AskwalaToday is Jummah. Happy Jummah, Happy friday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!


                                     

Welcome to askwala!


Inform          Today is Friday, October 02, 2020

የስልክ ቻርጀር

Informed 3 days ago

በኤሌክትሪክ ቻርጅ የሚሰሩ የተለያዩ እቃዎች የተመረቱበትን የ2000 መጀመሪያን ስናስብ እያንዳንዱ የኤሌክትሮኒክስ እቃ የራሱ ብቻ የሆነ ቻርጀር ነበረው፡፡ ያው አንዱ ቻርጀር ከተበላሸ በሌላ ለመተካት በጣም አስቸጋሪ ነበር፡፡ ከተጠቀሰው ዓመታት በኋላ አብዛኞቹ አምራች ድርጅቶች USB-C የምንላቸውን ቻርጅ ማድረጊያ ገመዶች ማምረት ጀመሩ፡፡
ስልኮትን ቻርጅ ሲያደርጉ “the phone is charging slowly” የሚል ጽሁፍ አንብበው ያውቃሉ? ወይስ ከኮምፒውተር ወይም የስልካችሁ ባልሆነ ቻርጀር ተጠቅማችሁ ቻርጅ ስታደርጉ ዘግይቶ አስቸግሯችኋል? ሌላ አንድ ጥያቄ ቻርጀር ሲገዙ እንዴት ነው የሚመርጡት? እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስና ችግሮቹን ለመፍታት በቅድሚያ ቻርጀር እንዴት ነው የሚሰራው የሚለውን ማወቅ ተገቢ ነው፡፡ በዚህ ጽሁፍም ከቻርጀር ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ልናጋራችሁ ወደድን፡፡ መልካም ንባብ፡፡
ቻርጀር ምናልባት በሀይስኩል ደረጃ የተማርናቸው ሶስት መሰረታዊ የፊዚክስ ትምህርቶች ድምር ውጤት ነው፡፡ እነዚህም power (watts), current (amperes or milliamperes), and voltage (volts) የምንላቸው ናቸው፡፡ ከአንድ ቻርጀር የምናገኘው የሀይል መጠን የcurrent እና የ voltage ብዜት ውጤት ነው፡፡ የሁለቱ ብዜት እየጨመረ በሔደ ቁጥር የምናገኘውም የኃይል መጠን ይጨምራል፡፡ ስለዚህ ስላካችንን በቶሎ ሊሞላልን የሚችልን ቻርጀር ለመግዛት በቻርጀሩ ላይ የተጻፉ ጽሁፎችን መመልከት ተገቢ ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ 87 watt የሚያመነጭ ቻርጀር 20.2 voltን በ4.3 amperes፣ 9 voltን በ 3 amperes ሊሰጠን ይችላል፡፡
ቻርጀር ስንገዛ የገመዱን ጥንካሬ ከማየት በተጨማሪ በቻርጀሩ ላይ የተጻፉ የcurrent እና የ voltage መረጃዎችን መመልከት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እዚህ ላይ አንድ ጥንቃቄ ሊደረግበት የሚገባ ጉዳይ አለ፡፡ ይኽውም ከቻርጀሩ የምናገኘው ኃይል ከሚገባው በላይ ከበዛ ስልካችንን ሊያቃጥልብን ይችላል፡፡
የኃይል ማስተላለፊያ ገመድ ልኬትን (USB standard limit) ማወቅ ሌላው በጣም አስፈላጊው ጉዳይ ነው፡፡ ለUSB 1.0፣ 5 volts በ500 milliamperes ከፍተኛው የኃይል መጠን 2.5 watts ነው፡፡ እንዲሁም በፈጣን ቻርጅ ለማድረግ (“fast charging”) በUSB PD (USB Power Delivery) ከ0.5 እስከ 100 ዋት በ5, 9, 15, or 20 volts ልዩነቶች እና በ100 milliamperes እና በ5 amperes መጠቀም እንችላለን፡፡ የሚጠቀሙትን ቻርጀር በመምረጥ የስልኮትን ደህንነት ይጠብቁ፡፡
መረጃውን ከ popular science አገኘነው  


ሲንጋፖር የዜጎቿ ፊት አይቶ ማንነታቸውን የሚለይ መሣሪያ መተግበር ጀመረች

Informed 5 days ago

Informer:  BBC News Amharic
ሲንጋፖር የዜጎቿ ፊት አይቶ ማንነታቸውን የሚለይ መሣሪያ (ፌሻል ሪኮግኒሽን) በመተግበር በዓለም ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። የአገሪቱ የቴክኖሎጂ ኤጀንሲ መሣሪያው የዲጂታል ምጣኔ ሀብት መሠረት ነው ብሏል።  


የሰው-ሰራሽ አስተውሎት ተአማኒነት እስከ ምን?

