askwala.com - ህንድ የአስትራዜኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አስታወቀች
Header







ህንድ የአስትራዜኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው አስታወቀች


ህንድ የአስትራዜኔካ ክትባት ከደም መርጋት ችግር ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለውና ክትባቱንም በስፋትና በሙሉ አቅሟ ለዜጎቿ መስጠት እንደምትቀጥል አስታወቀች፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱ ምንም ችግር የማያስከትልና አስተማማኝ መሆኑን ገልጾ ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል የሰጠውን ፈቃድ ወደ ጎን በመተው ፈረንሳይ፣ ስፔንና ጀርመንን ጨምሮ አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል ማገዳቸው ህንድን ብዙም እንደማያሳስባት ገልጻለች።
በመሆኑም ክትባቱን በስፋት ከመጠቀም የሚያግዳት ነገር እንደሌለ የአገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያ ገልጸዋል፡፡
ይህ ክትባት የተመረተው በዓለም ትልቁ ክትባት አምራች በሆነው በህንድ ሴሩም ኢንስቲትዩት ሲሆን በአገሪቱ ኮቪሺልድ እየተባለ ይጠራል፡፡
እስካሁንም በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር የአስትራዜኔካ ብልቃጥ ክትባቶችን በማምረት በዓለም ለሚገኙ ታዳጊ አገሮች መሰራጨቱ የተገለጸ ሲሆን ህንድም ለ35 ሚሊዮን ዜጎቿ መስጠቷ ተገልጿል፡፡
የህንድ የመድሃኒት ቁጥጥር መስሪያ ቤት እና ሌሎች ተቋማት በክትባቱ ዙሪያ መረጃዎችን ማጣራታቸውንና በክትባቱ እና በደም መርጋት ችግር መካከል ምንም አይነት ምክንያታዊ ግንኙነት እንደሌለ መረጋገጡን የመንግስት አማካሪ ምክር ቤት አባል ቪኖድ ኬ ፖውል መግለጻቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ 

















Short info

× Chat