AskwalaWishing You a very Beautiful Tuesday

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!


                                     

Welcome to askwala!


Inform          Today is Tuesday, October 20, 2020

የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) 3.3 ትሪሊየን ብር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ

Informed 11 hours ago

የመንግስትን አቋም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያቀረቡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) 3.375 ወይም 107.4 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቀዋል።
በዚህም አለም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከዜሮ በታች እድገት እንደሚያስመዘግብ በሚጠበቅበት ወቅት ኢትዮጵያ 6.1 በመቶ ተስፋ ሰጪ የምጣኔ ሀብት እድገት ማስመዝገቧን ከወቅታዊ ችግር አንፅር ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመልክተዋል።
ለዚህም ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ መንግስት የወሰዳቸው እርምጃዎች ስኬታማነት ለእድገቱ ጉልህ ሚና እንደተጫወቱ ገልፀዋል።
መንግስት በአለም አቀፍ መድረኮች ለአፍሪካም ጭምር የበጀ ከፍተኛ የዕዳ ስረዛ መደረጉና የብድር መክፈያ ጊዜ ማሻሻያ እንዲደረግ የዲፕሎማሲ ስራዎች መሰራታቸው ለእድገቱ ሚናው የጎላ እንደነበር ተመልክቷል።
በዚህ በ2012 የበጀት ዓመት የአገሪቱ ጠቅላላ አገራዊ ምርት 3.375 ትሪሊዮን ብር ወይም 107.4 ቢሊዮን ዶላር መመዝገብ መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት አስረድተዋል።
ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት የነፍስ ወከፍ ገቢ 1000 ዶላር በላይ መድረሱ ኢትዮጵያ ከመካከለኛ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው አገራት ለመመደብ የነበረውን እቅድ እውን ማድረግ ማስቻሉ የእድገቱ ትርጉም ላቅ እንድል እንደደሚያደርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የግብርናው ፣የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፉ እድገቱ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ጥረት የተደረገ ሲሆን በአንፃሩ የትራንስፖርትና ቱሪዝም እንዲሁም የትምህርት ዘርፉ እድገታቸው በኮሮና ምክንያት እንዲስተጓጎል አድርጎታልም ተበሏል፡፡  


Informed 11 hours ago

በከፊል አማራ፣ በከፊል ኦሮሚያ፣ በከፊል ትግራይ፣ አፋር እና ሱማሌ በሚገኙ ወረዳዎች ላይ የበረሀ አንበጣ ጥቃት ደርሷል። በግብርና ሚኒስቴር የተመራ ቡድን በመጀመሪያው ዙር ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል ሥራ ያከናወነ ቢሆንም፣ በሁለተኛ ዙር የተከሰተው የበረህ አንበጣ ጉዳትን አስከትሏል። ለቅኝት የሚሆኑ ሄሊኮፕተሮች እና ድሮኖች እንዲገቡ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደ ቀጠለ ነው። ቅኝት የሚያካሂዱ ሄሊኮፕተሮች በካርጎ ተጭነው ገብተው ሀገራችን የሚገጣጠሙ መሆኑ ጊዜ ፈጅቷል። ከኬሚካል ርጭት ባለፈ፣ አንበጣውን ለማስወገድ በእጅ የማጥፋት ሥራንም ስለሚጠይቅ ማኅበረሰቡ ጥረቱን አጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል። ጥቃቱ እንዳይስፋፋና የረሀብ አደጋ እንዳይከሰት ሥራዎች እየተሰሩ ነው። የደረሰው አደጋ ምርታማነትን ከ5% በላይ እንዳይጎዳ መቆጣጠር ይቻላል። በዘላቂነት ችግሩን ለመፍታት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትንንሽ አውሮፕላኖችን የመጠቀም አቅሙን እንዲያጠናክር እየተሠራ ነው። አረንጓዴ ዐሻራን ማጠናከርም ለጎርፍም ሆነ ለአንበጣ መፍትሄ ይሆናል።  


Informed 11 hours ago

አንድ መንግሥት ፌደራላዊ ከሆነ ዴሞክራሲያዊ ነው፣ አሐዳዊ ከሆነ ደግሞ ዴሞክራሲያዊ ሊሆን አይችልም ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ አይደለም። መንግሥት ልዩ ልዩ ቅርጽ ሊይዝ ይችላል። በታሪካችን የዘውድ አገዛዝ ንጉሳዊ አገዛዝ ሆኖ ቆይቷል። የደርግ መንግሥት አሀዳዊ ነበር። የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ደግሞ ፌደራላዊ ነበር። ነገር ግን ሦስቱም ዴሞክራሲያዊ አልነበሩም። በኢትዮጵያ ባለን የባህል ውቅር እና የቋንቋ ስብጥር ተመስርተን ሁሉ የሚወከልበት ፌደራላዊ አደረጃጀትን መርጠናል። ይህም ስልጣን የታችኛው መዋቅር ድረስ መውረዱን እና ራስን በራስ ማስተዳደር መተግበሩን የሚያረጋግጥ ነው። ከለውጡ በኋላ በክልሎች ጉዳይ የፌደራል መንግሥት ስልጣንን አስመልክቶ ጣልቃ ገብቶ አያውቅም።
የብልጽግና ሕብረ-ብሔራዊነት ለፌደራላዊነት አደጋ ይሆናል ብለው የሚያስቡም አካላት አሉ። ነገር ግን፣ የፌደራል ስነ ስርዓት የሚመራው በሕገ-መንግሥት፣ ብሎም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አማካኝነት በሚወጣ ሕግ ነው። ሕብረ-ብሔራዊ ፓርቲ ደግሞ በፓርቲ ሕገ-ደንብ የሚመራ ሲሆን፣ ቀድሞ ለተጠቀሱት ሕግጋት ተገዢ ነው። በሕብረ-ብሔራዊነት በመገንባት ላይ የምንገኘው ተግባራዊ ፌደራላዊነት እና ዲሞክራሲያዊነትን ነው።  


የምንጊዜውም አጭሩ የጊዜ ርዝማኔ

Informed 12 hours ago

አንድን ድርጊት አከናውነን ለመፈጸም ርዝማኔው ወይም ቆይታው ይለያይ እንጂ ጊዜ ያስፈልገናል፡፡ ታዲያ አንድን ድርጊት ሰርተን የጨረስንበትን ቆይታ የተለያዩ አሀዶችን በመጠቀም እንለካለን፡፡ ይኸውም በአመታት፣ በወራት፣ በሳምንታት፣ ወይም ደግሞ በቀናት፣ በሰዓታት፣ በደቂቃዎችና በሴኮንዶች ሊሆን ይችላል፡፡
ከጊዜ መለኪያ ምድቦች አንጻር ከሴኮንድ በታች ያሉ ለመደበኛ ጊዜ መለኪያ የማንጠቀማቸው ነገር ግን ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ ጥቃቅን ምድቦች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክልም ዴሲ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ አስረኛ)፣ ሴንቲ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ መቶኛ)፣ ሚሊ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሺኛ)፣ ማይክሮ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሚሊዮንኛ)፣ ናኖ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ቢሊዮንኛ)፣ ፒኮ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ትሪሊዮንኛ)፣ ፌምቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ኳድሪሊዮንኛ)፣ አቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ኳንቲሊዮንኛ)፣ ዜፕቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሲክስቲሊዮንኛ)፣ ዮክቶ ሴኮንድ (የሴኮንድ አንድ ሴፕቲሊዮንኛ) እና ፐላንክ (Planck time) የሚታወቁት ናቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩት ምድቦች በጊዜ ምድብነት ይታወቁ እንጂ በቅርብ በወጣ ዘገባ ተመራማሪዎች የብርሃን ቅንጣቶች የሃይድሮጅን ሞሎኪዩልን ለመቋረጥ የሚወስድባቸውን የጊዜ ርዝማኔ መለካት ችለዋል፡፡ ይህም ልኬት እስካሁን ከተመዘገቡት ርዝማኔዎች የመጨረሻ ትንሹ የጊዜ ርዝማኔ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ የብርሃን ቅንጣቶቹ የሃይድሮጅን ሞሎኪዩልን ለማቋረጥ የወሰደባቸው ጊዜም 247 ዜፕቶ ሴኮንድ (zeptoseconds) ሆኗል፡፡
ከዚህ በፊት በ1999 የኖቤል ሽልማት ማግኘት የቻለ በፌማቶ ሴኮንድ የተለካ የኬሚካል ቦንድ ለመሰራትና ለመከፈል (break and form) የሚወስደው ጊዜ ታውቆ ነበር፡፡
የዚህ ግኝት ተጨማሪ ማብራሪያዎች በጥቅምት 16 የሳይንስ ጆርናል ላይ ታትሟል፡፡
ምንጭ Science alert  


