askwala.com - የደህንነት ስጋት ምንጭ የሆነው የደህንነት ካሜራ
Header







የደህንነት ስጋት ምንጭ የሆነው የደህንነት ካሜራ

Image name: security camera.jpg

የደህንነት ቁጥጥር እንዲያደርጉ በየተቋማቱ የተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች ለሀከሮች ተጋላጭ እየሆኑ በመምጣታቸው ተቋማት ስጋት ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ ተባለ፡፡ እነዚህ የኮምፒውተር ጠላፊዎች የደህንነት ካሜራዎችን ሲስተም ሰብረው በመግባት ሆስፒታሎችን፣ ትምህርት ቤቶችን፣ ፋብሪካዎችን፣ እስር ቤቶችንና ሌሎች ተቋማትን ማጥቃት መቻላቸውን እየተናገሩ ነው፡፡
አንድ ራሱን APT-69420 አርሰን ካትስ ብሎ የሚጠራ የሀከሮች ቡድን ከአሶሺየትድ ፕሬስ ጋር በኦንላይን አደረገው በተባለው ውይይት ነገሩን በአላማ ሳይሆን ለመዝናናት በሚል እንደሰሩት ተናግረዋል፡፡ በዚህ መልኩ የተጀመረው ስራ አሁን ላይ በሺዎችና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የደህንነት ካሜራዎችን መቆጣጠር እስከመቻል መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡
በ2012 በኒውታውን በሚገኘው የሳንዲሁክ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 26 ተማሪዎችና 6 መምህራን የትምህርት ቤቱ የውስጥና የውጭ የደህንነት ካሜራዎች ሃክ በመደረጋቸው ምክንያት ተገድለዋል፡፡ በሳንፍራንሲስኮ የሚገኙ ተቋማት በግቢያቸውና በየቢሮዎቹ የተገጠሙ የደህንነት ካሜራዎች በመጠለፋቸው ተጨማሪ ኪሳራ ከመድረሱ በፊት አገልግሎታቸውን እያቋረጡ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ለምሳሌ በዚሁ ከተማ የሚገኝ አንድ ኦክታ የተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ በቢሮ መግቢያዎች የገጠማቸው አምስት ካሜራዎች በሀከሮች በመታዎቃቸው እንዳነሳቸው ተናግሯል፡፡
የሳይበር ደህንነት ሙያተኞችን ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ እንደሆነና ተቋማት የደህንነት ካሜራዎቻቸውን እያንዳንዱን እንቅስቃሴ በንቃት መከታተል አለባቸው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ 

















Short info

× Chat