askwala.com - ለምን ታረፍጃለሽ በማለቷ ብቻ የስራ ባልደረባዋን በቢላዋ ወግታ የገደለቻት ወንጀለኛ በእስራት ተቀጥታለች፡፡
Header







ለምን ታረፍጃለሽ በማለቷ ብቻ የስራ ባልደረባዋን በቢላዋ ወግታ የገደለቻት ወንጀለኛ በእስራት ተቀጥታለች፡፡


ተከሳሽ ቤተልሄም እሸቱ ትባላለች የ24 አመት ወጣት ስትሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ክልል ልዩ ቦታዉ የካ አባዶ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ዉስጥ ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር በመሆን ተዳራጅተዉ የተማሪዎችን ምግብ በማብሰል ስራ ይተዳደራሉ ፡፡ በዚህ መሃል ተከሳሿ በቀን 30/03/2012 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 3፡30 ሲሆን ወደ ስራ ስትገባ መቅደስ ከበደ የተባለች የስራ ባልደረባዋ ለምን ታረፍጃለሽ በማለቷ ምክንያት በመካከላቸዉ አለመግባባት ይፈጠራል፡፡
ተከሳሽም ማርፈዴን የበላይ አለቃዬ ድረስ በመግባት ተናግረሻል ስትል ሟች መቅደስ ከበደን በያዘችዉ ቢላዋ አንድ ጊዜ የግራ አንገቷን በመዉጋት ህይዎቷ እንዲያልፍ ታደርጋለች፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ዐቃቤ ህግም የወንጀል ህግ አንቀፅ 540 ስር የተመለከተዉን ድንጋጌ በመተላለፍ በፈፀመችዉ ተራ የሆነ የሰዉ ግድያ ወንጀል ክስ በመመስረት የሰዉ፣የፅሁፍ፣ ገላጭና የኤግዚቪት የማስረጃ ዝርዝሮቹን አጠናቅሮ የክስ ሂደቱ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡ መዝገቡን የተመለከተዉ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የወንጀል ችሎትም የቀረቡለትን ማስረጃዎች አይቶ ተከሳሽን ወንጀለኛ ነሽ ሲል ቅጣት አስተላልፏል፡፡ ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋት ሪከርድ የሌለባት መሆኑ፣ ያላት ባህሪ መልካም መሆኑና የቤተሰብ ጧሪ መሆኗ በቅጣት ማቅለያነት ተይዞላት በ11 አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ተወስኖባታል፡፡
ህብረተሰቡ በጊዚያዊና በደቂቃዎች ዉስጥ ሊያልፍ በሚችል ስሜት ተነሳስቶ እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ተግባር ከመፈፀም በመቆጠብ ሌሎችን ከመጉዳትና የራሱንም ህይዎት አደጋ ላይ በመጣል ልጆችን ያለ አሳዳጊ እናት አባትን ያለ ጧሪ ላለማስቀረት ራሱን በመግዛት ነገሮችን በትእግስት ሊያልፍ ይገባዋል መልእክታችን ነዉ፡፡ 

















Short info

× Chat