askwala.com - ከግማሽ ቢሊዮን የሚበልጥ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ማፈትለኩ ተነገረ
Header







ከግማሽ ቢሊዮን የሚበልጥ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መረጃ ማፈትለኩ ተነገረ

Image name: facebook.jpg

ከግማሽ ቢሊዮን የሚበልጡ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ግላዊ መረጃዎች በኦንላይን መለቀቁን ሁድሰን ሮክ /Hudson Rock/ የተባለ የሳይበር ደህንነት ኩባንያ አስታውቋል፡፡
የስልክ ቁጥሮችን፣ የመኖሪያ ቦታን፣ የልደት ቀንን፣ የፌስቡክ አድራሻን፣ ሙሉ ስምን እና የኢ-ሜይል አድራሻዎችን የያዘ መረጃ በጠላፊዎች ድረ-ገጽ ላይ መውጣቱ ተገልጿል፡፡
የሁድሰን ሮክ ኩባንያ ኃላፊ አሎን ጋል /Alon Gal/ ችግሩ መታየት ከጀመረ ጥቂት ዓመታት ማስቆጠሩን እና በ106 ሀገራት ተጠቃሚዎች ላይ መታየቱን ተናግረዋል፡፡
ተጠቂ ከሆኑ ተጠቃሚዎች ውስጥ 32 ሚሊዮን የዩናይትድ ስቴትስ፣ 11 ሚሊዮን የዩናይትድ ኪንግደም እና 6 ሚሊዮን የህንድ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡
የፌስቡክ ቃል-አቀባይ አንዲይ ስቶን /Andy Stone/ በመጋቢት 26 ለሲ.ኤን.ኤን /CNN/ በሰጡት ቃል ችግሩ በ2019 ሪፖርት የተደረገና የቆየ መረጃ መሆኑን አንስተዉ በፈረንጆቹ ሐምሌ 2019 ችግሩ ተለይቶ ማስተካከያ እንደተደረገበትም አስረድተዋል፡፡
ይሁን እንጂ መረጃው የቆየ መሆን የሳይበር ወንጀለኞችን እና የማንነት ዘራፊዎችን ከመበዝበዝ እንዳላገዳቸው የሁድሰን ሮክ ኃላፊ አሎን ጋል ተናግረዋል፡፡
አሎን ጋል ጨምረው እንዳሳወቁት ህገ-ወጦች መረጃውን ለማህበራዊ ምህንድስና፣ ለማጭበርበር፣ ለጠለፋ እና ለንግድ ሊጠቀሙበት ይችላሉ ብሏል፡፡
በመረጃ ማፈትለክ አደጋ ካጋጠማቸው የፌስቡክ ተጠቃሚ ሀገሮች መካከል ኢትዮጵያም 103ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን 12,753 ተጠቃሚዎች ግላዊ መረጃ መሹለኩን bleeping Computer.com ገልጿል፡፡
በመሆኑም ሁሉም የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ግላዊ መረጃዎችን የሚጠይቁ ወይም ማስፈንጠሪያዎችን እንዲከፍቱ የሚጋብዙ ያልተለመዱ የኢ-ሜይል ወይም የጽሑፍ መልዕክቶች ላይ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ 

















Short info

× Chat