askwala.com - በአውሮፓ የመጀመሪያ የሆነው አሽከርካሪ አልባ የህዝብ ትራንስፖር
Header







በአውሮፓ የመጀመሪያ የሆነው አሽከርካሪ አልባ የህዝብ ትራንስፖር

Image name: Autonomous_vehicle.jpg

አዲስ ራስ ነድ ወይም አሽከርካሪ አልባ በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶቢስ በደቡባዊ ስፔን፣ ማላጋ ስራ መጀመሩ ተሰምቷል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ስራ እንደጀመረ የተነገረለት የህዝብ ማመላለሻ አውቶቢሱ የተለያዩ ሴንሰሮችና ካሜረዎች የተገጠሙለት ሲሆን 8 ኪሎሜትር ያክል ርቀት የሚሸፍነውን ከማላጋ ወደብ እስከ መሐል ከተማ ድረስ ያለውን በማካለል አገልግሎት ይሰጣል፡፡ እስካሁን በታቀደለትም በቀን ስድስት ዙሮችን ደርሶ መልስ ይሰራል፡፡
የስፔን ደቡባዊ ግዛት የትራንስፖርት ኩባንያ የሆነው አቫንዛ ስራ አስኪያጅ የሆነው ራፌል ዱረባን አውቶቢሱ ምንጊዜም የት እንዳለ እና በዙሪያው ያሉትን ሁኔታዎች በሙሉ እንደሚያውቅ ተናግረዋል፡፡ አክለውም መኪናው ከትራፊክ የመንገድ ዳር መብራቶች ጋር እንዲግባባ ተደርጎ የተሰራ በመሆኑ ህግ አክባሪ ነው ብለዋል፡፡ በጉዞ ወቅትም የተለያዩ ውሳኔዎችን ለመወሰን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ይጠቀማል፡፡
ይህ በስፔኑ አይሪዛር የተሰራው አውቶቢስ እንደሌሎች መደበኛ አውቶቢሶች 12 ሜትር የሚረዝም ሲሆን በአንድ ጊዜ 60 ሰዎችን የመያዝ አቅም አለው፡፡ በአውሮፓ ሌሎች የተለያዩ አሽከርካሪ አልባ መኪኖች ያሉ ቢሆንም በዚህ መጠን ከሌሎች መደበኛ መኪኖች ጋር አንድ ላይ መንቀሳቀስ የሚችሉ ግን እስካሁን ወደ መስመር አልወጡም፡፡
ምንም እንኳን ቴክኖሎጂው መኪናውን ያለ አሽከርካሪ ማንቀሳቀስ የሚችል ቢሆንም የስፔን ህግ አንድ መኪና ያለ አሽከርካሪ እንዲንቀሳቀስ የሚፈቅድ ባለመሆኑ ያለ ስራም ቢሆን አንድ ሰው የአሽከርካሪው ወንበር ላይ ይቀመጣል፡፡ ይህ በስፔን መንግስት የገንዘብ ድጋፍ የተሰራው ፕሮጀክት የሀገሪቱ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተሳተግፎ አድርገውበተል፡፡ 

















Short info

× Chat