askwala.com - የሸማቾችን ባህሪና ፍላጎት የሚተነትነው ሮቦት
Header







የሸማቾችን ባህሪና ፍላጎት የሚተነትነው ሮቦት

Image name: A robot that analyzes shoppers behavior.jpg

በእለት ከእለት የሰዎች የንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የራሱ የሆነ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡ ስኮልቴክ በሚባለው የሮቦት ማበልጸጊያ ማዕከል የሚሰሩ ተመራማሪዎች በተለያዩ መደብሮች ውስጥ በመሆን የደንበኞችን ባህሪ ማጥናትና መተንተን የሚችል ሮቦት መስራታቸው ተነግሯል፡፡ ይህ ሮቦት በትልልቅ የገበያ ቦታዎች ላይ ደንበኞች በፈለጉት ሰዓት የፈለጉትን ማንኛንውም እቃ እንዲሸምቱ እና የሚፈልጉትን እቃ ትክክለኛ መገኛ ቦታ እንዲሁም ዋጋ ማሳወቅ የሚችል ነው፡፡
ሮቦቱ በ0.3 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ የተለያዩ ታጎችን ማንበብ የሚችል ሲሆን ሸማቾች አዘውትረው የሚጎበኟቸውን ቦታዎች በመመዝገብ ትርፍ የሚያስገኙ የተለያዩ ሸቀጦችን ነጋዴዎች እንዲያስቀምጡ መረጃ ይሰጣል፡፡ የስኮልቴክ ማዕከሉ አልክሳንደር ፕተሮቭስኪ ሮቦታችን የሸማቾችን ፍላጎት በማጥናት ዝርዝር መረጃዎችን የሚሰጥ ሲሆን የሬዲዮ ፍሪኩየንሲ መለያን (RFID) ማንበብ የሚችል ነው ሲል ተናግሯል፡፡
በዚህ ቴክኖሎጂ አማካኝነት የሚገኝ መረጃ የሽያጭ ትርፎችን ከፍ ለማድረግ እና ወቅታዊ የፍላጎት መገለጫዎችን ለመተንበይ እንዲሁም ሸቀጣ ሸቀጦቹን በማዛወር ረገድ በጣም አስፈላጊ ናቸው፡፡ በማበልጸግ ሂደቱም በአንድ ትልቅ መደብር ውስጥ በተከታታይ ለ10 ወራት ጥናቶች የተካሄዱ ሲሆን በሰዎች በሚሰበሰብ መረጃ ስህተት ምክንያት የሚፈጠርን ስህተት በከፍተኛ መጠን መቀነስ ያስችላል ተብሎለታል፡፡ 




© Tech Xplore   













Short info

× Chat