askwala.com - ተሻሽሎ የቀረበው ቀጣዩ ትውልድ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ
Header







ተሻሽሎ የቀረበው ቀጣዩ ትውልድ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ

Image name: Solar panel.jpg

ተመራማሪዎች የቀጣዩን ትውልድ የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፍ ብቃት አሻሽለው እንዳቀረቡ ተነገረ፡፡ ሲልከን እየተባለ የሚታወቀውን የፀሐይ ሐይል መሰብሰቢያ ንጣፍ ለመስራት የሚያገለግለውን ቁስ ቀስ በቀስ እየተካ ያለው ቁስ ፕሮቭስካይት ይባላል፡፡ ይህ ቁስ ተጣጣፊ የሆነ እንዲሁም በቀላል ዋጋ ሊገኝ የሚችል ንጣፍን ለመስራት የሚያስችል ቢሆንም የፀሐይ ሐይልን ወደ ኤሌክትሪክ ሐይል በመቀየር በኩል ግን እጥረት ይስተዋልበታል፡፡
ተመራማሪዎች የዚህን ቁስ ሐይል የማመንጨት ብቃት ከ20 እስከ 22 በመቶ የሚያሻሽል አዲስ ስልትን መቀየሳቸው ተሰምቷል፡፡ ይህንንም ማድረግ የቻሉት ቲን ዳይኦክሳይድ የተባለ አስተላላፊ ንጣፍን በመጨመር እንደሆነ ተመራማሪዎቹ አሳውቀዋል፡፡
የፀሐይ ሐይል ንጣፉን ሀይል የማመንጨት ብቃቱን ለመጨመር ከንብርብሮቹ አንዱንና መካከለኛውን ከፍተኛ አስተላላፊ የሆነ ንጣፍ በማድረግ ጭምር ነው፡፡ የሐይል መሰብሰቢያውን ብቃት ለመጨመር ተመራማሪዎቹ የተጠቀሙት ዘዴ ኬሚካል ባዝ ዲፖዚሽን ተሰኝቷል፡፡ 

















Short info

× Chat