askwala.com - ማይክሮሶፍት ዋይፋይ ላይ ላጋጠመው የአገልግሎት መቆራረጥ የሚሆን ማዘመኛ መልቀቁን ገለፀ
Header







ማይክሮሶፍት ዋይፋይ ላይ ላጋጠመው የአገልግሎት መቆራረጥ የሚሆን ማዘመኛ መልቀቁን ገለፀ


ማይክሮሶፍት የዊንዶውስ-10 ተጠቃሚዎች የበይነ-መረብ ግንኙነት ለመፍጠር ዋይፋይ በሚከፍቱበት ወቅት የሚፈጠረዉን የዋይፋይ መቆራረጥ የሚቀርፍ ማዘመኛ መልቀቁን ገለጸ፡፡
ከመደበኛዉ የማይክሮሶፍት የደህንነት ዘመና ወቅት በተለየ ሁኔታ የተለቀቀዉ ድንገተኛ ማዘመኛ በዋይፋይ ላይ የሚፈጠሩ የአገልግሎት መቆራረጦችን ለመቅረፍ የሚረዳ መሆኑ ታዉቋል፡፡
ይህ የደህንነት ክፍተት የሚፈጠረዉ "የተለየ ስህተት" ወይም በተለምዶ ብሉ ስክሪን ኦፍ ዴዝ /Blue-Screen of Death/ ዋይፋዩን ከኢንተርኔት ጋር ለምናደርገዉ ግንኙነት በምንከፍትበት ወቅት ሊፈጠር የሚችል ነዉ፡፡
በዚህም የኢንተርኔት ግንኙነት ለመፍጠር ዋይፋይ ፕሮቴክትድ አክሰስ-ሶስት /WiFi Protected Access-3 ልንጠቀም ጥረት በምናደርግበት ጊዜ "ስህተት ስላለ አቁም" የሚል መልዕክት በሰማያዊ ስክሪን ላይ ሊደርሰን እንደሚችል ማይክሮሶፍት አሳውቋል፡፡
ይህ መሰሉ ክስተት ሊያጋጥመን የሚችለው ያቋረጥነውን ዋይፋይ መልሰን ስናገናኝ ወይም ኮምፒውተራችንን ከስሊፕ /Sleep/ ወይም ሀይበርኔሽን /hibernation/ መልሰን ስናስነሳ መሆኑ ታዉቋል፡፡
ሆኖም ብዙዎቹ የዋይፋይ በአሁኑ ሰዓት የሚጠቀሙት የዋይፋይ ፕሮቴክትድ አከሰስ ሁለትን በመሆኑ የተጠበቀዉን ያክል ጉዳት አለመድረሱ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
እርስዎም የዊንዶዉስ-10 ተጠቃሚ ከሆኑ አሁኑኑ የዊንዶዉን በማዘመን ሊደርስ የሚችሉ የአገልግሎት መስተጓጎል እና የደህንነት ክፍተቱን ይጠግኑ፡፡ 

















Short info

× Chat