askwala.com - አስከ ታህሳስ 30 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ 20% የሚሆኑ ዜጎች የኮቪድ 19 ክትባት ለመከተብ እየተሰራ ነው
Header







አስከ ታህሳስ 30 2014 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ 20% የሚሆኑ ዜጎች የኮቪድ 19 ክትባት ለመከተብ እየተሰራ ነው


የጤና ሚኒትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጃ ዱጉማ ባሳለፍነው ቅዳሜ በኤካ ኮተቤ ጠቅላላ ሆስፒታል በተዘጋጀው በብሄራዊ የኮቪድ-19 የክትባት ማስጀመሪያ መርሃግብር ላይ እንደተናገሩት የጤና ሚኒስቴር ክትባቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደረጃ በደረጃ ለመስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እያጠናቀቀ መሆኑን ጭምር ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እስከ መጭው ታህሳስ 2014 ዓ.ም ድረስ 20 በመቶ የሚሆነውን ህዝቧን ለመከተብ ማቀዷን የጤና ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡የኢትዮጵያ መንግስት በመጀመሪያ ዙር ኮቫክስ ከተሰኝ 2.2 ሚሊዮን ክትባት መረከቡ ይታወሳል፡፡
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመሩንና በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ የሚታመሙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት ከፍ እያለ መሆኑን ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ አስታውሰው አሁንም ህብረተሰባችን ቀደም ሲል ሲደረጉ የነበሩ የጥንቃቄ እርምጃዎቸን በእጅጉ ተግበራዊ ሊያደር ይገባል ብለዋል፡፡
በእለቱ በክብር እግድነት የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ á‹¶/ር ኢንጂነር ጌታሁን መኩርያ በበኩላቸው ኮቪድ 19 የማህበረሰባችን የጤና ስጋት በመሆኑ ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሁላችንም በቅንጅት ልንሰራ ይገባ ያሉ ሲሆን እስካሁን ለተደረጉት የመከላከልና የአገልግት ተግበራትም ጤና ባለሙዎችንና ሌሎችንም አላካት አመስግነዋል፡፡ 

















Short info

× Chat