የፍልስጤም ዋና ተደራዳሪ በጠና ታመው ወደ የእስራኤል ሆስፒታል ተወሰዱ

Informed 12 hours ago

Informer:  BBC News Amharic
የፍልስጤም ዋና ተደራዳሪ ሳኢብ ኢሬካት በጠና ታመው በእስራኤሉ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።
የፍልስጤም ዋና ተደራዳሪ ሳኢብ ኢሬካት በኮቪድ-19 ከተያዙ በኋላ የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሕክምና እያደረገላቸው የሚገኘው ሆስፒታል ገልጿል።
ትናንት ጠዋት ላይ ሳኢብ ኢሬካት ሕመማቸው እየተባባሰ ሲመጣ ከመኖሪያ ቤታቸው ወጥተው ለእየሩሳሌም ቅርበት ወዳለው የዌስትባንክ ዩኒቨርሲቲተ ሆስፒታል እንዲገቡ ተደርገዋል።  


Informed 12 hours ago

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል ዶክትሪኑ ከአንድ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የመነጨ፣ ከሀገራዊ እሳቤ የተነሳ፣ በሚገባ የሰለጠነ እና የታጠቀ እንዲሆን ሰፊ የማሻሻያ ስራዎች ተሰርተዋል። በምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ በሚያስችል ሁኔታ ተደራጅተዋል። የአመራር ሽግሽግ ማድረግ፣ በሁኔታ ትንተና የማብቃት፣ የኃይል አሰላለፍ ትንተናን በሚገባ በመከወን በቂ አመራር ለመስጠት የሚቻልበት ሁኔታ ተመቻችቷል። አደጋን ለማስቀረት፣ ከገጠመም በአጭሩ ለመቅጨት የሚቻልበት ስራ ተሰርቷል።

Extensive reform has been conducted to ensure that the Ethiopian peacekeeping force is based on a political and national ideology. The forces were well-trained and well-equipped. They are organized in a way that protects the sovereignty of the country under any circumstances. The leadership was restructured and trained on situational analysis and alignment of power to provide appropriate guidance. Efforts have been made to build national capacity to prevent accidents, and if not to avert them easily.  


የአንድ ወር የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ተጀመረ

Informed 14 hours ago

ከጥቅምት 9 እስከ ኅዳር 9 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆየው የእምቦጭ አረም የማስወገድ ዘመቻ ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። በዘመቻው ጣና ሐይቅን የወረረው የእምቦጭ አረም በተቻለ መጠንና በዘላቂነት እንደሚወገድ ይጠበቃል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዘመቻው ማስጀመሪያ ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በዚህ ንቅናቄ ተሳታፊ እንዲሆን በክልሉ መንግስት ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡  


Informed 14 hours ago

ኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ ከቢሮ ወደ ግቢ፣ ከግቢ ወደ ከተማ፣ ከከተማ ወደ ሀገር እየተጓዝን ነው። በትንሹ ጀምሮ ወደ ትልቅ መሄድ ያስፈለገበት ምክንያት፣ አስፈላጊውን ልምድ እየቀሰሙ የጀመሩትን ለማጠናቀቅ እንዲቻል ነው። ትውልድን ከችግር ለማውጣት እኛ ሁሉ እስኪመቻችልን አንጠብቅም። በየጊዜው በሚገጥሙን እክሎች ተዘናግተን የምንቀርም አይደለንም። እየሰራን የሚያጋጥመንን ችግር እንከላከላለን እንጂ፣ ችግር ገጠመ ብለን ለሀገር ያለምነውን ማጠናቀቅን አንዘነጋም። በእንጦጦ ብቻ እንኳን ከ400 በላይ እናቶች እለት እለት ከሚሸከሙት እንጨት ተገላግለዋል፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሥራ አግኝተዋል። ይህን በቦሊ ለሚ የኢንደስትሪ ፓርክ፣ በኮይሻ፣ በወንጪ፣ ጎርጎራ፣ ጣና በለስ እና ሌሎችም እናስቀጥላለን።  


በኢትዮጵያ በዓመት 67 ሺህ 827 ዜጎች በማገዶ ጪስ ህይወታቸውን ያጣሉ

Informed 14 hours ago

64 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ለምግብ ማብሰያ ማገዶ ተጠቃሚ ናቸው

በኢትዮጵያ
በዓመት 67 ሺህ 827 ዜጎች በማገዶ ጪስ የአየር መበከል ህይወታቸውን እንደሚያጡ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ያካሄደው አንድ ጥናት አመለከተ። በግብጽ ደግሞ በዓመት 73 ሰዎች ብቻ በዚህ ምክንያት ይሞታሉ።
ኢንስቲትዩቱ እ.ኤ.አ በ2019 ባደረገው ጥናት እንዳመለከተው ከኢትዮጵያ ህዝብ 64 ሚሊየን ያህሉ ለምግብ ማብሰያ ማገዶ ተጠቃሚ ሲሆን ከዚህም መካከል 67 ሺህ 827 ያህሉ በቤት ውስጥ በሚያጋጥማቸው የአየር መበከል ለሞት ይዳረጋሉ።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ባላገኙ የዓባይ ተፋሰስ አገራትን ጨምሮ በ12 ምሥራቅ አፍሪካ አገራት 278 ሺ 288 ሰዎች በማገዶ ምክንያት በሚፈጠር የቤት ውስጥ አየር ብክለት ለሞት ተዳርገዋል። ከነዚህ ውስጥ 85 በመቶ ድርሻ የያዙት ኢትዮጵያ፣ ዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ ሶማሊያ ፣ ዩጋንዳና ኬንያ መሆናቸውን ጥናቱ አረጋግጧል።
በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2019 ለምግብ ማብሰያነት በሚውል ማገዶና ከሰል በመሳሰሉ መጠቀሚያዎች በተፈጠረው የአየር ብክለት ለሞት ከተዳረጉት መካከል የጨቅላ ህፃናት ሞት ቀዳሚ ሲሆን ለአካል ጉዳት መዳረግ ደግሞ ሁለተኛው ምክንያት ነው።  


Informed 14 hours ago

ህዳሴ ካለፈው ይልቅ በገንዘብ፣ በቴክኒክ እና ምህንድስና ስራም አንጻር ወደፊት ብዙ ሥራን የሚጠይቅ ሆኗል። ፕሮጀክቱ ዕድልም ተግዳሮትም አጣምሮ የያዘ ነው። እንዳይሳካ የሚሹ መብዛታቸው በጥንቃቄ እንድናስቀጥለው ያደርገናል። ሌሎች ተግባራት እና ሁኔታዎች ቢደቀኑብንም እንኳ፣ ለህዳሴ የምንሰጠውን ትኩረት ሳናቋርጥ መቀጠል ይኖርብናል። ሀይድሮ፣ ሶላር፣ ጂኦተርማል ዘርፎች የሚገኙበት የኮይሻ ፕሮጀክት ተቋርጦ የነበር ቢሆንም፣ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
GERD will become more demanding in the future in terms of finance, technique and engineering. The project combines both opportunity and challenges. Those who want it to fail encourage us to protect it and keep it going. Despite the challenges we face, we must not take our focus off GERD. The Koysha project, which includes hydro, solar and geothermal alternatives, has now continued as well.  


