askwala.com - የማህበራዊ ትስስር ገጽዎን ደህንነት በምን መልኩ ማስጠበቅ ይችላሉ?
Header







የማህበራዊ ትስስር ገጽዎን ደህንነት በምን መልኩ ማስጠበቅ ይችላሉ?

Image name: Social Media Sites.jpg

እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲውተር፣ ዋትስአፕ እና ቲክ ቶክ ያሉ የማህበራዊ የትስስር ገጾች ሰዎች ግላዊ አመለካከታቸውን እና በህይወታቸው እየተፈጠሩ ስላሉ ጉዳዮች መረጃዎችን የሚያጋሩበት መድረክ ነው፡፡ ነገር ግን ቆም ብለን ልናስብባቸው የሚገቡ ጉዳዮችም አሉ፡፡
አንዳንድ ጊዜ በጣም ግላዊ የሆኑ መረጃዎች በይነ-መረብ ላይ ልናጋራ እንችላለን፡፡ እነዚህን የምናጋራቸውን ነገሮች ከምናምናቸው ጓደኞቻችን እና ከቅርብ ቤተሰቦቻችን ውጪ ማን ጋር እንደሚደረሱ መገመት ግን አዳጋች ነው፡፡ አጥፊ ሶፍትዌሮች፣ ቂመኛ ባልንጀሮቻችን እንዲሁም የሳይበር ወንጀለኞች ጭምር በምናጋራቸው መረጃዎች ላይ ፍላጎት ሊኖራቸውና ሊያጠቁን ይችላሉ፡፡
በመሆኑም ቀጥሎ የቀረቡ ምክረ-ሀሳቦችን የማህበራዊ የትስስር ገጾችን ስንጠቀም ተግባራዊ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
1. የይለፍ ቃልዎን ደህንነት ያስጠብቁ፣
• እንደ የልደት ቀን፣ የፍቅረኛ ወይም የትዳር አጋር ስም፣ የሚወዱትን ጓደኛ፣ የወላጅ ወይም የልጅ ስም በምስጢራዊ የይለፍ ቃልዎ ውስጥ መጠቀም የይለፍ ቃልዎን በቀላሉ ለመገመት ያስችላሉ፤
• ፊደላትን እና ቁጥሮችን ያሰባጠረ፣ በይበልጥም ምልክቶችን እና ካፒታል ፊደሎችን የያዘ የይለፍ ቃል መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
2. አድራሻ እና የጉዞ እቅድን ከማጋራት ይቆጠቡ፣
• አንበልእና የመኖሪያ ቤትዎን ዘግተው ለአንድ ሳምንት ያህል ከሀገር እንደሚወጡ በማህበራዊ ሚዲያ ገፅዎ ቢያጋሩ ራስዎን፣ መኖሪያ ቤትዎን እና ንግድዎን ወዴት እንደሚሄዱ በመግለጽዎ ብቻ ለአደጋ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡
• ይህ ዘበት ሊመስል ይችላል ነገር ግን ህጻናትን የሚሰርቁ፣ ንብረት የሚመዘብሩ ዘራፊዎችና ሌቦች ያጋሩትን መረጃ በመጠቀም በመኖሪያ ቤትዎ ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ በመሆኑ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
3. የግል መረጃን ለህዝብ እይታ አለማቅረብ
• በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ ስለግላዊ መረጃዎቻችን ለጓደኞቻችን ያለገደብ መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ያለገደብ የተቀመጡ መረጃዎች ለጥቃት ሊያጋልጦ የሚችሉ በመሆናቸው የግላዊ መረጃ መቆጣጠሪያ ስርዓት /Privacy Setting/ ተደራሽነት ላይ ገደብ ሊያበጁ ይገባል፡፡ በተቻለ አቅም እንግዳ የሆኑ መልዕክቶችን በማህበራዊ የትስስር ገጾች አለመቀበልና አስፈላጊ ሲሆንም መዝጋት ተገቢ ነው፡፡
• የመኖሪያ አድራሻዎን፣ ስልክ ቁጥርዎን እና የኢ-ሜይል አድራሻዎን በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ከማስቀመጥዎ በፊት በአግባቡ ማሰብ ያስፈልጋል፡፡
4. ህዝባዊ የዲጂታል መሣሪያዎችን ስንጠቀም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ
• ህዝባዊ በሆኑ ቤተ-መፅሐፍቶች፣ ካፍቴሪያዎች እና በመሳሰሉት ቦታዎች ላይ ያሉ መሣሪያዎችን እና ነጻ የህዝብ ዋይፋይ /Wi-Fi/ ሲጠቀሙ ማናቸውንም ዓይነት የፋይናንስ መረጃ ያላቸው ወይም የኢ-ሜይል አድራሻዎችን በኮምፒውተሮቹ ላይ ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡
• እነዚህ መሣሪያዎች የናንተን ሰነዶች ያለፈቃዳችሁ መዝግበው የሚያስቀሩ ሊሆኑ ስለሚችሉ መጠንቀቅ ተገቢ ነው፡፡
5. ጥሩ ፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌር መጠቀም
• በግል መሣሪያዎቻችሁ ላይ የምትጭኗቸው ፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮች መሣሪያዎቻችሁን ከጥቃት እንደሚጠብቁ እርግጠኛ ሊሆኑ ይገባል፡፡ በየወቅቱ የሚፈጠሩ አጥፊ ሶፍትዌሮችን ታሳቢ በማድረግ ያልዎትን ፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮች መቀየርና ማዘመንም ተገቢ ነው፡፡ 

















Short info

× Chat