askwala.com - የቴክኖሎጂ ኢንተርፕሪንየርሺፕ (Entrepreneurship) ምንነት
Header







የቴክኖሎጂ ኢንተርፕሪንየርሺፕ (Entrepreneurship) ምንነት


የቴክኖሎጂ ኢንተርፕሪንየርሺፕ ሳቢ የሆነና ትልቅ ዋጋ ያለው የንግድ እድልን መፍጠር፣ በቴክኖሎጂ በቀላሉ ሊሰሩ የሚችሉ ምርቶች፣ ጠንካራ የሆነ የእውቀት ሀብት፣ ቀጣይነት ያለው የመወዳደር ብቃት፣ ትልቅ የሆነ አቅም ያለው ገበያ፣ እንዲሁም ሊለካ የሚችል የንግድ ሞዴልን ያጠቃልላል። ቴክኖሎጂያዊ ኢንተርፕሪንየርሺፕ በተሟላ ሁኔታ ስራውን እንዲሰራ የድርጅቱን አላማ ከግብ ሊያደርሱ የሚችሉ አሰራሮችን፣ የሳይንስና ቴክኖሎጂ እውቀትን የበለጠ ሊያጎለብቱ የሚችሉና በተለያዩ መስኮች ስፔሻላይዝ ያደረጉ ሰዎችን እንዲሁም የተሻለ የገንዘብ አቅምን ሊጠይቅ ይችላል ።
መስኩ ይበልጥ ትኩረት የሚያደርገው በትብብር ምርትን ማምረት ላይ እንጂ በግል የሚደረጉ ጥረቶች ላይ አይደለም። በመሆኑም በስራው ላይ የተሳተፉ እያንዳንዱ አካላት የራሳቸውን አስተዋፅኦ የሚያበረክቱበትን እድል ይፈጥራል። በየዕለቱ በሚደረጉት ያላሰለሱ ጥረቶች ቴክኖሎጂያዊ ኢንተርፕሪንየርሺፕ በቴክኖሎጂው መስክ ለውጦችን ያመጣል። ከነዚህም ለውጦች ውስጥ የመጀመሪያው አዲስ ቴክኖሎጂ ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ በመጀመሪያ ጊዜ ያልተሰራንና አዲስ የሆነ የቴክኖሎጂ ውጤት ማምረትን ይመለክታል። በሌላ መልኩ ደግሞ ቴክኖሎጂ ኢንተርፕሪንየርሺፕ በነበሩ ቴክኖሎጂዎች ላይ እሴትን በማከል በገበያው ላይ ልዩነትን ይፈጥራል። ይህን ሲባል መሰረታዊውን የሀገራዊ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስርዓት ለማሻሻል ይህ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ምን ያህል ጥቅም እንደሚሰጥ በማስመልከት ነው፡፡
ባለፉት 20 እና 25 ዓመታት በዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፉም ይሁን በኢኖቬሽን መስክ ላይ ትልቅ ለውጦች ያመጣል ተብሎ ሰፊ ምርምሮች እና ትኩረቶች የሚደረጉበት ይህ ዘርፍ እያደገ ያለውን የቴክኖሎጂ ኢንተርፕሪንየርሺፕ አስተዋፅኦንም በመረዳት በአሁኑ ሰዓት ፖሊሲ አውጪዎችም ጭምር ለዘርፉ ትልቅ ትኩረት ሰጥተዋል። በመሆኑም መስኩን ሊያበረታቱ የሚችሉ አንቀፆችን በፖሊሲ ውስጥ የማካተት ስራን እየሰሩ ነው። የቴክኖሎጂ ኢንተርፕሪንየርሺፕ ለአገር ሊያበረክተው የሚገባውን ጥቅም እንዲሰጥ ለማስቻል ሰፋ ያለ ጥናት ማካሄድ ተገቢ ነው። ጥናቱም የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች እንዴት ሊያድጉ፣ ሊረዳዱ፣ ሊወዳደሩና ራሳቸውን ሊያሻሽሉ ይችላሉ የሚሉትን ሊያጠቃልል ያስፈልጋል። 

















Short info

× Chat