የሐኪሙ ምክር -ዶር አፈወርቅ ሐጎስ ! የውስጥ ደዌ ስፔሻሊስትና ሄማቶሎጂስት

Informed 15 hours ago

ባሳለፍነው ሳምንት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የኮሮና አስተኝቶ ማከሚያ ክፍል ተረኛ ሲኒየር በመሆን ለአንድ ሳምንት ሰርቼ ነበር። በሆስፒታላችን የኮሮና ህክምና ከተጀመረበት ላለፉት ሰባት ወራት ገደማ በኮንሰልታንትነት፣ በኮቪድ19 ምክንያት የሚከሰቱ የደም ችግሮች ምርመራ ማድረግ እንዲሁም ህክምናው ለይ ማማከር ፣ የኮቪድ19 ህክምና አጋዥ መመሪያ ዝግጅት ላይ ስሳተፍ የነበረ ቢሆንም በተኝቶ ህክምና ክፍል ውስጥ ተመድቤ ከክፍሉ ባለሞያዎች ጋር በመሆን ወገኖቼን መርዳት በመቻሌና የሞያ ግዴታዬን በመወጣቴ ደስታ ተሰምቶኛል።
በኮቪድ19 በሽታ ለከፋ ጉዳት እና ሞት የሚዳረጉት በዋናነት ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች እንደሆኑ ሁላችንም የምናወቅ ቢሆንም በነኝህ ወገኖች ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት መገንዘብ የሚችሉት በቅርበት የደረሰባቸው ታማሚና ቤተሰብ እንዲሁም የጤና ባለሞያዎች ይመስሉኛል። እነኚህ ተጋላጭ ወገኖች በኮቪድ19 በሽታ ለከፋ ህመምና ሞት ከመጋለጣቸው በተጨማሪ የተለያዩ የደምና ሌሎች የካንሰር ታማሚዎች የምርመራ ሂደታቸውና ሕክምናቸው ተቋርጦ በሽታቸው ስር ሲሰድ በወቅቱ ህክምና ማግኘት ሳይችሉና ሲመቱ፣ የኩላሊት ታማሚዎችና ጥሪታቸውን ሸጠው ህይወታቸውን በዳያሊስ ለማቆየት የሚታገሉ ወገኖች በተለይ ደግሞ በከፍተኛ ወጪ የመልካም ወገኖችና ቤተሰብ ውድ የሂወት ስጦታ ተደርጎላቸው የኩላሊት ንቅለ ተካላ ተሰርቶላቸው በመልካም የጤና ሁኔታ ላይ የነበሩ ወገኖች በኮቪድ19 ተጠቅተው ከባድ የጤና ውስብስብ ውስጥ ሲገቡና ለሞት ሲዳረጉ ማየት የዕለት ተዕለት ክስተት እየሆነ ነው። እነኚህንና ሌሎች በኮቪድ19 ምክንያት እየደረሱ ያሉ ጉዳቶችን ከቀጥተኛ ተጠቂዎች እና የጤና ባለሞያዎች አንደበት ለሕብረተሰቡ በየወቅቱ ማቅረብ በተለይ በአሁኑ ወቅት ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ እየተዛመተ ባለበትና ሕብረተሰባችን የመከላከያ ጥንቃቄዎች ላይ ከፍተኛ ቸልተኝነት እያሳየ ባለበት ሁኔታ ከላይ የጠቀስኳቸውን መንገዶች መጠቀም አስተማሪ ሊሆን ይችላል እላለው ።  


Informed 15 hours ago

እስካሁን 69 ወረዳዎች የመብራት አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል። 12 ያህል መለስተኛ ከተማዎች የሶላር ኃይል አገልግሎት ተጀምሮባቸዋል። ከመደበኛው የኃይል ማመንጫ አሠራር በተለየ፣ ሌሎች አማራጮችን በመጠቀም የኃይል አቅርቦትን ማስፋፋት እንቀጥላለን።

So far, 69 additional woredas have gained access to electricity. Solar services have been launched in 12 small towns. Aside the conventional power generation system, we will continue to expand the power supply using off grid energy options.  


Informed 15 hours ago

ግብርና፣ ኢንደስትሪ፣ ኮንስትራክሽን፣ ጤና እና ማኅበራዊ ዘርፎች የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም እድገት አሳይተዋል። ኮቪድ 19 ጫና ያሳረፈባቸው እና ጥቂት እድገት ብቻ ያስመዘገቡት ደግሞ የትንራስፖርት፣ ትምህርት፣ የህዝብ አገልግሎት ናቸው። ቱሪዝም በ8በመቶ ያህል እድገቱ የቀነሰ ሲሆን፣ በፋይናንስ ሴክተር ከፍተኛ እድገት ታይቷል። የጥሬ ገንዘብ ለውጥ ጋር ተያይዞ የቁጠባ አቅምን መጨመር እና የተበተነ ሀብትን የማሰባሰብ ሥራ ተሠርቷል። ለዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት እንደ ሀገርም እንደ አሕጉርም ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት ከዕዳ ስረዛ እና ቅነሳ አንጻር ትልልቅ ውጤቶችን አስመዝግበናል።
Certain levels of growth has been observed in the agriculture, industry, construction, health and social sectors. Due to stronger impacts of COVID 19 transport, education, and public service sectors have only made some progress. Tourism has decreased progress by 8% while significant growth is observed in the financial sector. In addition to the change of cash denominations, there has been an increase in savings capacity and the accumulation of resources. Inn terms of debt cancellation and reduction, through persistent request to international financial institutions as a country and as a continent, we have achieved great results.  


Informed 15 hours ago

የኮቪድ-19 ተጽዕኖ ቢገጥመንም የተከተልነው መንገድ ዘርፈ ብዙ ችግሮች ስላሉ ቫይረሱን እየተከላከልን ሥራችንን እንሠራለን የሚል ነበር። የዓለም ኢኮኖሚ ያሽቆለቁላል ተብሎ በተገመተበት ሁኔታ ውስጥ በኢትዮጵያ 6.1% የኢኮኖሚ እድገት ተመዝግቧል።

Despite the influence of Covid-19, we followed a strategy of protecting our country from the virus and continuing to work. While the world’s economy is predicted to decline, Ethiopia's economy has grown at a rate of 6.1%.  


የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) 3.3 ትሪሊየን ብር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ

Informed 16 hours ago

የመንግስትን አቋም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያቀረቡ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (GDP) 3.375 ወይም 107.4 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን አስታውቀዋል።
በዚህም አለም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ከዜሮ በታች እድገት እንደሚያስመዘግብ በሚጠበቅበት ወቅት ኢትዮጵያ 6.1 በመቶ ተስፋ ሰጪ የምጣኔ ሀብት እድገት ማስመዝገቧን ከወቅታዊ ችግር አንፅር ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመልክተዋል።
ለዚህም ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ መንግስት የወሰዳቸው እርምጃዎች ስኬታማነት ለእድገቱ ጉልህ ሚና እንደተጫወቱ ገልፀዋል።
መንግስት በአለም አቀፍ መድረኮች ለአፍሪካም ጭምር የበጀ ከፍተኛ የዕዳ ስረዛ መደረጉና የብድር መክፈያ ጊዜ ማሻሻያ እንዲደረግ የዲፕሎማሲ ስራዎች መሰራታቸው ለእድገቱ ሚናው የጎላ እንደነበር ተመልክቷል።
በዚህ በ2012 የበጀት ዓመት የአገሪቱ ጠቅላላ አገራዊ ምርት 3.375 ትሪሊዮን ብር ወይም 107.4 ቢሊዮን ዶላር መመዝገብ መቻሉንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት አስረድተዋል።
ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት የነፍስ ወከፍ ገቢ 1000 ዶላር በላይ መድረሱ ኢትዮጵያ ከመካከለኛ ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው አገራት ለመመደብ የነበረውን እቅድ እውን ማድረግ ማስቻሉ የእድገቱ ትርጉም ላቅ እንድል እንደደሚያደርገው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
የግብርናው ፣የኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፉ እድገቱ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ጥረት የተደረገ ሲሆን በአንፃሩ የትራንስፖርትና ቱሪዝም እንዲሁም የትምህርት ዘርፉ እድገታቸው በኮሮና ምክንያት እንዲስተጓጎል አድርጎታልም ተበሏል  


