askwala.com - በታክስ አከፋፈል ላይ ለከፍተኛ የስጋት ደረጃ ውስጥ የሚያስገቡ ጥፋቶች
Header







በታክስ አከፋፈል ላይ ለከፍተኛ የስጋት ደረጃ ውስጥ የሚያስገቡ ጥፋቶች


በታክስ አከፋፈል ላይ ለከፍተኛ የስጋት ደረጃ ውስጥ የሚያስገቡ ጥፋቶች
👉 ትክክለኛውን ክፍያ እና በወቅቱ አለመክፈል፣
👉 የግብር ውሳኔ ማስታወቂያ ከደረሳቸው በኃላ ክፍያ አለመፈጸም፣
👉 በጊዜ ስምምነት ለመክፈል ስምምነት ከገቡ በኃላ ማቋረጥ፣
👉 በግብር ተመላሽ ወቅት የሚቀርቡ የታክስ መጠን በስህተት ወይንም ሆን ብሎ በትክክል ያለማቅረብ፣
👉 አግባብ ያልሆነ ተመላሽ መጠየቅ፣
👉 ግብር የመክፈል አቅም ያላቸው ግብር ከፋዮች በግብር ሥርዓት መረብ ውስጥ ያለመታቀፍ፣
የስጋት ደረጃን ለማሻሻል የሚረዱ ሁኔታዎች
• በግብር ከፋይነት መመዝገብ እና በግብር ስርዓቱ መታቀፍ
• ትክክለኛውን መረጃ ለግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ማሳወቅ
• ለግብር አወሳሰን የሚረዱ የሂሳብ ሰነዶችን በአግባቡ መያዝ
• የሚጠበቀውን ግብር በወቅቱ ማስታወቅ እና መክፈል
• የተቀመጡ የተመላሽ፣ ኪሳራ የማሳወቅ መብቶችን በአግባብ መጠቀም
የስጋት ደረጃን ማሻሻል ምን ጠቀሜታ አለው?
• ከግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በማሻሻል ገቢ በወቅቱ እና በትክክል ተሰብስቦ ለስራ እንዲውል ያግዛል፤
• የህግ ማስከበር ወጪዎችን ይቀንሳል፤
• ግብር ከፋዩም ሆነ ግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ስራቸው ላይ ላይ በትኩረት እንዲሰሩ በማድረግ ምቹ አሰራር ይፈጥራል፤
• ተቋሙ ለተሻለ የህግ ተገዢነት ላላቸው ግብር ከፋዮች ልዩ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ በዚህ ደረጃ ያሉ ግብር ከፋዮች ያለ ወረፋ ይስተናዳሉ፤ በሌሎች መስሪያ ቤቶችም የቅድሚያ አገልግሎት እንዲያገኙ ሁኔታዎች እየተመቻቹ በመሆኑ ከአላስፈላጊ ጊዜና ገንዘብ ብክነት ይድናሉ፡፡ 

















Short info

× Chat