askwala.com - በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ጊዜ ከሚያገኟቸው ሶስት ግለሰቦች አንዱ የኮቪድ-19 ቫይረስ ሊኖርበት ይችላል፡፡
Header







በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ጊዜ ከሚያገኟቸው ሶስት ግለሰቦች አንዱ የኮቪድ-19 ቫይረስ ሊኖርበት ይችላል፡፡


በኢትዮጵያ ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ይህም በበሽታው የሚያዙ ፤ በጽኑ የሚታመሙና ህይወታቸውን የሚያጡ ወገኖቻችን ቁጥር በተለየ ሁኔታ በከፍተኛ መጠን ጨምሯል።
በትላንትናው ዕለት ለኮቪድ-19 ናሙና የሰጡ 7,659 ግለሰቦች የተመረመሩ ሲሆን 1,981 ሰዎች ማለትም ከተመረመሩት ከ100 ግለሰቦች 26 ያህሉ (26%) ኮቪድ-19 ቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡ ይህም በአጭሩ አብረውን ካሉ ሶስት ግለሰቦች አንዱ ኮቪድ-19 ቫይረስ ሊኖርበት ይችላል ማለት ነው፡፡
ስለዚህ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አሁን ማስክን በሚገባ ማድረግ፣ ሁልጊዜ የእጆቻችንን ንጽሕና መጠበቅ፣ ከሰዎች ጋር ያለንን ርቀት መጠበቅና ሊፈጠሩ ከሚችሉ የሰዎች መሰባሰብ ራስን መቆጠብ ይገባል። 




© ኢሕጤኢ   













Short info

× Chat