አሜሪካ ከ70 አመታት በኋላ በፌደራል ደረጃ አንዲት ሴትን በሞት ልትቀጣ ነው

Informed 18 hours ago

Informer:  BBC News Amharic
አሜሪካ ከ70 አመታት በኋላ የፌደራል እስረኛን በሞት ልትቀጣ መሆኑን የፍትህ ዲፓርትመንቱ አስታውቋል። የሞት ብያኔ የተወሰነባት ግለሰብ ሊዛ ሞንቶጎመሪ ትባላለች። ሊዛ፣ በጎሮጎሳውያኑ 2004 ከሞንቶጎነመሪ ወደ ካንሳስ፣ ሚዞሪ ግዛት ቡችላ ለመግዛት ጆ ስቲኔት የተባለች ግለሰብ ቤት ሄደች። ሊዛ ግለሰቧ ቤት ከገባች በኋላ ጆ ስቲኔትን አንቃ መሬት ላይ ጣለቻት። ጆ ስቲኔት በወቅቱ የስምንት ወር ነፍሰ ጡርና ለመውለድም ተቃርባ ነበር ተብሏል።

ጆ ስቲኔት ራሷን በሳተችበት ወቅትም ሊዛ ሆዷን በቢላዋ ቀዳ ልጁን ለማውጣት ስትሞክር ጆ ነቃች። ሊዛም ጆን ከገደለቻት በኋላ ህፃኑን ይዛ ሄዳለች። የራሷም ልጅ እንደሆነ ለሰዎች ትናገር ነበር ተብሏል። በ2007ም የሞንቶጎመሪ ፍርድ ቤት በግድያና ህፃን በማገት ወንጀል የሞት ቅጣት ወሰነባት። በወቅቱ ጠበቆቿም ህፃን እያለች በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ የተወሰነ የአዕምሮ ክፍሏ እንደተጎዳና ይህም ሁኔታ የአዕምሮ ህመም ስላስከተለባት ሞት አይገባትም ብለው ተከላክለው ነበር። ሆኖም ክርክራቸው ተቀባይነት አላገኘም። የሞት ብያኔውም የሚፈፀምባት ከሁለት ወራት በኋላ በኢንዲያና ግዛት ነው። ቅጣቱም ተፈፃሚ የሚሆነው በመርፌ ነው።  


Survey finds that concern about cyberbullying in school-aged children has increased during COVID-19

Informed 18 hours ago

New research released by Relationships Australia shows that concern about cyberbullying has increased during COVID-19, yet people still struggle to know where to turn for help.  

Source:  The Relationships Australia

Study: More Than 200 Million Americans Could Have Toxic PFAS in Their Drinking Water

Informed 18 hours ago

A peer-reviewed study by scientists at the Environmental Working Group estimates that more than 200 million Americans could have the toxic fluorinated chemicals known as PFAS in their drinking water at a concentration of 1 part per trillion, or ppt, or higher. Independent scientific studies have recommended a safe level for PFAS in drinking water of 1 ppt, a standard that is endorsed by EWG.  

Source:  Environmental Working Group

በህገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት ተታለው ወደ ሱዳን ገብተው ታስረው የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ከእስር ተፈቱ

Informed yesterday at 05:39 PM

ጥቅምት ወር በደላሎች አማካኝነት ተታለው ወደ ሱዳን ገብተው ታስረው የነበሩ 38 ኢትዮጵያውያን ክስ ሳይመሰረትባቸው ከእስር መፈታታቸውን በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።
በኮሚዩኒቲ እና በኤምባሲው አስፍላጊውን ድጋፍ በማድርግ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበትና ከቤተስባቻቸው ጋር የሚቀላቀሉበትን መንገድ እየተመቻቸ መሆኑ ተጠቁሟል።
ህገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሱዳንን እንደ መሸጋገሪያ በመጠቀም ወደ ተለያዩ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ዜጎችንን በማይጨበጥ ተስፋ በመደለልና በማታለል በየጊዜው ብዛት ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን ወደ ሱዳን በሕገወጥ መንገድ በማስገባት መንገላታት እንደሚደርስባቸው ተጠቁሟል።
ኤምባሲውም ከሚመለከታቸው የሱዳን የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ተጠቂዎችን ከደላሎች መጋዝን እና ከእስር ነጻ በማውጣት ለሀገራቸው እንዲበቁ ሲያደርግ መቆየቱ ይታውሳል፡፡
በመሆኑም ዜጎች መንግስት የስራ ስምምነት ከተፈራረመባቸው ሀገራት ብቻ በሀገር ቤት በመመዝግብ፣ አስፈላጊው የስልጠና ቅድመ ሁኔታ በማሟላት ወደ ውጭ ጉዞ እንዲያደርጉ ኤምባሲው አሳስቧል።  


በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን የሚያፈሱ የፈረንሳይ ባለሀብቶች ቁጥር ባለፉት 5 ዓመታት በሁለት እጥፍ ጨምሯል

Informed yesterday at 05:24 PM

በኢትዮጵያ መዋዕለ-ነዋያቸውን የሚያፈሱ የፈረንሳይ ባለሀብቶች ቁጥር ባለፉት አምስት ዓመታት በሁለት እጥፍ መጨመሩን በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሪሾ ገለጹ።
በፈረንሳይ ትልቁ የኢንቨስትመንት ማህበር ልዑካን ቡድን ከሁለት ወር በኋላ ኢትዮጵያን እንደሚጎበኝም ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሪሾ በኢትዮጵያ መዋዕለ-ነዋያቸውን የሚያፈሱ የፈረንሳይ ባለሀብቶች ቁጥር አሁን ላይ 55 መድረሱንና ይህም ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረው አንጻር በሁለት እጥፍ መጨመሩን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ እየሰሩ የሚገኙት የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢነርጂ ዘርፍ በተለይም በእንፋሎትና በሃይድሮ ፓወር የንግድ ልማት እንዲሁም በአምራች ዘርፍ በዋነኛነት መሰማራታቸውን አመልክተዋል።
ታዋቂ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በኢነርጂ፣ ሎጅስቲክና ቴሌኮም ዘርፎች መዋዕለ ነዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እያሳዩ መሆኑንም አምባሳደሩ ተናግረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ በሎጅስቲክና በባህር ትራንስፖርት የሚታወቁ የፈረንሳይ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
አምበሳደሩ በቴሌኮም መስክም በኢትዮጵያ ለመሰማራት የሚሰጠውን ፈቃድ ለማግኘት የፈረንሳይ ኩባንያዎች ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸውም አክለዋል።  


121 ሚሊዮን ብር ድጎማ የተደረገላቸው 560 አውቶብሶች ከነገ ጀምሮ ለህዝቡ አገልግሎት ይሰጣሉ - ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Informed yesterday at 04:17 PM

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት 121 ሚሊዮን ብር ድጎማ የተደረገላቸው 560 አውቶብሶች ለህዝቡ አገልግሎት እንዲሰጡ አስተዳደሩ መከራየቱን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
የመዲናዋን ነዋሪ የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ተግባራዊ ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ለከተማዋ ነዋሪ አገልግሎት የሚሰጡ አስተዳደሩ ከሀገር አቋራጭ ትራንስፖርት ማህበራት የተከራያቸው 560 አውቶብሶች ከነገ ጀምሮ ወደ ስራ ይገባሉ።
ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በስነ ስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት የትራንስፖርት ችግር በከተማዋ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ነው።
በቀጣይ 3 ሺህ የሚሆኑ አውቶብሶችን በግዢ ለማስገባት የከተማ አስተዳደሩ በሂደት ላይ መሆኑንም ም/ከንቲባዋ ተናግረዋል።
አውቶብሶቹ ነገ ስራ የሚጀምሩ ሲሆን ለአንድ ሳምንት ያህል ለሁሉም የከተማዋ ነዋሪ የነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ተገልጿል።
በይድነቃቸው ሰማው  