Informed 5 days ago

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትልቁ ሀሳብ ማሽኖችን እራስ ገዝ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት እራሳቸውን በራሳቸው የሚያሽከረክሩ መኪኖች፣ ውሳኔ የሚወስኑ ሮቦቶችን እና ሌሎችንም እንደዛ የሆኑ ማሽኖች እየተመረቱ እና እየተሰሩ ነው፡፡ይሁንና እነዚህን ማሽኖች ምን ያህል ማመን ይቻላል የሚለው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡
የሰው ልጆች አዕምሮ እንዳላቸው ሁሉ ኒውራል ኔትዎርክ የሰውሰራሽ አስተውሎቶች አዕምሮ ነው፡፡ ይህ መረብ አዕምሮ ለሰው ልጆች የሚሰራውን ሁሉ ለማሽኖች እንዲሰራ የታሰበ ሲሆን በዋናነት ትንበያን ማመንጨት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ይሁንና ይህ ምንጭ ተአማኒነቱ ምን ያህል ነው የሚለው ነገር አሳሳቢ ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል ብናይ የእራስ ገዝ መኪናዎች ፈተና በመንገድ ላይ የሚገጥሟቸውን ነገራት ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ አለማወቅ ላይ ነው፤ ማለትም መንገድ እያቋረጠ ያለው ነገር እንስሳ ነው ወይስ ህጻን ልጅ ፣ ይህ አካል ፈጣን እርምጃ ነው ያለው ወይስ ቀርፋፋ ፣ ሌላ መኪና በተሳሳተ አቅጣጫ ቢመጣበትስ ወደየትኛው ለመንዳት ይወስናል እና የትኛው ያነሰ ጉዳት ያመጣል የሚሉትን በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ የሚወሰኑ ውስበስብ ውሳኔዎችን ለመወሰን ለማሽኖች ቀላል አይሆንም፡፡
ለመኪናው መረጃ አቀባይ ምንጮች ብዙ ናቸው፡፡ የፊት ለፊት ካሜራ፣ የኮምፒውተር እይታ እና ሌሎችም ይህ መኪናው የትኛውን ሴንሰር ማመን እና መቀበል እንዳለበት ግራ እንያጋባው ያደርጋል፡፡ በተለይም የመረጃ መጣረሶች በሚከሰቱበት ሰዓት መኪናው የሚወስነውን ነገር ጠንቆ ማወቅ ይቸገራል፡፡
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እስከዛሬ ድረስ የሰው ሰራሽ አስተውሎቶችን ተአማኒነት የሚለካ ምንም ዓይነት አሰራር እና መሳሪያ የለም የሚሉት የካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ተመራማረዎች ምንም እንኳን ስህተት የማሽኖች ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆችም መገለጫ ነው ያሉ ሲሆን የሰው ልጆችም የመወሰን ችግር፣ የመዘግየት በሃሪ እና ሌሎችንም የትንበያ እክሎች እንደሚያተናግዱ እናውቃለን ብለዋል፡፡
ይሁንና አሁንም ቢሆን ኒውራል መረብ ላይ እጅግ መልፋት እና የትክክለኝነቱን መጠን ማሰፋት ላይ በትጋት ሊሰራ ይገባል ያሉ ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በኦገስት31 /2020 ማሽኖች በማያውቁበት እና ግራ በሚጋቡበት ጊዜ አናውቅም ማለት የሚችሉበትን አዲስ አሰራር የፈጠሩ ሲሆን ይህ ሁኔታ በተሳሳቱ ውሳዎች የሚከሰቱ ውድመቶችን ለመከላከል ዓይነተኛ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- ScienceDaily  


