askwala.com - በ “CBE Birr” /707070 ላይ/ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ለመክፈል ለደንበኞች የተዘጋጀ የአጠቃቀም መመሪያ
Header







በ “CBE Birr” /707070 ላይ/ ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ለመክፈል ለደንበኞች የተዘጋጀ የአጠቃቀም መመሪያ


ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆን የድህረ ክፍያ ቆጣሪ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲፈፅሙ የኦንላይን ዲጅታል የክፍያ ስርዓት ተግባራዊ መደረጉ ይታወቃል፡፡
በዚሁ መሰረት ከቀረቡት 5 በላይ አማራጮች አንዱ የሆነው የ “CBE Birr” አገልግሎትን ለመጠቀም ሁለት አይነት መንገድ ቀረቧል፡፡ ይህም የ “CBE Birr” የሚጠቀሙ የተቋሙ ደንበኞች በቀጥታ መክፈል የሚችሉ ሲሆን፤ አገልግሎቱ የማይጠቀሙት ደግሞ በ “CBE Birr” የሚያስጠቅሙ ወኪሎች /Agents/ አማካኝነት መክፈል ይችላሉ፡፡ የ “CBE Birr” አካውንት ቁጥሩም 707070 ነው፡፡
በመሆኑም የ “CBE Birr” የምትጠቀሙ ደንበኞች፤ የሚከተሉትን የአጠቃቀም መመሪያዎች በመከተል ክፍያ መፈፀም ትችላላችሁ፡፡
For CBE Birr service /Customer User Guide by Engilsh/
To Pay for Ethiopia Electric Utility, follow the following Steps:
Step 1. Dial On *847#
Step 2. input Number 5 for pay bill.
Step3. input Number 2 to enter short code.
Step 4. input short code(707070) for Ethiopia Electric Utility.
Step 5. Input customer account number.
Step 6. Check customer name and Amount
Select 1. OK
0. Cancel.
Step 7. Input PIN.
For confirmation- check message on you mobile.
ለ‘’CBE Birr’’ አገልግሎት /የደንበኞች መጠቀሚያ በአማርኛ/
1. ወደ *847# ይደውሉ፤
2. 5 ቁጥር በመጫን የክፍያ አገልግሎት የሚለውን ይምረጡ፤
3. 2 ቁጥር በመጫን የአገልግሎት አቅራቢ ቁጥር ያስገቡ የሚለውን ይምረጡ፣
4. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አቅራቢ ቁጥር /707070/ ያስገቡ
5. የደንበኛ መለያ ቁጥር (Customer account number) ያስገቡ፤
6. የክፍያን መጠኑንና ስም ያረጋግጡ፤
ሀ. ክፍያውን ለመፈፀም ለአዎንታ “1” ቁጥርን ያስገቡ፤
ለ. ለማቋረጥ “0” ን ያስገቡ፤
7. የሚስጥር ቁጥር ያስገቡ፤
8. ክፍያን የሚያረጋግጥ መልእክት ወዲያውኑ ከሲቢኢ ብር ይደርስዎታል፤ 

















Short info

× Chat