ዩኒቨርሲቲዎች #የምርምር ፣ #አጠቃላይ ፣ #የአፕላይድ ሳይንስ ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂና የቴክኒካል ዩኒቨርስቲዎች ተብለው ተለዩ

Informed 2 days ago

Informer:  Debark University
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ስርዓት ልየታ መመሪያ በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል።
በዚህ
መሰረት ተቋማቱን በአምስት የትኩረት መስኮች የተለዩ ሲሆን ፥ በዚህም የምርምር ፣ አጠቃላይ ፣ የአፕላይድ ሳይንስ ፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የቴክኒካል ዩኒቨርስቲዎች ተብለው ተለይተዋል።
በምርምር ዩኒቨርስቲነተ የተመደቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም፥ አዲስ አበባ፣ አርባ ምንጭ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ሀረማያ፣ ሀዋሳ፣ ጅማ እና መቐለ ናቸው።
አክሱም፣ አምቦ፣ አርሲ፣ አሶሳ፣ ደብረ ብርሃን፣ ደብረ ማርቆስ፣ ዲላ፣ ድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ኮተቤ፣ ሰመራ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወልቂጤ፣ ወለጋ እና ወሎ ዩኒቨርስቲ የአፕላይድ ዩኒቨርስቲዎች ተብለዋል።
አዲግራት፣ ቦንጋ፣ ቦረና፣ ቡሌ ሆራ፣ ደባርቅ፣ ደብረ ታቦር፣ ድምቢ ዶሎ፣ ጋምቤላ፣ እንጅባራ፣ ጂንካ፣ ቀብሪ ደሃር፣ መዳ ወላቡ፣ መቅደላ አምባ፣ መቱ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ራያ፣ ሰላሌ፣ ዋቸሞ፣ ወራቤ እና ወልዲያ ዩኒቨትስቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ዩኒቨርስቲዎች ሆነዋል።
የአዳማ ሳይንስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና የአዲስ እርበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲነት ተለይተዋል።
በቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ስር ደግሞ የፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተመድቧል።
ይህንን ውሳኔ ለማሳለፍ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ መሰረት በማድረግ ጥናቱ ስለመደረጉም ተነስቷል።
ይህንንም የልየታ ምክረ ሃሳብ ተግባራዊ ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ እንደሆንም ተጠቁሟል።
ምንጭ FBC.com  


ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ትኩረት መስክ ቶሎ ይገባሉ

Informed 2 days ago

ዩኒቨርሲቲዎች በተልእኮ እና በትኩረት መስክ ወደ ተደለደሉበት ዓላማ ቶሎ እንዲገቡ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ገለጹ፡፡
ዶ/ር ሙሉ እንደ ገለጹት የዩኒቨርሲቲዎች ልየታ ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎቹን ለማበላለጥ ሳይሆን ከነበራቸው የትኩረት አቅጣጫ በመነሳት የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ነው፡፡
በትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ጥናት ውጤት መሠረት 8 የምርምር፣ 15 የአፕላይድ ሳይንስ፣ 2 የሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ቀሪዎቹ 21 የአጠቃላይ ዩኒቨርሲቲ ተብለው ተለይተዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ዩኒቨርሲቲዎቹን በትኩረት መስክ መለየት የሀገራችንን ብልጽግና ለማሳካት እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ተቋማቱ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ዓርአያ ሆነው የሀገራችን ኢኮኖሚ የሚፈልገውን ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ማፍራት እንዳለባቸው ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡  


Two planets around a red dwarf

Informed 2 days ago

The “SAINT-EX” Observatory, led by scientists from the National Centre of Competence in Research NCCR PlanetS of the University of Bern and the University of Geneva, has detected two exoplanets orbiting the star TOI-1266. The Mexico-based telescope thus demonstrates its high precision and takes an important step in the quest of finding potentially habitable worlds.  

Source:  University of Bern

Safe Sex or Risky Romance? Young Adults Make the Rational Choice

Informed 2 days ago

Eros, the fabled Greek god of love, was said to bring confusion and weaken the mind. New research, however, suggests that young adults are instead quite rational when it comes to selecting potential sexual partners.  

Source:  Association for Psychological Science

Remember That Fake News You Read? It May Help You Remember Even More

Informed 2 days ago

Thinking back on a time you encountered false information or “fake news” may prime your brain to better recall truthful memories.  

Source:  Association for Psychological Science

Researchers Find Existing Medications May Fight Coronavirus Infection

Informed 2 days ago

University of New Mexico researchers who combed through a “library” of previously approved drugs believe they have identified a medication with the potential to help speed a patient’s recovery from SARS-CoV-2 infection.  

Source:  University of New Mexico Health Sciences Center

Ground-breaking discovery finally proves rain really can move mountains

Informed 2 days ago

A pioneering technique which captures precisely how mountains bend to the will of raindrops has helped to solve a long-standing scientific enigma.  

Source:  University of Bristol

Internet connectivity is oxygen for research and development work

Informed 2 days ago

Fast and reliable internet access is fundamental for research and development activity around the world. Seamless connectivity is a privilege we often take for granted. But in developing nations, technological limitations can become stumbling blocks to efficient communication and cause significant disadvantages.  

Source:  University of Illinois College of Agricultural, Consumer and Environmental Sciences

New research comparing HIV medications set to change international recommendations

Informed 2 days ago

A new study by University of British Columbia faculty of medicine researchers is set to change international treatment recommendations for people who are newly diagnosed with HIV—an update that could affect nearly two million people per year worldwide.  

Source:  University of British Columbia

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ በሁሉም ዘርፍ ያሉ ተቋማት ላይ የተጣሉ ግዴታዎች

Informed 3 days ago

ማናቸውም መንግስታዊም የሆነ የግል ተቋም የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጋላጭነትን ለመከላከል፣ ዝግጁነት ለማረጋገጥ እና ምላሽ አሰጣጥ ሁኔታን በተመለከተ በዘርፉ በመመሪያ የሚወሰኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች የማክበር እና የማስከበር ግዴታ አለበት፡፡  


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ የኢንዱስትሪ እና ምርት መስክ የተሰማሩ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ላይ የተጣሉ ግዴታዎች

Informed 3 days ago

ለሰራተኞቻቸው ስለበሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን ማዘጋጀት፣ የስራ ቦታዎችን በቂ የአየር ዝውውር ሊኖርበት በሚችል መልኩ የማደራጀት፣የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ ሰራተኞች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችንመተግበራቸውን የማረጋገጥ፣ እንዲሁም ሌሎች ዘርፉ በመመሪያ የሚያስቀምጣቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው፡፡  


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ የሆቴልና ቱሪዝም አሰሪዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች

Informed 3 days ago

ማንኛውም በሆቴል፣ በአስጎብኚነት እና በሌሎችም የቱሪዝም መስክ የተሰማሩ ተቋማት በሰራተኞቻቸው እና ተገልጋዮቻቸው መካከል ሁለት የአዋቂ እርምጃ ወይም የሁለት ሜትር ርቀት እንዲኖር የማድረግ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን የመቆጣጠር፣ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት፣ ለሰራተኞቻቸው የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ እንዲሁም የቱሪዝም አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ዘርፉ በመመሪያ የሚያስቀምጣቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።  


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ የኮንስትራክሽን አሰሪዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች

