More
Today is Jummah. Happy Jummah, Happy friday!

Get to know the fact, and the fact itself will set you free!

የዓለም ባንክ 80 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ሰጠ

Informed 18 hours ago

በሚ/ር መ/ቤቱ ሲተገበር የቆየው የሁለተኛ ዙር የግብርና ዕድገት ፕሮግራም ፕሮጀክቶች ማስጨረሻ የሚሆን የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት በዓለም ባንክና በገንዘብ ሚኒስቴር ተፈረመ፡፡ ይህ ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ስምምነት የሚያተኩረው ግብርና ሚኒስቴር በሁለተኛ ግብርና ዕድገት ፕሮግራም በተለያዩ ክልሎች የአርሶ አደሮች ኑሮ እንዲያሻሻል የግብርና ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ፣ የተጨማሪ ገቢ ማገኘት የሚያስችላቸውና የግብርና ምርት ዕሴት ሰንሰለት እንዲጎለብት እየተገበረ ለነበሩ ፕሮጀክቶች ማስጨረሻና የአነስተኛ አርሶ አደሮች የግብርና ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚውልና የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጾል፡፡
የድጋፉ ስምምነቱ የተፈረመው በመንግስት በኩል በክቡር አቶ አህመድ ሺዴ የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትርና በአለም ባንክ በኩል ደግሞ በክቡር ሚስቴር ኦስማን ዲዮን በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ናቸው፡፡
የዓለም ባንክ ግብርና ሚኒስቴር የአነስተኛ አርሶና አርብቶ አደሮች ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና የኑሮ ሁኔታ ለማሻሻል የሚያስችሉና በአጠቃላይ ድህነትን ለመቀነስ የሚያካሂደውን የተለያዩ ዓይነት የልማት ፕሮግራሞች በገንዘብና በቴክኒክ እየደገፈ የሚገኝ መሆኑ ይታወሳል፡፡ONLINE E-BOOKS


Online E-books, Textbooks and related materials.