እንደ ምክንያት ማቅረባቸውን የጠቆሙት ዳይሬክተሩ ፣ በአመራሩ በኩል ለማስመዝገብ ፍቃደኝነት መኖሩን አመልክተዋል ።  


ባይደን ወይስ ትራምፕ? ቅድመ ምርጫውን ማን እየመራ ነው?

Informed 5 days ago

Informer:  BBC News Amharic
ጥቅምት 24፤ አሜሪካውያን ቀጣይ መሪያቸውን የሚመርጡበት ወሳኝ ቀን። የአሜሪካ የምርጫ ትንቅንቅ የምርጫ ዕለት ብቻ የሚታይ አይደለም። የቅድመ ምርጫ ምርጫም አለው። ድምፅ ሰብሳቢ ድርጅቶች የትኛውን ዕጩ ነው የምትመርጡት እያሉ ከአሜሪካውያን የሚሰበስቡትን ድምፅ ይፋ የሚያደርጉበት ነው ቅድመ ምርጫ ማለት። እና በዚህ ቅድመ ምርጫ ማን እየመራ ነው? ትራምፕ ወይስ ባይደን?  


ህወሃት ከፌዴራሊስት ሀይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት ህብረተሰቡን እያወናበደ ይገኛል- የኢትዮጵያ ፌዴራሊስ ሀይሎች ጥምረት

Informed 5 days ago

ህወሃት ከፌዴራሊስት ሀይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት ህብረተሰቡን እያወናበደ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ፌዴራሊስ ሀይሎች ጥምረት አስታወቀ።
በፌዴራሊስ ሀይሎች ጥላ ስር የተሰባሰብን አካላት የህወሃት አካሄድ ስላልተመቸን እንዲታገድ በማድረግ ውይይታችንን በአዲስ አበባ እያካሄድን እንገኛለን ብሏል ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ።
ህወሃት የፌዴራሊስት ሀይሎችን በመጠቀም የስልጣን ጥማቱን ለማሳከት ሲንቀሳቀስ ተመልክተነዋል ያለው ጥምረቱ አሁንም ከፌዴራል ሀይሎች ጋር እየሰራሁ ነው በማለት የትግራይን ህዝብ ለማሳሳት ሲሞክር እየተመለከትን ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ ፌዴራሊስት ሀይሎች ጥምረት በመግለጫው ሀገር በታኝ የሆነ አጀንዳ ካላቸው ቡድኖች ጋር አንዳችም ዓይነት ህብረት እንደሌለን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቅ እንፈልጋለን ነው ያለው።
የፌዴራሊስት ሀይል ሆኖ ለመቀጠል በሀሳብም ይሆን በኢኮኖሚ አሃዳዊ ቁመና ይዞ መቀጠል ተገቢ አይደለም ብሏል ጥምረቱ።  


ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድብ ግንባታ ሱዳንንም ሆነ ግብፅን የመጉዳት ፍላጎት የላትም፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

Informed 5 days ago

ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሱዳንንም ሆነ ግብፅን ለመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሱዳንና ግብፅ በግድቡ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት በጋራ መግባባት ለመፍታት ቁርጠኛ ነች ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ሀገሬ ግንባታውን እያካሄደች ያለው ከ65 ሚሊዮን በላይ የኃይል አቅርቦት ለሌላቸው ዜጎቿ ኃይል ለማሟላትና ከጨለማ ህይወት ለማውጣት ነው” ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ፍለጎት በደንብ ትረዳለች ያሉት ጠቅላይ ሚነስትሩ መሬት ላይ ያለውን አውድ መሰረት በማድረግ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት ዘላቂ መፍትሄ ለመፈለግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆኑዋንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተመድ አረጋግጠዋል፡፡  


"በእጩዎችና በታዛቢዎቹ ላይ ማስፈራርያና ጫና ነበረ" ሳልሳይ ወያነ ትግራይ

Informed 2 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በሰጠው መግለጫ፣ በምርጫው ሂደት በተወዳዳሪዎቹና በታዛቢዎቹ ላይ "ማስፈራርያና ጫና" ይደርስ እንደነበረ አስታወቀ።
ፓርቲው እንዳለው ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች ከምርጫው ቀን በፊት አንስቶ ይስተዋሉ እንደነበር ጠቅሶ፤ በዚህም የገዢው ፓርቲ አባላት ከምርጫው በፊት ቤት ለቤት እየዞሩ "ምልክት የምታደርጉት እዚህ ላይ ነው" በማለት በመራጮች ላይ ጫና ሲያሳድሩ እንደነበር ገልጿል።
በተጨማሪም ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በመግለጫው ላይ እንዳለው በተወዳዳሪዎቹ እና ታዛቢዎቹ ላይ "ማስፈራርያና ጫና" እንደደረሰም አመልክቷል።
"የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮችን በመጠቀም፣ በእጩ ተመራጮቻችን እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ማስፈራርያ ይደርስ ነበር፤ በሕዝብ እንደ ጠላት እንዲታዩና እንዲሸማቀቁም ሲደረግ ነበር" ብሏል።  


የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው ማገዱን አስታወቀ።

Informed 3 weeks ago

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሥራ አስፈጻሚ የድርጅቱን ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው ማገዱን አስታወቀ።
የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ቀጀላ መርዳሳ ዛሬ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፤ አቶ ዳውድ በፓርቲው አንድነትና ሰላማዊ ትግል ላይ እየፈጠሩት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ተደጋጋሚ ጥረቶች ቢደረጉም ያሉባቸውን ችግሮች ከማስተካከል ይልቅ ፓርቲውን የመከፋፈልና አንጃ የመፍጠር አካሄዶችን ሲከተሉ ቆይተዋል። በመሆኑም ለፓርቲው ህልውናና ጥንካሬ ሲባል የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አቶ ዳውድ ኢብሳን ከፓርቲው አግዷቸዋል።
በቀጣይ በፓርቲው ህገ ደንብና አሰራር መሰረት የሚከናወኑ ተግባራት መኖራቸውን ያስታወቁት አቶ ቀጃላ፤ ሁሉንም ሂደቶች በተመለከተ ፓርቲው ለምርጫ ቦርድ አስፈላጊውን ሰነድና መረጃ ማስገባቱን አስታውቀዋል።  