Informed 3 days ago

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክት አሰሪዎች በግንባታ ሳይቶች ላይ አስፈላጊውን ንጽህና ለመጠበቅ የሚረዱ እንደ ውሃ፣ ሳሙና፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ፣ ሳኒታይዘር ወይንም አልኮል፣ የሙቀት መለኪያ መሳሪያ እንዲሁም የጸረ ተህዋሲያን ግብዓት የማቅረብ ወይንም የሟሟላት፣ ሰራተኞች በተቻለ መጠን ርቀታቸው ጠብቀው እንዲሰሩ የማድረግ፣ እንዲሁም በኮንስትራክሽን ዘርፍ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጋላጭነትን ለመከላከል፣ ዝግጁነት ለማረጋገጥና ምላሽ አሰጣጥ ሁኔታን በተመለከተ በዘርፉ በመመሪያ የሚወሰኑ የጥንቃቄ እርምጃዎች የማክበር እና የማስከበር ግዴታዎች አለባቸው፡፡  


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች

Informed 3 days ago

ሀገር አቀፍም ሆነ የከተማ ውስጥ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሰው በህግ ከሚወሰነው የመጫን አቅም ልክ ሰዎችን የመጫን፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ያላደረጉ ሰዎችን አገልግሎት አለመስጠት፣ መስኮቶችን በመክፈት በተሽከርካሪው ውስጥ በቂ የአየር ዝውርውር እንዲኖር የማድረግ እና በዘርፉ በመመሪያ የሚወጡ ሌሎች መወሰድ የሚገባቸውን የጥንቃቄ እርምጃዎች በመተግበር አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡  


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ አገልግሎት ሰጪ በሆኑ የመንግስትና የግል ተቋም ላይ የተጣሉ ግዴታዎች

Informed 3 days ago

ማንኛውም አገልግሎት የሚሰጥ የመንግስታዊ እና የግል ተቋም አገልግሎቱን ለማግኘት ወደ ተቋሙ ለሚመጡ ተገልጋዮች ቫይረሱን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳሶችን የማቅረብ፣ ተገልጋዮች ሁለት የአዋቂ እርምጃ ተራርቀው የሚቆሙበትን ቦታ ምልክት የማድረግ እና ተገልጋዮች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪም ለሰራተኞች ስለበሽታው አስፈላጊውን መረጃ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የማድረስ፣ በመግቢያና መውጫ በሮችና ሌሎች አስፈላጊ ቦታዎች በሽታውን ለመከላከል የሚያስችሉ አስፈላጊ ነገሮችን የማዘጋጀት፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሚረዱ የጥንቃቄ ቁሳቁሶችን የማቅረብ፣ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረጋቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ጥንቃቄዎችን መተግበራቸውን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው፡፡  


የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ በግለሰቦች ላይ የተጣሉ ግዴታዎች

Informed 3 days ago

በመመሪያዉ አንቀፅ 5 ላይ ማንኛውም ኮቪድ 19 በሽታአለብኝ ብሎ እራሱን የሚጠረጥር ሰው ለሚመለከተው አካል ሪፖርት በማድረግ የመመርመርና ቫይረሱ ወደ ሌሎች እንዳይተላፍ አስፈላጊውን ጥንቃቄ የማድረግ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ በተጨማሪም በሽታው አለበት ተብሎ የሚጠረጠር ሰው ሰለመኖሩ የሚያውቅ ማንኛውም ሰው ለጤና ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ በአቅራቢያው ለሚገኙ የጤና ተቋም ወይም ባለሞያ የማሳወቅ ግዴታ አለበት፡፡  


ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30/2013ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ ያደርጋሉ

Informed 3 days ago

ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ትምህርትና ስልጠናን ለማስቀጠል ሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23-30/2013ዓ.ም አስፈላጊውን ዝግጅት በማጠናቀቅ የመጀመሪያ ዙር የተማሪዎች ቅበላ እንዲያደርጉ አሳሰቡ፡፡
ክቡር ሚኒስትሩ በቅርቡ በኮቪድ-19 ፕሮቶኮል መሠረት በተካሔደው የተቋማት ድጋፍና ምልከታ ውጤት በአንድ አንድ ተቋማት የታዩት ክፍተቶች በፍጥነት ተሟልተው በግልጽ መርሃ-ግብር ለተማሪዎች ቅበላ እንዲያደረግ አሳስበዋል፡፡
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ የተቋማቱን የቅድመ ቅበላ ዝግጅት ዳሰሳ ውጤት ባቀረቡት ገለጻ ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ የመማር ማስተማር ስራን ማስቀጠል ጥንቃቄ የሚሻ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በሀዋሳ እየተካሔደ ባለው የተማሪዎች ቅበላ ቅድመ ዝግጅት የማጠቃለያ ምእራፍ የግምገማ መድረኩ ላይ ኮቪድ-19 እና የሠላም ጉዳይ አስመልክቶ በተነሱት ስጋቶች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
ተሳታፊዎቹ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና በየደረጃው ያሉት ባለድርሻ አካላት ከሚኒስቴሩ እና ከተቋማቱ ጋር እንደሚሰሩ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡
በየደረጃው ያሉት ባለድርሻ አካላት፣ የተቋማቱ አመራሮች የበለጠ ተቀራርበው በቅንጅት በመስራት ተቋማቱ ሠላማዊ፣ ሳቢ እና የከፍተኛ ትምህርት የዓለም አቀፋዊነት(Universal) ባህሪ እንዲኖራቸዉ እና ከማንኛዉ ከተቋቋሙለት ዓላማ ጋር ካልጠጣጣሙ ጉዳዮችም እንዲላቀቁ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑን ዶ/ር ሳሙኤል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ክቡራን ሚኒስትሮች እና የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች በቅድመ ዝግጅት ሁኔታ ዙሪያ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለተማሪዎቹ እና ለማህበረሰቡ ተገቢው ግንዛቤ መሰጠት እንዳለበት የሚዲያ ተቋማቱም ሚናቸዉን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡  


ተጠንቶ የማያልቀው ስነ ከዋክብትና አዲስ መኖሪያ ፍለጋ

Informed 3 days ago

የዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች 24 ፕላኔቶችን በፀሐይ ዙሪያ ማግኘታቸው ተሰማ፡፡ The Cosmic Companion የተሰኘ የስነ-ከዋክብት መረጃዎችን የሚያዎጣው ተቋም እንደዘገበው ከምድራችን የተሻለ ምቹነት ያላቸው 24 ፕላኔቶች የራሳቸው ከዋክብትንም የያዙ ናቸው፡፡
ፕላኔቶቹ የሚዞሯቸው አብዛኞቹ ከዋክብት ከፀሐይ በተሻለ መልኩ ለህይዎት ተስማሚ ሊሆኑ እንደሚችሉ ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ጂኦ ባዮሎጂስት የሆኑት Dirk Schulze-Makuch ተስፋ ሰጪ ሁኔታ በታየባቸው ፕላኔቶች ተጨማሪ ጥናቶችን እናካሂዳለን ብለዋል፡፡
እነዚህ ምቹ መኖሪዎች ከመሬት የተሻለ ሙቀት፣ ርጥበት፣ መጠንና እድሜ ያላቸው እንደሚሆን ተገምቷል፡፡ ተመራማሪዎቹ እንዳሉት በጣም ረጅም እድሜ ያላቸው ፕላኔቶች ለአደገኛ ጨረር ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ለህይዎት አማራጭ ሊሆኑ የሚችሉት ፕላኔቶች ከ5 እስከ 8 ቢሊዮን ዓመት የሚደርስ ዕድሜ ያላቸው ናቸው፡፡
ከእድሜ በተጨማሪ የእነዚህን ፕላኔቶች ለህይዎት ምቹነት ክብደታቸውና መጠናቸው ይወስነዋል፡፡ በተጨማሪም መጠነ-ሙቀት የአዲስ ፕላኔት ፍለጋው አንድ አካል ነው፡፡ በአማካኝ 20 ዲግሪ ሴልሺየስ ያላቸው ፕላኔቶች ከምድራችን የተሻለ ምቹነት ይኖራቸዋል፡፡
ምንጭ፡- The Cosmic Companion  


