More
ሐሙስ የቀን ቅዱስ, Have a nice Thursday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!

የሰው-ሰራሽ አስተውሎት ተአማኒነት እስከ ምን?

Informed 4 days ago

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ትልቁ ሀሳብ ማሽኖችን እራስ ገዝ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ሰዓት እራሳቸውን በራሳቸው የሚያሽከረክሩ መኪኖች፣ ውሳኔ የሚወስኑ ሮቦቶችን እና ሌሎችንም እንደዛ የሆኑ ማሽኖች እየተመረቱ እና እየተሰሩ ነው፡፡ይሁንና እነዚህን ማሽኖች ምን ያህል ማመን ይቻላል የሚለው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው፡፡
የሰው ልጆች አዕምሮ እንዳላቸው ሁሉ ኒውራል ኔትዎርክ የሰውሰራሽ አስተውሎቶች አዕምሮ ነው፡፡ ይህ መረብ አዕምሮ ለሰው ልጆች የሚሰራውን ሁሉ ለማሽኖች እንዲሰራ የታሰበ ሲሆን በዋናነት ትንበያን ማመንጨት ላይ ትኩረት ያደርጋል፡፡ ይሁንና ይህ ምንጭ ተአማኒነቱ ምን ያህል ነው የሚለው ነገር አሳሳቢ ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል ብናይ የእራስ ገዝ መኪናዎች ፈተና በመንገድ ላይ የሚገጥሟቸውን ነገራት ምንነት ጠንቅቆ ማወቅ አለማወቅ ላይ ነው፤ ማለትም መንገድ እያቋረጠ ያለው ነገር እንስሳ ነው ወይስ ህጻን ልጅ ፣ ይህ አካል ፈጣን እርምጃ ነው ያለው ወይስ ቀርፋፋ ፣ ሌላ መኪና በተሳሳተ አቅጣጫ ቢመጣበትስ ወደየትኛው ለመንዳት ይወስናል እና የትኛው ያነሰ ጉዳት ያመጣል የሚሉትን በሰው ልጆች አዕምሮ ውስጥ የሚወሰኑ ውስበስብ ውሳኔዎችን ለመወሰን ለማሽኖች ቀላል አይሆንም፡፡
ለመኪናው መረጃ አቀባይ ምንጮች ብዙ ናቸው፡፡ የፊት ለፊት ካሜራ፣ የኮምፒውተር እይታ እና ሌሎችም ይህ መኪናው የትኛውን ሴንሰር ማመን እና መቀበል እንዳለበት ግራ እንያጋባው ያደርጋል፡፡ በተለይም የመረጃ መጣረሶች በሚከሰቱበት ሰዓት መኪናው የሚወስነውን ነገር ጠንቆ ማወቅ ይቸገራል፡፡
ይህንን ጉዳይ በተመለከተ እስከዛሬ ድረስ የሰው ሰራሽ አስተውሎቶችን ተአማኒነት የሚለካ ምንም ዓይነት አሰራር እና መሳሪያ የለም የሚሉት የካሊፎርኒያ ዩኒቨርስቲ ተመራማረዎች ምንም እንኳን ስህተት የማሽኖች ብቻ ሳይሆን የሰው ልጆችም መገለጫ ነው ያሉ ሲሆን የሰው ልጆችም የመወሰን ችግር፣ የመዘግየት በሃሪ እና ሌሎችንም የትንበያ እክሎች እንደሚያተናግዱ እናውቃለን ብለዋል፡፡
ይሁንና አሁንም ቢሆን ኒውራል መረብ ላይ እጅግ መልፋት እና የትክክለኝነቱን መጠን ማሰፋት ላይ በትጋት ሊሰራ ይገባል ያሉ ሲሆን በፈረንጆቹ አቆጣጠር በኦገስት31 /2020 ማሽኖች በማያውቁበት እና ግራ በሚጋቡበት ጊዜ አናውቅም ማለት የሚችሉበትን አዲስ አሰራር የፈጠሩ ሲሆን ይህ ሁኔታ በተሳሳቱ ውሳዎች የሚከሰቱ ውድመቶችን ለመከላከል ዓይነተኛ አማራጭ ነው ብለዋል፡፡
ምንጭ፡- ScienceDaily


Click on an image to view it in a separate window

Image size: 92kb Download image.

Image name: ai.jpg


ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.