Share this fact with a friend
Your name
Subject
Your email
Recipient (s) email
አልበርት አንስታይን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ ስሌት ለመቅረፅ ሲሞክር በእጅ ፅሁፍ የሰፈረ ሰነድ በ13 ሚሊዮን ዶላር ተሽጧል።በፓሪስ በሚገኘው የክራይስቲ የጨረታ ቤት ሰነዱ የተሸጠ ሲሆን ዋጋው የሳይንሳዊ ሰነድ ክብረ ወሰን ሰብሯል። የቲዎሬቲካል ፊዚክስ ሊቃውንት የሆነው አንስታይን ታላቅ ሳይንሳዊ ግኝቱን ከሚያሳዩ ሁለት ወረቀቶች መካከል የተሸጠው ሰነድ አንደኛው ነው።እ.ኤ.አ በ2015 ይህ ንድፈ ሀሳብ ከታተመ በኃላ ስለ ቦታ፣ ጊዜ እና ስበት የሰው ልጅ ያለው ግንዛቤ የቀየረ ሆኗል። የሂሳብ ቅጂው የተፃፈው በ1913 እና በ1914 መካካል ባለው ጊዜ ውስጥ አንስታይን እና የስዊዘርላንድ ባልደረባው ሚሼል ቤሶ አማካይነት ነው። የአንስታይን በጣም ጥቂት ማስታወሻዎችን የያዘ ሰው እንደመሆኑ የእጅ ፁሁፉ ተገኝቶ ለዚህ መብቃቱ ያልተለመደ ያደርገዋል ሲል የጨረታ ባለሙያው ቪንሰንት ቤሎይ ተናግሯል። ፅሁፍ በጥቁር እስኪሪብቶ የሰፈረና ንድፈ ሀሳቡን ለማስፈር በተደረገ ጥረት በርካታ ስህተቶች የሚታዩበት ነው።ሰነዱን ማን እንደገዛው ባይገለፅም ባለ 54 ገፅ ስለመሆኑ ይፋ ተደርጓል። የአንስታይን የአንፃራዊነት ፅንሰ ሀሳብ ስለ ስለ ፕላኔቶች ምህዋርና ስለ አፅናፈ ሰማይ ብርሃን የፈነጠቀ ነበር።ባለፈው ግንቦት ወር በአንስታይን የተፃፈው የንድፍ ሀሳብ ታዋቂው E=mc2 የያዘ ሰነድ በ1.2 ሚሊዮን ዶላር መሸጡ ይታወሳል። Via ዳጉ ጆርናል
Message
Share
Reset