askwala.com - በትግራይ ክልል አሮጌ ብር መቀየርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ማሳሰቢያ
Header







በትግራይ ክልል አሮጌ ብር መቀየርን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ ማሳሰቢያ


እንደሚታወቀው ከትግራይ ክልል በስተቀር በመላ ሀገሪቱ አሮጌዉን ብር በአዲስ የመቀየሩ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በነበረዉ የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ሳቢያ ብር የመቀየሩ ሂደት ተስተጓጉሎ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ከ100ሺ ብር በታች አሮጌ ብር ያላቸዉ እንዲቀይሩ የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ መፈቀዱ ይታወሳል፡፡
እስካሁን ባለዉ በክልሉ ይቀየራል ተብሎ የሚታሰበዉ አሮጌ የገንዘብ መጠን በአብዛኛዉ የተቀየረ በመሆኑና የሚቀየረዉ አሮጌ ገንዘብ መጠንም በጣም ጥቂት መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በክልሉ የተጀመረዉን ብር የመቀየር ሥራ ለማጠናቀቅ የጊዜ ገደብ ማስቀመጡ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በዚህ መሠረት ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 10 ቀን 2013 á‹“/ም ባሉ ተጨማሪ ቀናት አሮጌዉ ብር ሙሉ በሙሉ እንዲቀየር፣ ይህ ማሳሰቢያ የመጨረሻ መሆኑ ታዉቆ የባንክ ቅርንጫፍ በተከፈተባቸዉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በመሄድ ይኸዉ ተግባራዊ እንዲደረግ፣ ባንኮችም በዚሁ መሠረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከአደራ ጭምር እናሳስባለን፡፡ 

















Short info

× Chat