askwala.com - ዘ ባችለር የተሰኘው በኤቢሲ ቴሌቪዥን የሚሰራጨው ሪያሊቲ ሾው ባለፈው ሳምንት ማለትም ማርች አስራ አምስት ተጠናቋል፡፡
Header







ዘ ባችለር የተሰኘው በኤቢሲ ቴሌቪዥን የሚሰራጨው ሪያሊቲ ሾው ባለፈው ሳምንት ማለትም ማርች አስራ አምስት ተጠናቋል፡፡

Image name: Zehabesha.PNG

ዘ ባችለር የተሰኘው በኤቢሲ ቴሌቪዥን የሚሰራጨው ሪያሊቲ ሾው ባለፈው ሳምንት ማለትም ማርች አስራ አምስት ተጠናቋል፡፡ ማት ጀምስ የተባለውን ወንድ የግላቸው ለማድረግ ሰላሳ ሰባት ሴቶች ከፍተኛ ውድድር ካደረጉ በኋላ ራሄል የተባለች የጆርጂያ ነዋሪ የሀያ አራት አመት ወጣት አሜሪካዊት አሸናፊ ሆናለች፡፡
ይህ ውድድር ለሀያ አምስተኛ ጊዜ የተከናወነ ሲሆን የዘንድሮውን ለየት የሚያደርገው አንዲት ኢትዮጵያዊት በመወዳደሯ ነው፡፡ ይህች ተወዳዳሪም ማእረግ(ማጊ) ታረቀ የምትባል የሰላሳ ሁለት አመት ሴት እንደሆነች ከዚህ ቀደም ዘሀበሻ መዘገቡ ይታወሳል፡፡
በዲቪ ሎተሪ ከአስር አመት በፊት አሜሪካ የገባችው ማጊ በሙያዋ ፋርማሲስት ስትሆን በሞዴልነትም የምትሰራ ናት፡፡ ማጊ ከቫንቲ ፌይር መፅሄት ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ወግ አጥባቂ ኢትዮጵያዊያን ለአንድ ወንድ ከበርካታ ሴቶች ጋር ፉክክር ውስጥ መግባቷን መመልከታቸውን እንዳልወደዱት ገልፃለች፡፡ ቢሆንም በውድድሩ ላይ በመሳተፏ አሁንም ትስማማለች፡፡
እንደተናገረችው ማት ጀምስ እሷ የምትፈልገው አይነት ወንድ ነበር፡፡ ማት ጀምስን ያፈቀረችው በዘሩ ወይንም በቀለሙ ምክንያት ሳይሆን በክርስቲያንነቱና ለህፃናት እርዳታ የመስጠት ስራ ላይ በመሰማራቱ እንደሆነም አስታውቃለች፡፡ እሷም ለደሀ አገራት ተማሪዎች በተለይ ለኢትዮጵያዊያን ጫማ የሚሰጥ ‹‹ቤር ፉት›› የተሰኘ እርዳታ ድርጅት እንዳላት ገልፃለች፡፡
ስትናገር ‹‹እኔ ሁሌም ከእንደዚህ አይነት ለሰዎች እርዳታ ከሚሰጥ ሰው ጋር መሆን እፈልግ ነበር፡፡›› ብላለች፡፡ እንደመፅሄቱ ዘገባ በውድድሩ ላይ ከሌሎቹ ሴቶች ተወዳዳሪዎች ጋር ብትግባባም ብዙም እይታ ውስጥ ሳትገባ ቀርታለች፡፡ ማት ጀምስ በውድድሩ አጋማሽ እስከሚያባርራት ድረስም በትዊተር ‹‹ፍትህ ለማጊ›› የሚል ዘመቻ ሲደረግ እንደነበርም ዘገባው አስረድቷል፡፡ ማጊ በዚህ ውድድር ያገኘችውን ታዋቂነት በመጠቀም አሁን ‹‹ፍትህ ለትግራይ›› የሚለውን የትዊተር ዘመቻ ተቀላቅላለች፡፡
በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ የህወሀት ደጋፊዎች ጋር በመሆንም የተቃውሞ ቪዲዮ ሰርታ በትዊተር ለቃለች፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቃ ስትመልስ ‹‹እኔ ፖለቲከኛ አይደለሁም፡፡ እኔ ከሰብአዊነት ጋር የምቆም ነኝ፡፡ ከዚህ ቀደም በየትኛውም ተቃውሞ ላይ ተሳትፌ አላውቅም፡፡ አሁን ወደዚህ ውስጥ እንድገባ ያስገደደኝ የቤተሰቦቼ ነገር ነው፡፡ እነሱ መናገር አልቻሉም፡፡ የእነሱ ብቸኛ ድምፅ እኛ ነን›› ማለቷን ዛሬ ከመፅሄቱ ላይ አንብበናል፡፡ 

















Short info

× Chat