askwala.com - የቴክኖሎጂ ሃብትን በትምህርት ተቋማት ማስፋፋት
Header







የቴክኖሎጂ ሃብትን በትምህርት ተቋማት ማስፋፋት

Image name: 160999455_3791980957576628_3391370549989027833_n.jpg

በሳይንስና ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ እና በቴክኖሎጂ ሽግግርና ልማት ዘርፍ ውስጥ የቴክኖሎጂ ፍላጎትን መለየት ቀዳሚው ተግባር ነው፡፡ አግባብነት ያላቸውን የቴክኖሎጂ ተዛማጅ መረጃዎችን በማደራጀትና በመተንተን አገልግሎት መስጠት ሌላኛው ወሳኛ ተግባር ነው፡፡ ቴክኖሎጂዎችን ለመቅዳት ወይም ለመላመድ እንዲያስችል የድጋፍ ስርዓት መዘርጋት፣ መደገፍና መከታተልም ያስፈልጋል፡፡ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሀብት አቅምን ለመገንባት የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ባላቸው ዘርፎች የምርምር ማዕከላትን የማቋቋም፣ የምርምር መሰረተ ልማትን የማሟላትና የምርምር ቴክኖሎጂ ፕሮጀክቶችን መደገፍ አንዱ መንገድ ነው፡፡
የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሀብትም አቅም ለመገንባት ውጤታማ የሆኑ የውጭ ቴክኖሎጂዎች ለማፈላለግ፣ ለመምረጥ፣ ለማስገባት፣ ለማላመድና አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችል የቴክኖሎጂ ሽግግር ዕቅድ ማዘጋጀት እና ሀገራትን የምርታማነት አቅም መፍጠር፣ የህዋ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ለልማት መጠቀም የሚያስችል አቅም መገንባት፣ የሳይንስና ቴከኖሎጂ ኢኖቬሽን መረጃዎችን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በማሰባሰብ በማደራጀት በመተንተን ለቴክኖሎጂ ሀብት ሽግግር ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማስቻል እና መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች የምርምር ተቋም እንዲያቋቁሙ ማበረታታት ለቴክኖሎጂ ሀብት ማደግ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛዎች ጨምሮ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚሰሯቸው ተግባራት መካከል አንዱና ዋንኛው ችግር ፈቺ የሆነ ቴክኖሎጂ ውጤቶችን ማምረትና የጥናትና ምርምር ማካሄድ ሲሆን የቴክኖሎጂ ውጤቶችንም ለማህበረሰቡ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የትምህርት ተቋማትን በቴክኖሎጂ ሀብት ማሳደግ ይቻላል፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለመተግበር ማህበረሰቡ በማህበረሰባዊ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ቴክኖሎጂን በሀገራችን በሁሉም የስራ ዘርፍ ማዕቀፍ ውስጥ እንዲካተትና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ከሌሎች ሀገሮች ልምድ በመውሰድ በሀገራችን የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ የሰው ሀብታቸውን በቴክኖሎጂ ቀና ለማድረግ ኃይልን ለቴክኖሎጂ ለውጥ ማዋል ያስፈልጋል፡፡
የትምህርትና የቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት መገንባትና የተቀናጀ መሪነትን እና አቅጣጫ ሰጪነቱን ሚና መጫወት ይኖርበታል፡፡ በዚህም ሂደት ፍትሃዊ፣ ጥራትና አግባብነቱ የተጠበቀ የትምህርት ተደራሽነትን ለማምጣት የትምህርትና የቴክኖሎጂ ልማት ሰራዊት መገንባት ያስፈልጋል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚከናወኑ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሱን አገልግሎት ለውጥ ለማሳደግ ሊያመጡ የሚችሉ ጥናቶችና ምክረ ሀሳቦችን እንደመነሻ ለመጠቀም በመማር ማስተማር፣ በጥናት እና ምርምር በማህበረሰብ አገልግሎት እና በቴክኖለጂ ሽግግር የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት የቴክኖሎጂ ሽግግሩን አፈፀፃሞችን ወደላቀ ደረጃ መግፋት ያስፈልጋል፡፡
የቴክኖሎጂ ውጤቶች አጠቃቀምና ሸግግሩን ለማሻሻል የብሔራዊ የምርምር ቴክኖሎጂን አገልግሎት አሰጣጥን በማጠናከር በሁሉም ደረጃ በሚገኙ በቴክኖሎጂ ምርምር አቅማቸውን ለማሳደግ እንዲችሉ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትኩረት መስጠትም አንዱ ለቴክኖሎጂ ሐብት እድገትና ለቴክኖሎጂ ሽግግር አስተዋፅኦ አለው፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቴክኖሎጂን የመቅዳት፣ የማላመድና የማሸጋገር ሂደት እንዲተገብሩ መስራት የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግ እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥም እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ 




© Innovation Management   













Short info

× Chat