የውል ምንነት

Informed 3 days ago

ዉል ምንድን ነዉ? ከሚለዉ ፅንሰ-ሀሳብ ስንነሳ “ዉል አንድን ግዴታ ወይም ከዚሁ ግዴታ ጋር የተያያዙ ሌሎች በርከት ያሉ ግዴታዎችን የሚያቋቁም ተግባርን የሚያመለክት አነጋገር ነዉ” በማለት ፕ/ር ጥላሁን ተሾመ ተርጉመውታል፡፡ በዚህ ግዴታ ባለገንዘብ የሆነዉ ወገን አንድ ነገር እንዲፈጸምለት የመጠየቅ መብት የሚኖረዉ ሲሆን ባለዕዳዉ ደግሞ አንድን ነገር የመፈጸም ግዴታ ይጠበቅበታል” በማለት አብራርተዉ ገልፀዉታል፡፡
እንዲሁም በፍ/ሕ/ቁ 1675 ላይ “ዉል ማለት ንብረታቸዉን የሚመለከቱ ግዴታዎችን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸዉ ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መሀል የሚደረግ ስምምነት ነዉ” በማለት ትርጉም ሰጥቶታል፡፡  


የዉል አመሠራረት

Informed 3 days ago

በፍ/ሕ/ቁ 1678 መሰረት በሕግ ፊት የሚፀና ውል የሚከተሉትን ማሟላት አለበት፡- ዉል የሚፈፀመዉ ለመዋዋል ችሎታ ባላቸዉ ሰዎች መካከል ጉድለት የሌለው ስምምነት መኖር፣ ተወያይ ወገኖች የሚዋዋሉበት ጉዳይ በእርግጠኝነት የሚቻል፣ ህጋዊና ሞራላዊ ጉዳይ ላይ መሆን የገባዋል፣ የዉል አቀራረጹ ወይም አፃፃፉ በህግ (ፎርም) ተለይተዉ የተቀመጡ ወይም ተዋዋይ ወገኖች ተለይቶ እንዲቀመጥ ከተስማሙበት የዉል ጉዳይ በቀር የተለየ የዉል ፎርም የማያስፈልግ መሆኑ፡፡
ከዚህ በላይ የተመለከትነዉ የዉል ትርጉም እና የዉል አመሰራረት ለሁሉም አይነት ዉሎች (የቤት ኪራይ ውል ጨምሮ) የሚያገለግል ደንብ ነዉ፡፡ ይህም የዉል ጠቅላላ ደንብ በመባል ይጠራል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ይህ ደንብ ለጠቅላላ ዉልም ይሁን ለልዩ ዉሎች የሚያገለግል ስለሆነ ነዉ፡፡  


የቤት ኪራይ ዉል

Informed 3 days ago

በህጋችን ላይ የቤት ኪራይ ዉል ትርጉም ባይሰጠዉም ከህጉ ድንጋጌዎች በመነሳት “አንድ የቤት ወይም ህንፃ ባለቤት ወይም ባለይዞታ የሆነ ሰዉ ቤቱን ወይም ህንፃዉን ሙሉ በሙሉ ወይም የተወሰኑ ክፍሎችን ወይም አንዱን ክፍል ለሌላ ሰዉ ከነዕቃዉ ወይም ባዶዉን የተወሰነ የኪራይ ዋጋ በመቀበል ለተወሰነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ አስተላልፎ መስጠት /ማከራየት/” ማለት ነዉ በማለት በግርድፉ ትርጉም ሊሰጠዉ ይችላል፡፡ ነገር ግን የሆቴል ክፍልን ለተወሰነ ጊዜ ተከራይቶ መኖርን አያካትትም፡፡ (ፍ/ሕ/ቁ 2945)  


የቤት ኪራይ ክፍያ መጠን እና ጊዜ

Informed 3 days ago

ተዋዋዮቹ ለፈለጉት ጊዜ ያህል በዉላቸዉ እንዲቆይ፣ በፈለጉት ዋጋ እና በተስማሙበት ጊዜ ክፍያዉ እንዲፈፀም በዉላቸዉ ዉስጥ ሊስማሙ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በዉላቸዉ ዉስጥ እነዚህን ነገሮች ካልገለፁ በህጉ የተቀመጠው ተፈፃሚ ይሆናል፡፡ በፍ/ሕ/ቁ 2950(2) ላይ ተዋዋይ ወገኖች በዉላቸዉ ዉስጥ የኪራዩን መጠን ካላስቀመጡ ወይም በሚያጠራጥር ጊዜ የማዘጋጃ ቤት ባለስልጣናት በወሰኑት ታሪፍ መሠረት ወይም የተወሰነ ታሪፍ ከሌለ የቦታዎቹን ልማድ በመከተል የሚወሰን መሆኑ ተደንግጓል፡፡ የዉሉን ቆይታ ጊዜ በተመለከተ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ሊሆን እንደሚችል በዚሁ ሕግ ተመላክቷል፡፡
የኪራዩ ዋጋ የሚከፈልበትን ጊዜ በተመለከተ በፍ/ሕ/ቁ 2951 ላይ ተዋዋይ ወገኖቹ በዉላቸዉ ዉስጥ ያልተስማሙበት ከሆነ፡- የቤት ኪራይ ዉሉ ለአንድ ወይም ለብዙ አመታት ተደርጎ እንደሆነ ኪራዩ በየሶስት ወሩ መጨረሻ የሚከፈል ይሆናል፡፡ የቤት ኪራይ ዉሉ በጣም አጭር ለሆነ ጊዜ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ በየወሩ መጨረሻ ላይ የሚከፈል ይሆናል፡፡  


የተከራዩትን ቤት ስለማደስ

Informed 3 days ago

ተዋዋይ ወገኖች በቤት ኪራይ ዉሉ ዉስጥ የቤቱን እድሳት በተመለከተ ከተስማሙ በዉሉ መሰረት የቤቱ እድሳት ይፈፀማል፡፡ ነገር ግን ተዋዋዩቹ ስለ ቤቱ እድሳት በዉላቸዉ ላይ የገለፁት ነገር ከሌለ ማደስ ማለት የቤቱ መዝጊያዎችን ወይም መስኮቶችን፣ የቤቱን ወለሎችን ወይም ንጣፎችን፣ የዉሃ መስመሮችንና የፍሳሽ ማስወገጃዎችን ማደስ እና ቤቱን የማፅዳት እና በደንብ መያዝ መሆኑን በፍ/ሕ/ቁ 2954 ላይ ተደንግጓል፡፡ ተከራዩ ሊያድሳቸዉ የሚገባዉን የተከራያቸዉን ቤቶች በራሱ ኪሳራ ለማደስ ይገደዳል በማለት በፍ/ሕ/ቁ 2953 ላይ ተደንግጓል፡፡ ይህም ማለት ተከራዩ በኪራይ ዉሉ ዉስጥ ለማደስ በተስማማዉ መሰረት በራሱ ወጭ ለማድስ ይገደዳል ማለት ነዉ፡፡  


የተከራዩትን ቤት ስለማከራየት

Informed 3 days ago

ሁለቱም ወገኖች ከተስማሙ የተከራየ ቤት ለሌላ ሰው መልሶ ሊከራይ ይችላል፡፡ ቢሆንም የቀድሞ ግዴታዎች ቀሪ አይሆኑም፡፡ (የፍ/ሕ/ቁ 2960)  


የቤት ኪራይ ክፍያን በጊዜዉ አለመክፈል ዉጤት

Informed 3 days ago

ተከራይ የሆነዉ አካል የቤት ኪራይ ክፍያዉን በጊዜዉ ያልከፈለ እንደሆነ ወይም ሳይከፍል የቆየ እንደሆነ የሚያስከትለዉ ዉጤት በፍ/ሕ/ቁ 2952 ላይ ተቀምጧል፡፡ በዚሁ መሠረትም፡- ዉሉ ለአንድ ዓመት ወይም ከዛ ለበለጠ ጊዜ የተደረገ ከሆነ የሠላሳ ቀን ማስጠንቀቅያ፣ ለአጭር ጊዜ የተደረገ ከሆነ አከራዩ የአስራ አምስት ቀን ማስጠንቀቅያ በመስጠት፣ በዚህ ጊዜ ካልተከፈለ ዉሉን የሚያቆርጥ መሆኑን መንገር ይችላል፡፡  