ቲክቶክና ማይክሮሶፍት ባለቀ ሰዓት ተፋረሱ

Informed 2 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
በዓለም እጅግ ገናና የሆነው የቲክቶክ ቪዲዮ መተግበርያ ለአሜሪካ ኩባንያ ድርሻውን ለመሸጥ ጫፍ ደርሶ ነበር፡፡ ባለቀ ሰዓት ግን ሽያጩ ከሽፏል፡፡
ቲክቶክ በመጨረሻው ሰዓት ላይ የተፋረሰው ከግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ ከማይክሮሶፍት ጋር ነው፡፡ አሁን ማይክሮሶፍት ከድርድሩ በይፋ የወጣ ሲሆን ቀጣዩ የቲክቶክ ገዢ ኦራክል እንደሚሆን እየተነገረ ነው፡፡
ቲክቶክ በአሜሪካ ብቻ 100 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ ዶናልድ ትራምፕ እስከ መስከረም 15 ቲክቶክ መተግበሪያውን ለአሜሪካ ኩባንያ ካልሸጠ ይዘጋል ሲሉ መዛታቸው ይታወሳል፡፡  


ByteDance kicks ball into Trump’s court by rejecting Microsoft and picking Oracle to partner with TikTok in the US

Informed 2 weeks ago

Future of video-sharing app in the US remains uncertain until people know for certain that ByteDance-Oracle partnership will persuade Trump to drop his ban

The deal reached by ByteDance will have Oracle take over the management of TikTok’s US operations  

Source:  South China Morning Post

TikTok’s algorithm not for sale, ByteDance tells US: source

Informed 2 weeks ago

Chinese tech company decides not to sell or transfer code behind the popular video-sharing app, source says.

Decision comes in final countdown to Trump’s deadline for sale of American operations  

Source:  South China Morning Post

The Best TVs For 2020

Informed 3 weeks ago

1. Best TV overall: LG OLEDCX
Type:
OLED
Resolution:
4K
HDR:
HDR10, Dolby Vision, HLG
2. Best 8K TV: Samsung Q900TS
Type: QLED
Resolution: 8K
HDR: Quantum HDR 32x, HDR10, HDR10+, HLG
3. Best TV For Gaming: Samsung Q80T
Type: QLED
Resolution: 4K
HDR: HDR10, HDR10+, HLG
4. Best Budget TV: TCL 6-Series
Type: QLED
Resolution: 4K
HDR: Dolby Vision, HDR10, HLG  

Source:  Forbes

AI shows how hydrogen becomes a metal inside giant planets

Informed 3 weeks ago

Researchers have used a combination of Artificial Intelligence (AI) and quantum mechanics to reveal how hydrogen gradually turns into a metal in giant planets.  

Source:  University of Cambridge

In China, GitHub Is a Free Speech Zone for Covid Information

Informed 3 weeks ago

On the Chinese internet, global social media platforms like Facebook and Twitter are banned, and domestic platforms like WeChat and Weibo are strictly monitored. But GitHub, known to some Chinese internet users as the “last land of free speech in China,” remains accessible.  

Source:  Johns Hopkins Center for Health Security and wired

Terahertz Receiver for 6G Wireless Communications

Informed 3 weeks ago

Future wireless networks of the 6th generation (6G) will consist of a multitude of small radio cells that need to be connected by broadband communication links. In this context, wireless transmission at THz frequencies represents a particularly attractive and flexible solution. Researchers at Karlsruhe Institute of Technology (KIT) have now developed a novel concept for low-cost terahertz receivers that consist of a single diode in combination with a dedicated signal processing technique. In a proof-of-concept experiment, the team demonstrated transmission at a data rate of 115 Gbit/s and a carrier frequency of 0.3 THz over a distance of 110 meters.  

Source:  Karlsruher Institut für Technologie (KIT)

New surgical tools with smart sensors can advance cardiac surgery and therapy

Informed 3 weeks ago

Researchers developed a new class of medical instruments equipped with an advanced soft electronics system that could dramatically improve the diagnoses and treatments of a number of cardiac diseases and conditions.  

Source:  Science X

ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.