askwala.com - ቻይና የመጀመሪየውን ቋሚ የህዋ ስቴሽን ዋና ክፍል ወደ ህዋ ላከች
Header







ቻይና የመጀመሪየውን ቋሚ የህዋ ስቴሽን ዋና ክፍል ወደ ህዋ ላከች

Image name: space station.png

ቻይና የህዋ ተመራማሪዎቿ የረጅም ጊዜ ምርምሮችን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ያለችውን ቋሚ የህዋ ስቴሽን ዋና ክፍል ወደ ህዋ መላኳ ተነገረ፡፡ ይህ ከዋንቻንግ የሮኬት ማስወንጨፊያ ማእከል ወደ ህዋ የተላከው የስቴሽን ክፍል ለሀገሪቱ የህዋ ምርምር እድገት ተጨማሪ ማሳያ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ የምርምር ማእከሉን የመላኩ ተግባር ለ11 ዙሮች ከታቀደው የመጀመሪያው ሲሆን የተመራማሪዎቹን ቡድንም ለምርምሩ የሚያስፈልጉ ግብዐቶችን እስከ ቀጣይ አመት መጨረሻ ድረስ ለማጓጓዝ ታስቧል፡፡
ወደ ህዋ የተላከው ክፍል ተመራማሪዎች በአንድ ዙር ለስድስት ወራት ያክል እንዲኖሩበት የሚያስችላቸው ሲሆን ሌሎች አስር ክፍሎችም ለዚሁ ተግባር የሚላኩ ያሆናል፡፡ በአሁኑ ሰዓት 12 የሚደርሱ ተመራማሪዎች ወደህዋ የመብረርና በዚያ የመኖር ክህሎት እንዲኖራቸው የተለያዩ ስልጠናዎችን እየወሰዱ ነው፡፡ በመጭው ሰኔም ወደ ህዋ በረራ ያደርጋሉ እንደ መረጃ ምንጫችን ዘገባ፡፡
በ2022 ሙሉ ለሙሉ ወደ ህዋ ከተላከ በኋላ የቻይና የቲ ቅርጽ በአጠቃላይ 66 ቶን ክብደት ይኖረዋል፡፡ ይህም 450 ቶን ከሚመዝነው በ1998 ወደ ህዋ ከተላከው አለማቀፍ የህዋ ስቴሽን ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ ክብደት ያለው ነው፡፡ 




© Phys.org   













Short info

× Chat