askwala.com - በአንድ ቀን ሁለት ጊዜ የኮቪድ ክትባት የተከተበው የ91 ዓመት አዛውንት
Header







በአንድ ቀን ሁለት ጊዜ የኮቪድ ክትባት የተከተበው የ91 ዓመት አዛውንት


በኦሃዩ አንድ የ91 ዓመት አዛውንት በአጋጣሚ በአንድ ቀን ውስጥ 2 ጊዜ በወሰዱት የኮቪድ 19 ክትባት ምክንያት ከፍተኛ መንቀጥቀጥ (ሾክ) እንደገጠማቸው ተነገረ፡፡ እኒህ ቪክተር ስሚዝ የተባሉ ግለሰብ የመጀመሪያውን ክትባት በፈረንጆቹ ጥር 22 ላይ ወስደው ነበር፡፡ በዚህም ወቅት የክትባቱ የታወቁ የጎንዮሽ ችግሮች በአዛውንቱ ላይ በመከሰታቸው ራሳቸውን ስተው ወድቀዋል፡፡ ከዚያም ጀምስታውን ወደሚባለው የማገገሚያ ማዕከል ተወሰዱ፡፡
በየካቲት 25 በኦሃዩ በሚገኘው የማገገሚያ ማዕከል የነበሩት አዛውንቱ ስሚዝ ሁለተኘውን ክትባት የሚወስዱበት ጊዜ በመድረሱ ወደ ክትባት ማዕከሉ ተወሰዱ፡፡ በዚህ ወቅት ዳውን ስሚዝ የተባለችው ልጃቸው አዛውንቱን እንዳገኘቻቸውና በጥሩ ጤንነት ላይ መሆናቸውን እንዳስተዋለች ተናግራለች፡፡ በዚሁ በተመሳሳይ ቀን በማገገሚያ ማዕከሉ ሌሎች ታካሚዎች ክትባታቸውን እየወሰዱ እንደነበር የሚገልጸው የመረጃ ምንጫችን በክትባት ቦታው ተመሳሳይ ስም ያላቸው ታካሚዎች መደበላለቅ ተፈጥሮ እንደነበር ይናገራል፡፡
አዛውንቱም ለዕለቱ የተመደበላቸውን ሁለተኛውን ክትባት ከወሰዱ ከ4 ሰዓታት በኋላ ሶስተኛ ክትባት በስህተት እንዲወስዱ ተደረጉ፡፡ እነዚህ ክትባቶች ቢያንስ በሶስት ወይም በአራት ሳምንተት ልዩነት መሰጠት የሚገባቸው ነበሩ፡፡ በእለቱ ቪክቶር ስሚዝ የተባሉት አዛውንት ሁለት ክትባቶችን እንደወሰዱ ሲደረስበት የህክምና ባለሙያዎችና አስታማሚዎቻቸው ወደ ክፍላቸው ሄዱ፡፡ ይሁን እንጂ በእለቱ በወሰዷቸው ክትባቶች ምክንያት ከፍተኛ የሰውነት መንቀጥቀጥ እና የደም መውረድ አጋጥሟቸው ነበር፡፡
ሀኪሞቹ በወቅቱ ተስፋ እንደቆረጡና ሁኔታውን አዛውንቱ ሊቋቋሙት እንደማይችሉ እንደነገሯት የምትናገረው ልጃቸው እሳቸው ግን በቀላሉ የሚበገሩ አልነበሩም፡፡ እንደ እድል ሆኖ ከቆይታ በኋላ የአዛውንቱ ጤና መሻሻል ማሳየት ጀምሯል፡፡ የማገገሚያ ማዕከሉ አስተባባሪዎች ችግሩ እንዴት ሊፈጠር እንደቻለ እየመረመሩ እንደሆነና ለአዛውንቱም ፍጹም ጤናን እንደሚመኙ ተናግረዋል፡፡ 

















Short info

× Chat