askwala.com - የአዕምሮ ጤና ምንድነዉ?
Header







የአዕምሮ ጤና ምንድነዉ?

Image name: mental health.jpg

ስለ አዕምሮ ጤና ከማዉራታችን በፊት ጤና ምንድነዉ የሚለዉን ማየቱ መልካም ነዉ። ጤና (Health) ለሚለዉ ቃል ሁሉንም ሊያስማማ የሚችል መልስ እስካሁን አልተገኘም። ነገር ግን እንደ አለም ጤና ድርጅት አተረጓጎም ፡- ጤናን “የበሽታ አለመኖር ሳይሆን የተሟላ አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማህበራዊ ደህንነት ነዉ” በማለት የሶስቱ ፈርጆች ጤናማነት ሲሟላ የሚመጣ ሁኔታ አድርጎ ይወስደዋል።
ወደ አዕምሯዊ ጤና ስንመጣ የአንድን ሰዉ አስተሳሰብ፣ ስሜትና ድርጊት ይገልጻል። አዕምሯዊ ጤና ስሜታዊና አዕምሯዊ ደህንነት ሲሆን እያንዳንዱ ግለሰብ የማገናዘብ አቅሙንና ስሜታዊ ችሎታዉን ተጠቅሞ በማህበረተሰቡ ዉስጥ ግዴታዉን በመወጣት የዕለት ተለት የኑሮ ፍላጎቱን መሟላት መቻል ነዉ።
አዕምሯዊ ጤና ሰዎች አቅማቸዉ እና መክሊታቸዉን የመጠቀም እና ከችሎታቸዉ ከፍታ የመድረስ ብቃት ነዉ። በስራ ዉጤታማ መሆንና ለማህበረተሰቡ አስፈላጊዉን አስተዋጽኦ ማበርከት መቻል አዕምሯዊ ጤናቸዉ የተስተካከለ ሰዎች መገለጫ ጠባይ ነዉ።
አዕምሯዊ ጤና ባጠቃላይ ከአሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ስሜቶቻችን ጋር የጠበቀ ቁርኝነት አለዉ። የአዕምሯዊ ጤና ባለቤት ልንሆን የምንችለዉ ከራሳችንም ሆነ ከሌሎች ጋር ስንታረቅና ፍሬያማ ግኑኝነት መፍጠር ስንችል ነዉ። ከራስ ጋር ለመታረቅ አስቀድሞ ራስን በማወቅ ከአሉታዊ ስሜቶች (መናደድ፣ ማዘን፣ መፍራት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል፣ ምቀኝነት፣ ቅናት፣ ቂም እና ተጠራጣሪነት) በመራቅ ወደ ሳቢ ስሜቶች (ፍቅር፣ ደስታ፣ አድናቆት፣ ሩህሩህነት፣ ጉጉነት፣ ፈጠራና የማወቅ ፍላጎት) መሳብ መቻል ከሌሎች ጋር ለምንመሰርተዉ የሰመረ ግኑኝነት ጠንካራ መሰረት ይጥላል።
አዕምሯዊ ጤና የሰመረ መሆኑ መገለጫዎች መካከል፡-
👉በራስ መተማመን
👉በመጥፎ ልማዶች ያለመዉደቅ እናም ራስን በማየት መታረም
👉ያለመሰላቸት
👉በየጊዜዉ አዲስን ነገር ለመማር ዝግጁ መሆን
👉ስለ ህይወት ትርጉም ያለዉ እንደሆነና፣ የተስተካከለ እና ቀና አመለካከት መኖር
👉አሉታዊ ስሜቶችን እና ዉጥረትን መቆጣጠር መቻል
👉መረጃዎችን አቀናብሮ መጠቀም መቻል
👉ለራስ እንደሚያስቡ ለሌሎችም ግድ ማለት መቻል
👉ችግርን መፍታት መሞከር ካልሆነም ለሌሎች ማካፈል እና አስፈላጊ ሲሆን ትብብር መጠየቅ መቻል
👉ራስን በበጎ አኳኋን መመዘን፣ ማሻሻል እና ማሳደግ መቻል
👉ራስን መምራት መቻል
👉በራስ መወሰን መቻል
እነዚህን ባህርያት መላበስ ከህይወታችን አሰራር ጋር የጠበቀ ዝምድና አላቸዉ። በመሆኑም በህመም ላለመጠቃት ብርታትም ጭምር ናቸዉ።
ባጠቃላይ፤ ዉጤታማነትና ስኬት የአዕምሮ ጤንነት ዋና ማሳያዎች ናቸዉ። ዘና ማለት፣ እችላለሁ ባይነት፣ የተወዳዳሪነት ስሜት፣ ጭንቀትን መቆጣጠር መቻልና ከመጥፎ ሁኔታ በቶሎ ማገገም መቻል አዕምሮ ጤንነት ትሩፋቶች ናቸዉ። 

















Short info

× Chat