askwala.com - አሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም አገራት ካልጋበዟት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ አስታወቀች
Header







አሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም አገራት ካልጋበዟት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ አስታወቀች


አሜሪካ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በሚደረገው ድርድር ሶስቱም አገራት ካልጋበዟት በስተቀር አገራቱን ለማደራደር ጣልቃ እንደማትገባ አስታወቀች
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የቀጠናዊ ጉዳዮች ቃል አቀባይ ሳሙኤል ዋርበርግ “ቴን” በተባለ የግብጽ የሳተላይት ቴሌቪዥን ላይ በሚሰራጨው “ፔን ኤንድ ፔፐር” ዝግጅት ላይ በዙም ተጋብዘው በሰጡት ማብራሪያ፤ የአባይ ወንዝ ለግብጽ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ለሱዳንም በጣም ጠቃሚ ወንዝ መሆኑን አሜሪካ ታምናለች ብለዋል።
በአገራቱ መካከል ያለው ልዩነት በውይይትና በድርድር እንዲፈታ አገራቸው ድጋፍ ማድረጋን እንደምትቀጥል ቃል አቀባዩ ገልጸዋል።
ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ አሜሪከ ሶስቱም አገራት ጥሪ ካደረጉላት የሚጠበቅባትን አዎንታዊ ሚና ለመወጣት ዝግጅት እያደረገች መሆኗን ነው የገለጹት።
አሜሪካ በግድቡ ዙሪያ ያሉ አለመግባባቶች መፈታታ ያለበት በሶስቱ አገራት ብቻ ነው የሚል አቋም እንዳላት የገለጹት ቃል አቀባዩ፤ አገራቸው በሶስቱ አገራት ጥሪ ካልቀረበላት በስተቀር ጣልቃ እንደማትገባ አስታውቀዋል። 

















Short info

× Chat