askwala.com - የመጀመሪያው ባለ 2 ናኖሜተር ቺፕ የሴሚኮንዳክተር ዲዛይን
Header







የመጀመሪያው ባለ 2 ናኖሜተር ቺፕ የሴሚኮንዳክተር ዲዛይን

Image name: 2 Nanometer Chip Technology.jpg

አይቢኤም በሴሚኮንዳክተር ዲዛይን እና ፕሮሰስ ዘርፍ ውስጥ በዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ባለ 2 ናኖሜተር (nm) ቺፕ የናኖሺት ቴክኖሎጂን በመጠቀም አበልፅጓል፡፡ አሁን ባለው የቴክኖሎጂ አቅም እጅግ ይልቃሉ ከሚባሉት የ 7 ናኖ ሜትር ኖድ ቺፖች በ45 በመቶ የላቀ አፈፃጸም ይኖረዋል የሚባለው ይህ ቺፕ በሴሚኮንዳክተር (Semiconductors) ዘርፍ እና በጠቅላላው በአይቲ እንዱስትሪ ውስጥ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚፈጥርም ይጠበቃል፡፡
ከአንድ ግለሰብ የእጅ ጣት ጥፍር ጋር በመጠን እኩል የሆነው አዲሱ ባለ 2 ናኖሜተር ቺፕ በውስጡ 50 ቢሊዮን የሚደርሱ ትራንዚስተሮችን እንደሚይዝም ተገልጿል፡፡ ብዙ አስርት አመታትን ፍጅቶ እዚህ ደረጃ የደረሰው ይህ ግዙፍ የምርምር ውጤት ኒው ዮርክ በሚገኘው አልባኒ ናኖቴክ ኮምፕሌክስ ላብራቶሪ ውስጥ የተከናወነ ሲሆን እንደ ኢንቴልና አፕል ያሉ ተፎካካሪ ድርጅቶች ይህን መሰል የሴሚኮንዳክተር ዲዛይን ለማበልፀግ አመታት ሊፈጅባቸው እንደሚችል ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡
ቺፑን መሰረት አድርገው የሚሰሩ የኮምፒውተር አልያም የሞባይል ፕሮሰሰሮች በተመሳሳይ የሃይል መጠን 45 በመቶ የአፈፃፀም አቅማቸውን ከመጨመሩም በላይ የበይነ መረብ ፍጥነቱ ይበልጥ እንዲጨምር እና የሚጫኑ መተግበሪያዎች በተሻለ ፍጥነት መስራት እንዲችሉ የሚያደርጋቸው ይሆናል፡፡ አሁን ያሉት አብዛኞቹ የዳታ ሴንተሮች በአለምአቀፍ ደረጃ እየጨመረ ላለው የካርቦን ፉትፕሪንት የራሳቸው አስተዋፅዖ የሚኖራቸው ሲሆን፤ አዲሱን ቺፕ መሰረት አድርገው የሚሰሩ ዳታ ሴንተሮችን ግን ይህን የካርቦን ፉትፕሪንት በእጅጉ እንደሚቀንሱ ይጠበቃል፡፡
በዚህ ዘርፍ ከፍተኛ ፉክክክር የሚደርጉት አፕል እና ኢንቴል በየጊዜው እጅግ የዘመኑ የሴሚኮንዳክተር ዲዛይኖችን ይፋ ማድረግ የቻሉ ቢሆንም አይቢኤም ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ ያደረገው ይህ ባለ 2 ናኖሜተር ቺፕ በይዘቱ እና በከፍተኛ አቅሙ የመጀመሪያው ያደርገዋል፡፡ ባለሙያዎች አንደሚያስረዱት ይህ የብዙ አመት የምርምር ውጤት የሆነው ባለ 2 ናኖሜተር ቺፕ እጅግ ብዛት ያለው ትራንዚስተር የሚይዝ በመሆኑ ለፕሮሰሰር አምራቾች የተሻለ ምርት ማወጣት እንዲያስችላቸው እና እንደ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ክላውድ ኮምፕዩቲንግ እና ሌሎች የአይቲ ዘርፎች ይበልጥ ልህቀት እንዲጨምሩ ያስችላቸዋል፡፡ 




© IBM News Room   













Short info

× Chat