ከጃዋር መሐመድ እስከ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም፡ የ2012 አይረሴ ንግግሮች

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
2012 ዓ. ም. ኢትዮጵያ እንደተቀረው ዓለም ሁሉ በኮሮናቫይረስ የተፈተነችበት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች የተቀሰቀሱበት፣ ብሔራዊ ቤተ መንግሥቱ ለሕዝብ ክፍት የሆነበት፣ ትግራይ ክልላዊ ምርጫ ያካሄደበትም ነበር።
ባሳለፍነው ዓመት ከነበሩ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ የምጣኔ ሀብት፣ የስፖርትና ሌሎችም ሁነቶች ጋር በተያያዘ እነማን ምን አሉ? በዓመቱ ጎልተው ከወጡ ንግግሮች መካከል ዐሥሩን መርጠናል።  


እስራኤልና ባህሬን ስምምነት ላይ ደረሱ

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
እስራኤልና ባህሬን ግንኙነታቸውን ሙሉ በሙሉ ለማሻሻል ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናገሩ።
"ሁለተኛዋ የአረብ አገር በ30 ቀናት ውስጥ ከእስራኤል አገር የሰላም ስምምነት ላይ ትደርሳለች።" ሲሉ ትዊተር ሰሌዳቸው ላይ አስፍረዋል።
ለበርካታ አስርታት በርካታ የአረብ አገራት እስራኤልን የፍልስጥኤም ጉዳይ ከተፈታ በኋላ ግንኙነታቸውን እንደሚቀጥሉ በመግለጽ አግልለው ነበር።
ነገር ግን ባለፈው ወር የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል ስምንት ላይ ደርሳለች።
ከዚያ ጊዜ ወዲህ ባህሬን ትከተላለች የሚል ግምት ነበር።  


አሜሪካ የ1ሺህ ቻይናዊያን ተማሪዎችን ቪዛ ሰረዘች

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
አሜሪካ ለደኅንነቴ ያሰጉኛል በሚል የ1ሺህ ቻይናዊያን እና ተመራማሪዎችን ቪዛ መሰረዟን አስታወቀች፡፡
ይህ እርምጃ ባለፈው ግንቦት ዶናልድ ትራምፕ ‹‹ቻይናዊያን ተማሪዎች መረጃ ይሰርቃሉ፤ ፈጠራ መብትን ይመነትፋሉ›› ብለው ቅሬታ ካቀረቡ በኋላ የተወሰደ የመጀመርያ ውሳኔ ነው፡፡
ቻይና በጉዳዩ ላይ ለጊዜው ምንም ያለችው ነገር የለም፡፡
በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች በ2018 እና 19 ብቻ 370ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበዋል፡፡
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በበኩሏ ‹‹ቪዛ የከለከልናቸው 2ኛ ዲግሪና የምርምር ሥራ ላይ ሊሰማሩ የነበሩትንና ስጋት የሆኑት ብቻ ነው››ብላለች፡፡  


በትግራይ ምርጫ መራጮች ድምጽ መስጠት ጀመሩ

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
የትግራይ ክልል እያካሄደ በሚገኘው ክልላዊ ምርጫ ዛሬ ከንጋት ጀምሮ መራጮች ድምጽ መስጠት ጀምረዋል።  


Ethiopia Hires U.S. Lobby Firm

Informed 3 weeks ago

Informer:  Addis insight
The Ethiopian Embassy in Washington DC has signed a three-month contract, worth 130,000 dollars, with a U.S. lobbying firm Barnes & Thornburg LLP.

The Indiana-based law firm will assist the Embassy in arranging meetings with U.S. government officials on matters of interest to the Embassy and assisting in strategic planning and advocacy.  


Ministry Concludes Annual Meeting Pledging for Better Performance

Informed 3 weeks ago

The annual meeting of senior officials, ambassadors, and consul Generals of the Ministry of Foreign Affairs of Ethiopia is concluded today (September 7).
The meeting was held under the theme: “Diplomatic Mission to National Prosperity," in Bishoftu town for 15 consecutive days.
Attendees have deliberated upon the Ministry’s performance in the current fiscal year and charted out a plan for the upcoming Ethiopian New Year taking the major issues that the ministry has to carry out into consideration.
Senior officials and various stakeholders tabled their views on the revised foreign policy of the country in line with the concept of “medemer” as expounded by H.E. Prime Minister Abiy Ahmed.
The meeting is concluded today with participants pledging that they would do their level best to advance the interest of their country based on the inputs they have got from all of the the major issues of discussion in the past two weeks.  


ወደ ትግራይ በመጓዝ ላይ የነበሩ ጋዜጠኞች ከአውሮፕላን እንዲወርዱ መደረጋቸውን ገለጹ

Informed 3 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
በመጪው ረቡዕ ጳጉሜ 4/2012 ዓ.ም ይካሄዳል የተባለውን የትግራይ ክልል ምርጫን ለመዘገብ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ዛሬ ረፋድ በመጓዝ ላይ የነበሩ የአገር ውስጥና የውጪ ጋዜጠኞች ከቦሌ የአውሮፕላን ማረፊያ እንዳይሄዱ መከልከላቸውን ለቢቢሲ ገለጹ።  


ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.