askwala.com - የታክስ ስሌት ሊሻሻል ይችላል?
Header







የታክስ ስሌት ሊሻሻል ይችላል?


በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀጽ 28 እንደተገለጸው የታክስ ባለስልጣኑ የቀረበለትን የታክስ ማሳወቂያ በሚያገኘው መረጃ መሰረት በመለወጥ፣ በመቀነስ ወይም በመጨመር ሊያሻሽል ይችላል፡፡
በማንኛውም ጊዜ በታክስ ከፋዩ ወይም በታክስ ከፋዩ ስም የማጭበርበር ድርጊት ሲፈጸም ወይም በከፍተኛ ሁኔታ በማወቅ የተፈጸመ የቸልተኝነት ድርጊት ሲኖር ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት ታክስ ከፋዩ በራሱ የሚያሰላው የታክስ ስሌት ሲሆን ታክስ ከፋዩ የራስ ታክስ ስሌት ማስታወቂያውን ካቀረበበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት አመት ውስጥ አልያም በሌላ በማንኛውም የታክስ ስሌት ባለስልጣኑ ለታክስ ከፋዩ የታክስ ስሌት ማታስወቂያ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር አምስት አመት ውስጥ ሊያሻሽል ይችላል፡፡
በመሆኑም ከላይ በተገለጸው አግባብ እንደሁኔታው የተሰላውን የታክስ መጠን፣ የማሻሻያውን ምክንያቶች፣ ሊከፈል የሚገባ ማንኛውም ታክስና ቅጣት ካለ የታክስ ማስታወቂያ ለግብር ከፋዩ ይሰጣል፡፡ ግብር ከፋዩም ማስታወቂያው በደረሰው ሰላሳ ቀናት ውስጥ በተሻሻለው ስሌት መሰረት መክፈል ይኖርበታል፤ ነገር ግን በውሳኔው የማይስማማ ማንኛውም ግብር ከፋይ ቅሬታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ 

















Short info

× Chat