askwala.com - የዳታ ማይኒንግ ደረጃዎች ወይም ሂደቶች
Header







የዳታ ማይኒንግ ደረጃዎች ወይም ሂደቶች


መረጃዎችን ከተከማቹ የመረጃ ስብስቦች አንጥሮና ለይቶ ለማውጣት ዳታ ማይኒንግ በብዙ ደረጃዎች ማለፍ ያስፈልገዋል፡፡ የመጀመሪያው ደረጃ ዳታ ማፅዳት ሲሆን በዳታ ማይኒንግ የመጀመሪያው ተግባር የማያስፈልገውን፣ የተደጋገመውንና ያልተሟሉ መረጃዎችን ከመረጃ ቋቱ ውስጥ ለይቶ ማጥፋት ነው፤ ይህም ዳታ ማጣራት ተብሎ ይጠራል፡፡ የማያስፈልጉ ዳታዎችን ከማስወገድ ባለፈም ተደጋግመው የተጠቀሱትን በአንድ መጠቅለልና ያልተሟሉ መረጃዎችን ማሟላት በዳታ ማጣራት ስር የሚወድቁ ተግባራት ናቸው፡፡
ዳታ ማዋሀድ የምንለው አንድና ከዚያ በላይ የሆኑ መረጃ ቋቶችን በአንድ መረጃ ቋት ሰብስቦ ማስቀመጥ ሲሆን ይህም መረጃዎችን በአንድ ላይ ለማስተዳደር ምቹ የሆነ መረጃ ቋት እንዲኖረን ያስችላል፡፡ በአንፃሩ ዳታ መረጣ ለትንተና የሚጠቅሙ መረጃዎችን ከመረጃ ቋት ነቅሶ የማውጣት ሂደት ሲሆን ቀጣዩ የዳታ ማይኒንግ ደረጃ ሆኖ ተቀምጧል፡፡ ዳታ ቅየራ ወይም ዳታ ትራንስፎርሜሽን ያሉንን ዳታዎች ለዳታ ማይኒንግ ሊጠቅሙ በሚችሉ አቀማመጥ መቀየርና ለማይኒንግ ምንጠራ ማዘጋጀት ነው፡፡ እውቀት ወይንም ጠቃሚ ሊሆኑ የሚችሉ መረጃዎችን ካሉን የመረጃ ስብስቦች ለመንቀስ የምንጠቀመው ቴክኒክና አልጎሪዝም ደግሞ ዳታ ምንጠራ ይባላል፡፡
ሌላውና የመጨረሻው ደረጃ እውቀትን ማቅረብ ሲሆን ያገኘነውን እውቀትና ጠቃሚ መረጃዎች ለሰዎች እይታ በሚመች መልኩ የምናቀርብበት መንገድ ነው፡፡ ከብዙ ክምችት አንጥረን የምናወጣቸው እውቀቶችን በሰንጠረዥ፣ በግራፍና በተለያዩ ምስሎች ሊቀርብ ይችላሉ፤ ይህም በመረጃ ክምችት ውስጥ ያሉ መረጃዎችን በቀላሉና ትርጉም ባለው መንገድ፣ ሰዎች እንዲረዱትና ለውሳኔ አሰጣጥም አመቺ በሆነ አገላለፅ እንዲቀርብ የሚደረግበት ሂደት ነው፡፡ 




© Medium   













Short info

× Chat