የቤት ኪራይ ዉል የሚፈርስባቸው ምክንያቶች

Informed 3 days ago

ተዋዋይ ወገኖች ያደረጉት የቤት ኪራይ ዉል በተለያየ ሁኔታ ሊቋረጥ ይችላል፡፡ እነዚህም፡- የቤት ኪራይ ዉሉ ጊዜዉ ሲያበቃ፣ ተዋዋይ ወገኖች በስምምነት ዉላቸዉን ለማቋረጥ ሲስማሙ፣ ተከራይ ኪራዩን በጊዜዉ ባለመክፈሉ አከራዩ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሰጥቶት በዚህ ጊዜ ዉስጥ ሳይከፍል በመቅረቱ አከራዩ ዉሉን ካቋረጠዉ፣ አከራዩ ቤቱን ሲያድስ ለተከራዩና ለቤተሰቡ አስፈላጊ የሆነዉን መኖሪያ ሊጠቀምበት የማይችል ያደረገዉ እንደሆነ ተከራይ አከራዩን በመጠየቅ ውሉን ሲያፈርስ (ቁ. 2956/2/)፣ አከራይ ቤቱን ፈልጎት ለተከራይ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ወይም ተከራዩ ቤቱን መልቀቅ ፈልጎ ለአከራዩ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ሲያቋርጥ፡፡
ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ምክንኛቶች አንድ የቤት ኪራይ ዉል ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ነገር ግን አከራይ ቤቱን ፈልጎት ለተከራይ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ሲያቋርጥ አከራዩ ሊሰጥ የሚገባዉ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ምንያክል መሆን አለበት የሚለዉ በህጉ መልስ አልተሰጠዉም፡፡ ይህ ጉዳይ በህብረተሰቡ ዉስጥም የተለያየ ዉዥንብር እና ጭቅጭቅ ሲፈጠር ይታያል፡፡ በፍትሐ ብሔር ጉዳያች ህግን ስንተረጉም ከምንከተላቸዉ መርሆች አንዱ ለተመሳሳይ ጉዳይ ተመሳሳይ ሁኔታን (አናሎጂ) በመጠቀም መተርጎም ይቻላል፡፡
በዚሁ መሰረትም አከራይ ቤቱን ፈልጎት ለተከራይ ማስጠንቀቂያ ጊዜ በመስጠት ሲያቋርጥ አከራዩ ሊሰጥ የሚገባዉ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ተከራዩ ኪራዩን በጊዜዉ ባለመለክፈሉ አከራዩ በፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥር 2952 መሠረት የሚሰጠዉ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ለዚህም
ተግባራዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም ማለት፡- የቤት ኪራይ ዉሉ ለአንድ ዓመት ወይም ከዛ በላይ ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ አከራዩ የሠላሳ ቀን ማስጠንቀቅያ በመስጠት፣ የቤት ኪራይ ዉሉ ለአጭር ጊዜ ተደርጎ እንደሆነ አከራዩ የአስራ አምስት ቀን ማስጠንቀቅያ በመስጠት፣ ዉሉን ሊያቋርጥ ይችላል፡፡ ወሉ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ከሆነ ግን ሕጉም ስላልመለሰው ለክርክር ሊዳርግ እንደሚችል መገንዘብ ይቻላል፡፡  


በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ለማሻሻያ ሥራ ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት መርሃ ግብር

Informed 3 days ago

ቅዳሜ ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በአደዋ ድልድይ፣ በአቧሬ፣ በኳስ ሜዳ፣ በቤሌር፣ በእንደራሴ ሆቴል፣ በመለስ ፋውዴሽን፣ በልቤ ፋና ኮንደሚኒየም፣ በካዛንቺስ በከፊል፣ በሚኒሊክ ሆስፒታል፣ በአራት ኪሎ፣ በፓርላማ፣ በግቢ ገብርዔል ቤተ-ክርስትያን፣ በዮርዳኖስ ሆቴል፣ በጉድ ሼፐርድ፣ በጣልያን በኤምባሲ፣ በቤላ ሆስፒታል፣ በቤተመንግስት በከፊል እና አካባቢዎቻቸው፣
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በኦሎምፒያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮሚያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ፣ በሃና ማርያም፣ በሃይሌ ጋርመንት፣ በቆጣሪ ኮንዶሚኒየም፣ በኦሮሚያ ኮንደሚኒየም፣ በማንጎ ሰፈር፣ በምስራቅ ፀሀይ ገብርኤል ፊት ለፊት፣ በየተባበሩት ነዳጅ ማደያ፣ በሚካኤል ፊት ለፊት፣ በጆሞ 1 በከፊል፣ በጆሞ 3፣ በወሎ ሰፈር፣ በጃፓን ኤምባሲ፣ በሩዋንድ ኤምባሲ፣ በካራማራ ድልድይ እና አካባቢዎቻቸው፤
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በመነን ት/ቤት፣ በሽሮ ሜዳ፣ በስብሰባ ማዕከል፣ በቀጨኔ መድሀኒዓለም፣ በላዛሪስት፣ በሀምሌ 19 መናፈሻ እና አካባቢዎቻቸው፤
እንዲሁም ሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በኦሎምፒያ፣ በፍላሚንጎ፣ በደንበል፣ በኦሮሚያ ቢሮ፣ በሰንሻይን ጀርባ በከፊል፣ በሚኒሊክ ሆስፒታል፣ በአራት ኪሎ፣ በፓርላማ፣ በግቢ ገብርኤል ቤተ-ክርስትያን፣ በዮርዳኖስ ሆቴል፣ በጉድ ሼፐርድ፣ በጣልያን ኤንባሲ፣ በቤላ ሆስፒታል፣ በቤተመንግስት በከፊል ፣ በኬንያ ኤምባሲ፣ በእንግሊዝ ኤምባሲ፣በእስራኤል ኤምባሲ እና አካባቢዎቻቸው፣
በተጨማሪም ማክሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በፔትራም፣ በክራውን ሆቴል፣ በሲ.አር.ቢ.ሲ ቻይና ዋና መስርያ ቤት፣ ካዲስኮ ቀለም ፋብሪካ፣ ኦሮሚያ ውሃ ስራዎች እና አካባቢዎቻቸው፤
በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በምስራቅ ዱቄት ፋብሪካ፣ በሙሉ ሸዋ ስጋ ቤት፣ በቦሌ ማተሚያ ቤት፣ በቦሌ ክራይ ቤቶች፣ በሳሪስ አቦ ቤተ-ክርስትያን፣ በቦሌ ቡልቡላ ኮንደሚኒየም፣ በቡልቡላ ማርያም ማዞርያ እና አካባቢዎቻቸው፤
በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ፡-
• በለገሃር፣ በቴሌ ባር፣ በራስ ሆቴል፣ በአንባሳደር፣ በሸራተን፣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በኮሜርስ፣ በፋና፣ በፖስታ ቤት፣ በጥቁር አንበሳ፣ በደራርቱ ት/ቤት፣ በአየር ሀይል ካንፕ፣ በወርቁ ሰፈር፣ በመንገድ ትራንስፖርት እና አካባቢዎቻቸው፤
በመካከለኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥ በመሆኑ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንድታደረጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡  


የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

Informed 3 days ago

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ  


የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፊታችን ሰኞ ልዩ ስብሰባ ያካሂዳል

Informed 3 days ago

5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባውን የፊታችን ሰኞ እንደሚያካሂድ ምክር ቤቱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በላከው መግለጫ አመልክቷል።
ስብሰባው ዶ/ር አብይ አሕመድ በተገኙበት በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድም ተገልጿል።  


ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.