askwala.com - ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተላከ ግልጽ ደብዳቤ
Header







ለፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተላከ ግልጽ ደብዳቤ


ክቡር ፕሬዝዳንት
ላለፉት አመታት እርስዎን እንደ ሴናተር፣ ምክትል ፕሬዝዳንትና አሁን ደግሞ እንደ ፕሬዝዳንትም ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውም እንደናውቅዎ አድርገውናል።
እአአ በፌብሩዋሪ 27/2021 ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የወጣው መግለጫና እሱን ተከትሎ በመስሪያቤቱ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት በእኔ እምነት የሚገነቡ ናቸው ብዬ አላምንም።
ምክንያቴንም እንደሚከተለው አስረዳለሁ፤
አገሬን ጥዬ ስደት የወጣሁት እአአ በ2005 ህወሓት ያለምንም ልዩነት ሴቶችን እና ህጻናትን ጭምር መግደል ሲጀምርና የእኔም ቤተሰብ የሆነ የ16 አመት ህጻን መኪናዬ ውስጥ በመንግስት ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ሲገደል ራሴን ለማትረፍ ነበር።
እኔ ከዚህ ግድያ ባመልጥም በወቅቱ በርካታ ጓደኞቼ ለእስር ተዳርገዋል፤ 40 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችም ወደወህኒ ተግዘዋል።
የህወሓት ግፍ ይህ ብቻ አይደለም፤ ከብዙው በጥቂቱ ልጥቀስልዎ፤
• እአአ በዲሴምበር 13/2003 ላይ 450 የአኙዋክ ብሄር ተወላጅ የሆኑ
ኢትዮጵያዊያን በመንግስት ወታደሮች በጋንቤላ ተጨፍጭፈዋል፤
• እአአ በ2006 እና 2007 በኦጋዴን በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን
በህወሓት ሃይሎች ተገድለዋል፤
• በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ እስር ቤቶች በርካቶች
ታስረዋል፤ አካላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፤ በመራቢያ አካላቸው ላይ
ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ እንዳይወልዱ ተደርገዋል፤
• በወልቃይት ጸገዴ በርካቶች በህይወት እያሉ ተቀብረዋል፤
• ብዙዎች የራሳቸውን የቀብር ጉድጓድ እንዲቆፍሩ ተደርገው
ተገድለዋል፤ ወደ ገደል ተወርውረዋል፤
• በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በህወሓት ዘመን ላለፉት 27 አመታት እስር ቤት
ሆና ቆይታለች፤
ከብዙ አመታት የህዝብ ተቃውሞ በኋላ የለውጥ ማዕበል በኢትዮጵያ ነፍሶ እአአ በኤምሪል 2018 ለውጥ መጥቷል። ከዚህ ለውጥ ማግስት ጀምሮ በአገሪቷ የተከሰቱ መፈናቀሎች፣ ማንነትን መሰረት አድርገው የተፈጸሙ ግድያዎች በሙሉ አቀነባባሪውና ድጋፍ አድራጊው ህወሓትና ጥቂት አመራሮቹ ነበሩ።
ህወሓት ይህ አልበቃው ብሎ እአአ ኖቬንበር 4/2020 በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ዘግናኝ ጥቃት ፈጽሟል።
ውድ ፕሬዝዳንት፤
እርስዎም ሆኑ ማንኛውም የሰው ልጅ ማንም ሰው በዘሩ በሃይማኖቱ በዜግነቱና በማንነቱ ምክንያት መድሎ ሳይደርስበት መከበር አለበት ብለው እንሚያምኑት ሁሉም እኔም በተመሳሳይ ለእነዚህ ማንነቶች ይገደኛል። ስለሆነም እርስዎንና አስተዳደርዎን የምጠይቀው፤
- ሁሉንም ወገን እኩል እንዲያዩና እንዲያዳምጡ እንጂ አንዱ ወገን አብዝቶ ስለጮሀ ወይንም በአግባቡ ተደራጅቶ ድምጹን ስላሰማ የበለጠ ሊደመጥ አይገባውም፤
- ከሁሉም አቅጣጫ እውነታዎችን እንዲመለከቱ እጠይቃለሁ፤
- በማይካድራ ምን እንደተፈጸመም እንዲመለከቱም በትህትና
እጠይቅዎታለሁ።
ወርቄ ብርዬ ረታ ትውልደ ኢትዮጵያዊ 

















Short info

× Chat