askwala.com - ኤልክትሪክን ለበረራ በ2035
Header







ኤልክትሪክን ለበረራ በ2035

Image name: Electric for flight in 2035.jpg

ናሳ በኤልክትሪክ የሚሰሩ አውሮፕላኖችን ለመስራት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ከአቪየሽን ኢንዱስትሪው ጋር በመሆን እየሰራ ነው፡፡ እቅዳቸውንም እውን ለማድረግ 2035 የሚጠበቅ አመት ነው፡፡ የብዙ ሀገራትና ተቋማት አይን ወደ ማርስ እያማተረ ባለበት በዚህ ወቅት ናሳ ከአካባቢ ጋር የተስማማ ወደ ምድር የመመለሻ መነገድ እየፈለገ ነው፡፡ የህዋ ምርምር ተቋሙ ከሌሎች የአቪየሽን ኢንዱስትሪው ተቋማት ጋር በመተባበር ለወደፊቱ የአየር ትራንስፖር የኤሌክትሪክ ሀይልን ለመጠቀም የሚያስችል የዲዛይንና የሞዴሊንግ ስራ እየሰራ ነው፡፡
ይህ ምርምር በሀይል ቁጠባ እና ከካርቦንና ናይትሮጅን ልቀት ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ወጥነት ያለው የአየር ጉዞ ጉዳይ ለአምራቾችና ለተቆጣጣሪዎች ቀዳሚ አጀንዳ ሆኗል፡፡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በ2019 ብቻ በተደረጉ በረራዎች 915 ሚሊዮን ቶን ካርቦን ዳይ ኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር ተለቋል፡፡ የኮቪድ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ የተቋረጠው በረራ ከካርቦን ልቀት ጋር በተያያዘ ለከባቢ አየሩ እፎይታ እንደሰጠ መነገሩ የማይረሳ ነው፡፡
አሁን ላይ ሁሉም በረራዎች ወደ ቀድሞ ይዞታቸው እየተመለሱ በመሆናቸው ልቀቱ እንደገና ማንሰራራት ጀምሯል፡፡ አሁን ላይ የአውሮፓ ህብረት የበረራ ደህንነት ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ከከባቢ አየር ጋር የተስማሙ በረራዎችን ደረጃ የሚያወጣበት እቅድን እያሰናዳ ነው፡፡ ናሳም ከባይደን መንግስት ጋር በጉዳዩ ላይ ለመምከር ከፍተኛ የአየር ንብረት ጉዳዮች አማካሪውን ሀላፊነት ሰጥቷል፡፡ 




© Engadget   













Short info

× Chat