askwala.com - የቬነስ ሬዲዮ ሞገድ
Header







የቬነስ ሬዲዮ ሞገድ


ተመራማሪዎች በቬነስ ያለውን የሬዲዮ ሞገድ መሰማት ወደሚችል ድምጽ መለወጣቸው ተሰማ፡፡ በሐምሌ 2020 ናሳ በቬነስ የሚገኝን ተፈጥሯዊ የሬዲዮ ሞገድን ከፕላኔቷ ውስጠኛ ክፍል ማግኘት በሚያስችለው መልኩ ቀርቧል፡፡ አሁን ላይ ተመራማሪዎች ይህንን የሬዲዮ ሞገድ ወደ ድምጽ መቀየር መቻላቸውን አሳውቀዋል፡፡
እዚህ ላይ አስገራሚው ጉዳይ በወና (vacuum) ውስጥ የተፈነጠቀ የሬዲዮ ሞገድ ድምጹ ሊሰማ የማይችል መሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የድምጽ ርግብግቢት መጠኑ የሰዎች ጀሮ ሊሰማው በሚችል መልኩ የተመጣጠነ ማድረግ ከፍተኛ ስራ ነው፡፡ ተመራማሪዎች ይህን FIELDS በተሰኛ መሳሪያ የያዙትን የሬዲዮ ሞገድ በመጠቀም ቬነስ አሁን ያላትን ከፍተኛ የሆነ ሙቀት እንዴት እንዳገኘች ለማጥናት ማሰባቸውን ተናግረዋል፡፡
በዋናነት ፓርከር ስነ-ፀሐይ ምርምር አላማ ያደረገው የፀሐይን የላይኛው ውጨኛ ክፍል ለማጥናት ቢሆንም ባለፈው አመት ለዚሁ ጥናት በተደረገ በረራ ከቬነስ 500 ማይል ርቀት ላይ መድረስ ተችሏል፡፡ በዚህ በረራ ወቅት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በቬነስ ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ወይም ሁኔታ ፀሐይ ምህዋሯን ጠብቃ በምትንቀሳቀስበት ወቅት እንደሚለዋወጥ መረዳት ተችሏል፡፡ 




© Futurism   













Short info

× Chat