askwala.com - የካርጎ ማጓጓዝ አገልግሎት ቀድሞ ወደነበረበት ተመልሷል
Header







የካርጎ ማጓጓዝ አገልግሎት ቀድሞ ወደነበረበት ተመልሷል


የአየር ላይ እቃ ማጓጓዝ አገልግሎት የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ከመምጣቱ በፊት ወደነበረበት ደረጃ መመለሱን አለም ዓቀፉ የአየር ትራንፖርት ማህበር (IATA) አስታወቀ፡፡ እንደ ማህበሩ ከሆነ የሚጓጓዘው ካርጎ መጠን በሚሄድበት ርቀት ሲሰላ ለካርጎ አገልግሎት ያለው ፍላጎት በአውሮፓውያኑ ወርሃ ጥር 2019 ከነበረበት አሁን ላይ በ1.1 አድጎ ተገኝቷል፡፡ ሆኖም አየር መንገዶች ከህዝብ ማመላለስ ጎን ለጎን የካርጎ አገልግሎትንም የሚሰጡ አውሮፕላኖችን በወረርሺኙ ሳብያ ከስራ ውጭ ማድረጋቸውን ተከትሎ የካርጎ አገልግሎት የመስጠት አቅሙ በዛው በጥር 2019 እንዲሁም በቅርቡ ታህሳስ 2020 ላይ ከነበረበት በ20 እና 5 በመቶ ወርዶ ተገኝቷል፡፡
ማህበሩ ስለ እቃ ማጓጓዝ አገልግሎቱ ይህን ቢልም የመንገደኞች ማጓጓዙ ግን አሁንም በቁልቁለት መንገድ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል፡፡ ቀደሞ ከአየር መንገዶች ገቢ ውስጥ የ85 በመቶ ድርሻን ይይዝ የነበረው መንገደኞችን የማጓጓዝ አገልግሎቱ አሁን ላይ በየ ኪሎ ሜትሩ የሚያመነጨው ገቢ ሲሰላ በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ በ72 በመቶ ወርዷል፡፡ ይህም ባሳለፍነው የፈረንጆች ዓመት መባቻ ላይ ሪፖርት ከተደረገው የ69.7 በመቶ ዓመታዊ ቅናሽም የባሰ ነው፡፡
ባለፈው ወር አየር መንገዶች በወረርሺኙ ምክንያት ብዙ ነገሮችን እንዳይሆኑ አድርጎ በተሰናበተን 2020 የ510 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣታቸውን አለም ዓቀፉ የአየር ትራንፖርት ማህበር ሪፖርት አድርጎ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ሀገራት እየተሰራጩ ያሉት የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባቶች ኢንዱስትሪው ከ2021 አጋማሽ በኋላ በፍጥነት እንዲያገግም እንደሚያስችሉት ተስፋ አድርጓል፡፡ 




© Tech Xplore   













Short info

× Chat