askwala.com - ”መብራት ለምን ታበራብናለህ“ በሚል በተነሳ ጸብ የሰው ሕይወት እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።
Header







”መብራት ለምን ታበራብናለህ“ በሚል በተነሳ ጸብ የሰው ሕይወት እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።


በምሽት የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥ ታክሲ ውስጥ “መብራት ለምን ታበራለህ” በሚል በተነሳ ጸብ የሰው ሕይወት እንዲያልፍ ያደረገው ተከሳሽ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኖበታል ።
አቶ ድሪባ ወርቁ የተባለው ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀፅ 540 ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ
ሀምሌ 20/2010 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡45 ሰዓት ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው“ ጣፎ አደባባይ” ሟች በታክሲ ረዳትነት በሚሰራበት ታክሲ ውስጥ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ተከሳሽ ባትሪ ሲያበራባቸው የታክሲው ሹፌርና ሟች ለምን በእኛ እና በታሳፊሪዎች ላይ ባትሪ ታበራብናለህ ብለው በመናገራቸው በተነሳ ፀብ ተከሳሽ ሽጉጥ አውጥቶ የታክሲ ረዳቱን በመምታቱ የሟች የቀኝ ሳንባውና ጉልበቱ ተጎድቶ በዚሁ ምክንያት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረጉ በፈፀመው ተራ የሆነ የሰው መግድል ወንጀል በዐቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ለተከሳሽ ክሱ ተነቦለት መከላከያ እንዲያቀርብና የእምነት ክህደት ቃሉን እንዲያሰማ ሲጠይቀው
ተከሳሽም “ድርጊቱን የፈፀምኩት ሆነ ብዬ አይደለም ሽጉጡ ባርቆብኝ ነው በዚህም ጥፋተኛ አይደለሁም” ሲል የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል።
ዐቃቤ ህግ በበኩሉ ድርጊቱ የተፈጸመው ተከሳሽእንደሚለው ሽጉጥ ባርቆበት አንዳልሆነ የተከሳሽን ጥፈተኝነት ለፍርድ ቤቱ ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር ስድስት የሰው ምስክሮችና ከዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የተላከው የአስክሬን ምርመራ ውጤት በሰነድ ማስረጃነት አቅርቧል።
ግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤቱ ግንቦት 04/2013 á‹“.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ የቤተሰብ አስተዳዳሪ፣ ከዚህ በፊት የጥፋት ሪከርድ የሌለበት፣ የጤና ችግር ያለበትና ማረሚያ ቤት ከገባበት ግዜ ጀምሮ የሚያሳየውን መልካም ባህሪ ከግምት ውስጥ ማስገባትና የቅጣት ማቅለያዎችን በመያዝ ተከሳሽ በ11 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል። 

















Short info

× Chat