More
Have a nice Wednesday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!

"በእጩዎችና በታዛቢዎቹ ላይ ማስፈራርያና ጫና ነበረ" ሳልሳይ ወያነ ትግራይ

Informed 2 weeks ago

Informer:  BBC Amharic
የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) በሰጠው መግለጫ፣ በምርጫው ሂደት በተወዳዳሪዎቹና በታዛቢዎቹ ላይ "ማስፈራርያና ጫና" ይደርስ እንደነበረ አስታወቀ።
ፓርቲው እንዳለው ተገቢ ያልሆኑ ነገሮች ከምርጫው ቀን በፊት አንስቶ ይስተዋሉ እንደነበር ጠቅሶ፤ በዚህም የገዢው ፓርቲ አባላት ከምርጫው በፊት ቤት ለቤት እየዞሩ "ምልክት የምታደርጉት እዚህ ላይ ነው" በማለት በመራጮች ላይ ጫና ሲያሳድሩ እንደነበር ገልጿል።
በተጨማሪም ሳልሳይ ወያነ ትግራይ በመግለጫው ላይ እንዳለው በተወዳዳሪዎቹ እና ታዛቢዎቹ ላይ "ማስፈራርያና ጫና" እንደደረሰም አመልክቷል።
"የወረዳና የቀበሌ መዋቅሮችን በመጠቀም፣ በእጩ ተመራጮቻችን እና ቤተሰቦቻቸው ላይ ማስፈራርያ ይደርስ ነበር፤ በሕዝብ እንደ ጠላት እንዲታዩና እንዲሸማቀቁም ሲደረግ ነበር" ብሏል።ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.