askwala.com - ሀገርአቀፍ የኮቪድ-19 የክትባት ማስጀመሪያ መርሃግብር በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል
Header







ሀገርአቀፍ የኮቪድ-19 የክትባት ማስጀመሪያ መርሃግብር በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች በዛሬው እለት በይፋ ተጀምሯል


በፌደራል ደረጃ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ በኤካ ኮተቤ የኮቪድ ማእከል በመገኝት የክትባት መርሃግብሩን አስጀምረዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና ሚኒስትር ዴኤታ ሳህረላ አብዲላሂ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ በመገኘት ፕሮግራሙን ያስጀመሩ ሲሆን ሚኒስትር ዴኤታ አለምጸሀይ ፓውሎስ በሀረር ከተማ በመኘት እንዲሁም የክልል ርእሳነ መስተዳድሮች፣ የክልል ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የክትባት መርሀግብሩን በይፋ አስጀምረዋል፡፡
ክትባቱን ይበልጥ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች፣ እድሜያቸው ከ65 አመት እድሜ በላይ እና ተጓዳኝ ህመም ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን እንዲያገኙ ደረጃ በደረጃ ለመከተብ መርሀግብር ተዘጋጅቶ እየተሰራ ይገኛል።
ቀደም ሲል የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ህብረተሰብን በማሳተፍ የተለያዩ መከላከያ ምክሮች እየተተገበሩ ሲሆን ነገር ግን በሚታየው ከፍተኛ መዘናጋት በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ኮቪድ-19 አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ሁኔታው ተባባሶ ወደማንወጣው ደረጃ ከመድረሱ በፊት እንዲሁም ክትባት መገኘት ማለት ጥንቃቄን ማቆም ማለት እንዳለሆነ ተገንዝቦ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኝ ግለሰብ ፤ ቤተሰብ ፤ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፤ የሐይማኖት ተቋማት ፣ ሲቪክ ማህበራት ፤ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ፤ የጤና ባለሙያዎች ፤ መምህራንና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ማስክ ማድረግ ፣ የእጃቸውን ንጽህና በተደጋጋሚ መጠበቅና በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ ተገቢውን የጥንቃቄ መንገዶችን በመተግበር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች በጋራ እንድንከላከል እናሳስባለን። 

















Short info

× Chat