askwala.com - ባለፉት 8 ወራት ብር 191.4 ቢሊዮን በላይ ገቢ ተሰበሰበ
Header







ባለፉት 8 ወራት ብር 191.4 ቢሊዮን በላይ ገቢ ተሰበሰበ


በ2013 በጀት ዓመት ስምንት ወራት ውስጥ ብር 191.28 ቢሊዮን ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ብር 191.45 ቢሊዮን በመሰብሰብ 100.09% ተመዝግቧል፡፡
ከአለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ24.63 ቢሊዮን ብር ወይንም የ14.76% ዕድገት አሳይቷል፡፡
ይህም ከሀገር ውስጥ ታክስ ብር 116.70 ቢሊዮን፣ ከውጭ ቀረጥና ታክስ ብር 74.59 ቢሊዮን እና ከሎተሪ ሽያጭ የተጣራ ገቢ ብር 154.46 ሚሊዮን የተሰበሰበ ነው፡፡
ይህ የገቢ አሰባሰብ ከነበረውና ካለው ዓለም አቀፋዊና ሀገር አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ከፈጠረው ኢኮኖሚዊ ተግዳሮት አንጻር ሲታይ የተሻለ የአፈጻፀም የተመዘገበበት ነው፡፡ ከዕቅድ በላይ አፈጻጸም እንዲመዘገብ አስተዋፅኦ ያደረጉ ምክንያቶች፡-
1ኛ). ዓለም አቀፍ የሆነው የኮሮና ወረርሽኝ በሀገራችን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ የፈጠረውተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ፤
2ኛ). በሀገር አቀፉ የሕግ ማስከብር ዘመቻ ለ3 ወራት ያህል በትግራይ ክልል ሁለቱም ገቢ ሰብሳቢ ተቋሞቻችን ገቢ ያልሰበሰቡ በመሆናቸው፤
3ኛ). ላለፉት 8 ወራት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የፀጥታ ችግርና መፈናቀል ስለተከሰተ የንግዱ ማህበረሰብም ሆነ ተቋማችን ተረጋግቶ መሥራት ያልቻሉባቸው ሁኔታዎች እያሉ እንዲህ ያለ አፈጻፀም ማስመዝገብ መቻል ውጤቱን ይበል የሚያሰኝ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡
ከላይ የተገለፀው አፈጻፀም ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የተሻለ ሆኖ የተገኘው በገቢዎች፣ በጉምሩክ ኮሚሽንና በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር አመራሮችና ሠራተኞች ጠንካራ ሥራ ብቻ ሳይሆን ከላይ እስከታች ያሉ የመንግሥት አካላት፣ ሀገርና ህዝብ ወዳድ ግብር ከፋዮቻችን፣ የአጋር አካላትና የመላው ህዝባችን ድጋፍና ትብብር ከፍተኛ በመሆኑ የገቢዎች ሚኒስቴር ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ 

















Short info

× Chat