askwala.com - E = MC2 የተባለውን ታዋቂ ቀመር የሚያብራራው ደብዳቤ
Header







E = MC2 የተባለውን ታዋቂ ቀመር የሚያብራራው ደብዳቤ

Image name: E = mc2.jpg

በሳይንሱና በፊዚክሱ አለም ትልቅ ስም ያለው የአልበርት አንስታይን E = MC2 የተባለውን ታዋቂ የፊዚክስ ቀመር የሚያብራራ ደብዳቤ በ1.2 ሚሊዮን ዶላር መሸጡ ተነግሯል፡፡ የአንስታይን የእጅ ፅሁፍ የሆነው ይህ ደብዳቤ ቦስተን መቀመጫውን ባደረገ የአጫራች ኩባንያ ሲቀርብ፤ ሊሸጥ ይችላል የተባለበት ዋጋ 4 መቶ ሺ ዶላር ቢሆንም ከታሰበው ውጭ በሶስት እጥፍ አድጎ የአንስታይን ዋጋ ትልቅ እንደሆነ አሳይቷል፡፡
ተዋቂውን የፊዚክስ ቀመር የሚያብራራው የአንስታይን የእጅ ፅሁፍ እንደአውሮፓውያኑ በ1946 ጥቅምት 26 የተጻፈ ሲሆን የፖላንድ ሳይንቲስት የሆነው ዶ/ር ሊዩዲክ ሲልበርስታይን ላነሳው ጥያቄ እንደምላሽ የቀረበ ደብዳቤ እንደሆነም ተገልጿል፡፡ በእየሩሳሌም የሚገኘው የሂብሩ ዩኒቨርስቲ እንዳስታወቀው የአንስታይን የምርምር ወረቀቶች እንደ ፕሮጀክት ተሰባስበው ከሚገኙበት አርካይቭ፤ በጨረታ የተሸጠው ይህ ደብዳቤ ስለ E = mc2 ከሚያነሱና በአንስታይን እጅ ከተጻፈ አራት ታዋቂ ደብዳቤዎች መካከል ዋነኛው መሆኑን አስታውቋል፡፡
ከዚህ በፊት በ1949 በአልበርት አንስታን የተጻፈ ደብዳቤ እንዲሁ ለጨረታ ቀርቦ በከፍተኛ ገንዘብ የተሸጠ ሲሆን ይህም የአንስታይን ስራዎች እና ግኝቶች በሳይንስ አፍቃሪያን ዘንድ ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠቻው ያመላከተ ነው ተብሏል፡፡ እንደሚታወቀው ይህ ታዋቂ የፊዚክስ ቀመር ማስ - ስክዌር (2) ከሆነው የብርሃን ፍጥነት ጋር በሚኖረው ብዜት የሚሰጠውን ኢነርጂ በመስላት የማስና ኢነርጂ ተለዋዋጭነትን የሚያሳይ ሲሆን፤ በፊዚክሱ አለም ትልቅ ተፅዕኖ ከፈጠሩ የሳይንስ ግኘቶችም እንደ አንዱ ይታያል፡፡ 




© Thehackposts   













Short info

× Chat