askwala.com - መንግስት ከአሁን በኋላ በትግራይ ከሚደረጉ ሰብዓዊ ድጋፎች 14 በመቶውን ብቻ እንደሚሸፍን አስታወቀ
Header







መንግስት ከአሁን በኋላ በትግራይ ከሚደረጉ ሰብዓዊ ድጋፎች 14 በመቶውን ብቻ እንደሚሸፍን አስታወቀ


መንግስት ከዚህ በኋላ ከትግራይ 92 ወረዳዎች ውስጥ በ14 በመቶው ብቻ ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ፡፡
ቀሪው 86 በመቶው የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ተቋማት እንደሚሸፈን የአደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ ገልጸዋል፡፡
በክልሉ በመደረግ ላይ ካለው ሰብዓዊ ድጋፍ 70 በመቶ ያሉ በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው መባሉ የሚታወስ ነው፡፡
ሁኔታውን በተመለከተ በሰላም ሚኒስቴር መግለጫ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡ 

















Short info

× Chat