askwala.com - ማርን ያለ ንብ፤ ወተትን ያለ ላም ማዘጋጀት
Header







ማርን ያለ ንብ፤ ወተትን ያለ ላም ማዘጋጀት


እንደአለም አቀፉ የምግብና ግብርና ተቋም (FAO) መረጃ ከሆነ ባለፉት ጥቂት አመታት የስጋና የወተት ውጤቶች በአለማችን የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀት ውስጥ 14.5 በመቶ እንደሚሸፍኑ አስታውቆ ነበር፡፡ እንዲሁም በከፍተኛ መጠን በአለማችን ላይ ጥቅም ላይ ከሚውለው የማር ምርት ጋር ተያይዞ ብዛት ያላቸው የንብ ዝርያዎች ከፍትኛ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ይነገራል፡፡ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ የስጋና የወተት ውጤቶች ከአትክልት በሚገኙ ምግቦች በተወሰነ መልኩ እየተተኩ በሚጡም የምርቶቹ ልዩ ባህርያት በአመጋገገብ ሂደት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ያደርጋቸዋል፡፡
በኢንግሊዟ ዋና ከተማ ለንደን መቀመጫውን ያደረገው ቤተር ዲያሪ የእነዚህን ምግቦች ተፈጥሮኣዊ ይዘት በጠበቀ መልኩ በሁሉም የሞሎኪውል ስርዓታቸው ከተፈጥሮአዊው ማር እና ወትት ጋር ምንም ልዩነት የሌላቸውን የማርና የወተት ውጤቶች በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን፤ እጅግ ብዛት ያላቸውን ደቂቅ አከላትን በመጠቀም በፈርመንቴሽን ቴክኖሎጂ (fermentation) አማካኝነት የማር እና የወተት ምርቶች በማምርት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ የሜታቦሊክ ሂደት በሆነው የፈርመንቴሽን ስርዓት ደቂቅ አካላትን (micro-organisms) በትክክለኛው መጠን በማቀነባበር እና ከእርሾ (yeast) ጋር በማጣጣም ሌሎች የመጠጥ እና የምግብ ውጤቶች እንደሚመረተው የማርና የወተት ወጤቶችም በዚህ መልኩ ማምርት እንደሚቻል ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
የእንስሳት ተዋፅዖችን መሰረት አድርገው የሚሰሩ የምግብ እና የመጠጥ ውጤቶችን የማይመገቡ (vegans) ሰዎች ይህን በሞሎኪውል ስርዓታቸው ከተፈጥሮአዊው ምርቶች ጋር ምንም ልዩነት የሌላቸው bio-identical ምርቶች ወደ ገበያ ለማቅረብ ረዥም የምርምር ሂደት የሚስፈልጋቸው ቢሆንም ለአካባቢ ስነምህዳር ከሚሰጡት የጎላ አዎንታዊ አስተዋፅኦ አንፃር ተቀባይነተቻው እጅግ ከፍ ያለ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ በዚህ ዘርፍ ላይ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት እንደ MeliBio እና Clara Foods ያሉ ድርጅቶችም በፈርመንቴሽን ቴክኖሎጂ የተቃኘ የማቀነባበሪያ ስርዓቶችን በመዘርጋት በተፈጥሮ ይዘታቸው ተመሳሳይ የሆኑ ምርቶችን በማዘጋጀት ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡ MeliBio የተባለው የአሜሪካን ድርጅት ከንብ የሚገኘውን የማር ምርት በፈርመንቴሽን ቴክኖሎጂ አማካኝነት ለመተካት እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን Clara Foods የተባላው ተቋም ደግሞ ተመሳሳይ ቴክኒኮችን በመጠቀም እስከ 2028 ድረስ ከእንቁላል የሚገኙትን ንጥር ነገሮች በራሱ በማምረት ለአለም ገበያ ለማቅርብ እንደሚሞክር አስታውቋል፡፡
ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የማር ምርት ለሌሎች የምርት ውጤቶች እንደግሪዲየንት ሆኖ ከማገልገሉ አንጻር እነዚህ ድርጅቶች ምርታቸውን ይዘው በሚቀርቡበት ወቅት ወደ ገበያው ለመግባት ቢዝነስ ቱ ቢዝነስ የተባለውን ሞዴል የሚከተሉ ይሆናል፡፡ ይህም በቀጥታ ምርታቸውን ወደተጠቃሚው ከማድረስ ይለቅ የምግብ፣ የመጠጥ፣ ኮስሞቲክ እና የመድሃኒት አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በጋራ በመስራት ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ ለማስገባት እቅድ ይዘዋል፡፡ የ MeliBio መስራች ሚስተር ማንዲች እንደሚሉት በአሜሪካ ከሚገኙ 15 ኩባንያዎች ጋር ምርታችንን ለማቅርብ የተስማማን በመሆኑ በዚህ አመት መጨረሻ ላይ ወደገበያ ለመቅረብ አቅድ አለን ብለዋል፡፡ 




© BBC   













Short info

× Chat