askwala.com - 7ኛው ጉማ የፊልም ሽልማትና የሥነ ሥርዓቱ ለየት ያሉት ክስተቶች
Header







7ኛው ጉማ የፊልም ሽልማትና የሥነ ሥርዓቱ ለየት ያሉት ክስተቶች


ኢትዮጵያ ውስጥ ቅዳሜ ዕለት በተካሄደው 'የጉማ' ሽልማት ላይ ከዚህ በፊት ከተካሄዱት የሽልማቱ ሥነ ሥርዓቶች የተለዩ መነጋገሪያ ጉዳዮች ተከስተዋል።
በተለይ ደግሞ ሽልማቱን ካሸነፉ የፊልም ባለሙያ ዎች መካከል አንዱ የነበረው ኢሳያስ ታደሰ በመድረኩ ላይ "እናቴ ደም ስታለቅስ፣. . . . በዚህ ሽልማት ልደሰት አልችልም" ሲል መናገሩና የታዳሚዎች አለባበስ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ባለቀለም ፊልም በሆነው "ጉማ" በተሰኘው የሚሸል ፓፓታኪስ ፊልም ስም የተሰየመው የፊልም ሥራ ሽልማት ቅዳሜ ዕለት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በድምቀት ተከናውኗል።
በየዓመቱ የሚካሄደው ይህ የ"ጉማ" ሽልማት ለሰባተኛ ጊዜ የተካሄደ ሲሆን ለአንድ ዓመት በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሳይካሄድ ቆይቶ ቅዳሜ ዕለት በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ተከናውኗል።
በዚህ ሰባተኛው የሽልማት መርሃ ግብር ላይ 45 ፊልሞች የተመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 15ቱ በተለያዩ 16 ዘርፎች ታጭተው እንደነበር ታውቋል። 

















Short info

× Chat